Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

“አንዱ ቡድን ሌላዉን ጥሎ ለማለፍ የሚያደርገዉ ግብግብ ዉጤታማ ሊሆን አይችልም”ትንሳኤ ኢህአፓ

$
0
0

Tensaye
ድር ቢያብር አንበሳ ያስር!

እኛ የትንሳኤ ስብስብ በተለያዩ ጊዜያት በጽሁፍ፤ በሬዲዮ ብሎም በቴለቪዥን መስኮትያለንን አላማ ለኢህአፓ አባላቶችና በተለያዬ ምክንያት ከድርጅቱ ለወጡ እንዲሁም በድርጅቱ ዉስጥ ለመታገል ለሚፈልጉ ታጋይ ኢትዮጵያዉያን ሁሉ በተደጋጋሚ አሳዉቀናል፤ ዛሬም እንደገና ወደፊት ድርጅቱን ለማጠናከር ተገቢ ናቸዉ ብለን ለምንመኛቸዉና አጥብቀን ስለምንታገልለት ዴሞክራሲያዊ አካሄድ መተንተኑ ተገቢ ነዉ እንላለን፤፤

አሁንም ቢሆን የኢህአፓ ከሁለት መከፈል እጅጉን አሳዝኖናል፤ አበሳጭቶናልም፤ ይህነዉ የሚባል ወይም መሰረታዊ የሆነ የአላማ፤ የርእዩተ አለምና የራእይ ልዩነት ሳይኖር፤ ብዙ ጓዶች ዉድ ህይወታቸዉን የገበሩበት፤ የቆሰሉለትና የደሙለትን ድርጅት፤ ሃላፊነት በጎደለዉና ከምክንያት ይልቅ በስሜት ተገፋፍቶ፤ በግብር ይዉጣ መልክ ድርጅቱን መከፋፈልና ትግሉን አደጋ ላይ መጣሉ፤ በትንሳኤ ስር የተሰባሰብነዉን ጓዶች አንገብግቦናል አሳስቦናልም፤ ለዚህም ነዉ እራሳችንን አሰባስበንና አጠናክረን በዲሞክራሲያዊ ማእከላዊነት የሚመራና፤ ከሁላም በላይ ለሰፊዉ ህዝብ የበላይነት የሚታገል የጋራ አአንድ ኢህአፓ ለማሰባሰብ ያለምነዉ፤፤
ትንሳኤ የኢህአፓ ልጆች ሲል ከሳሾቻችን እንደሚሉት ለወያኔ ያደረዉን፤ ወይንምየኢትዮጵያን ህዝብ ጥቅም አሳልፎ የሰጠዉን፤ አሊያም መስዋትነት የተከፈለበትን የመብትጥያቄ የረገጠዉን ሳይሆን፤ የህዝብን ችግር የራሱ አድርጎ የተነሳዉን፤ በሃገር ፍቅር ስሜትየተቃጠለዉንና፤ የሰማእታትን የትግል አርማ ለመሸከም የሚፈልገዉን፤ አላማ ጽኑ ታጋይ ማለታችን ነዉ፥ ኢህአፓ ይጠናከር፤ ከዉስጥም ሆነ ከዉጭ ያሉትን እናሰባስብ ስንል፤ እነዚያን ለህይወታቸዉ ሳይሳሱ ከጠላት ጋር በመተናነቅ አኩሪ ታሪክ ያስመዘገቡትን፤ በደማቸዉ ታሪክ የጻፉትን፤ በአጥንታቸዉ የኢህአፓን ሰንደቅ ከፍ አድርጎ ለመስቀል ሲሉእንደወጡ የቀሩትን፤ እሬሳቸዉ በየመንገዱ የተጣለዉን፤ በጅምላ በአንድ ጉድጓድ የተቀበሩትንና ፤የአዉሬ እራት የሆኑትን ጓዶች በማሰብ ነዉ፤፤
ኢህአፓ ተጠናክሮአል፤ አባላቶችም እየበዙ ነዉ፤ በህዝብ ዘንድም ሰርጾ እየገባ ነዉ፤ለምትሉን መልሳችን፤ ቤታችን ኢህአፓ ሲሞቅና፤ ሲቀዘቅዝ የትግል እሳቱም ሲጋይና፤ ሲዳፈን ነበርንበትና፤ በደንብ እናዉቀዋለን፤ በአሁኑ ሰአት ኢህአፓ መከፋፈልና መዳከም ብቻ ሳይሆን፤ በህዝባዊ ትግሉ ይህ ነዉ ሊባል የሚችል አወንታዊ ዉጤት ባለማሳየቱ፤ እታገልለታለሁ ከሚለዉ ህዝብ ጋር መራራቅ ብቻ ሳይሆን፤ ህዝቡም የኢህአፓን እንደ ድርጅት መኖርና መንቀሳቀሱን በመርሳት፤ ኢህአፓ በተባለ ቁጥር ኢህአፓ ደግሞ አለ ብለዉ የሚጠይቁ ብዙዎች ናቸዉ፤ ስለዚህ ያልተደረገዉን እንደተደረገ በማስመሰል፤ የህልም ዳቦ መግመጡን ትተን፤ ድርጅቱን እናጠናክረዉ እናጎልበተዉ ነዉ የኛ ምክር አላማም፤፤
እንዲያዉም እራሱን ኢህአፓ ነን በሚለዉ ቡድንና፤ ተገንጥሎ ወጥቶ እራሱን ኢህአፓ-ዴ ብሎ በሰየመዉ ቡድን፤ እርቅ ሰላም ለማዉረድ በቅርቡ የተሞከረዉ ጥረት ፍሬ ሳያሳይ በመቅረቱ፤ በጉጉት የጠበቅነዉም የአንድነት ትግል መጀመር በመጨናገፉ ቁጭታችን ከፍ ያለ ነዉ፤ ይህ ሙከራ ግዜ የፈጀ ዉጣ ዉረድ የነበረበት ስለነበረ፤ ዉድ ጊዜያቸዉን አጥፍተዉ ድርጅቱን ለማዳን የደከሙትን፤ ከወዲሁ እያመሰገን ይህን ቀና ሃሳብ የደገፉትን አበጃችሁ ስንል፤ ጀርባቸዉን የሰጡትን ግለኞች ደግሞ ሌላ ምንም ማለት አንችልም፤ የሰማእታት አጽም ይፋረዳችሁ ከማለት በስተቀር፤ ይህ እርቀ ሰላም ቢሳካ ኖሮ ኢህአፓን እንደ ድርጅት ከማጠናከሩም በላይ፤ በአሁኑ ሰአት የኢትዮጵያ ህዝብለሚያደርገዉ ጸረ ወያኔ ትግል፤ አጋዥም አበረታችም ይሆን ነበር፤ አለመታደል ነዉ እንዲሉ፤ በአመራር ቦታ ያሉትና፤ እርቅ ሰላሙን የተሳተፉት ጓዶች ቅራኔን ከማርገብ ይልቅ ማፋፋምን፤ ልዩነትን አጥብቦ በጋራ ከመቆም ይልቅ ቃላትን በመሰነጣጠቅ ልዩነትንአስፍቶ በተናጠል መቆማና፤ እንደጠላት መተያየትን መርጠዋል፤ ይህ ከድርጅትና ከጋራ ጥቅም ይልቅ ተክለ ሰዉነትን መገንባት የተጠናወተዉ በሽታ፤ ለድርጅቱ ዉድቀት ብቻ ሳይሆን በኢትዮጵያ ህዝባዊ ትግል ላይም የማይሽር ጠባሳ እንደሚያሳርፍም ጥርጥር የለነም፤፤

የዛሬን አያድርገዉና፤ ትናንትና በኢድሕቅ የትግል ሂደት ዉስጥ መኢሶን ጎን የተሰለፈዉ ኢህአፓ ዘንድሮ በዉስጡ የተፈጠሩ ችግሮችን በዲሞክራሲያዉ ሁኔታ መፍታት፤ ለኢትዮጵያ ህዝብ ትግል ሲባልም ይቅር ተባብሎና፤ ተቻችሎ ትግሉን መቀጠል አለምቻሉ ሁላችንም ያስገረመ ሚስጥር ብቻ ሳይሆን፤ ድርጅቱ ምን ያህል ከዲሞክራሲያዊ አሰራርና ከምንክንያት ጋር እንደተጣላም ያመላክታል፤ ድርጅቱ የራስ ንብረት ይመስል፤ ሌሎችን ድንጋይ ተሸክመዉ ይቅርታ ካላሉ፤ አይናች ሁን ላፈር ማለት፤ አዋቂነትን ሳይሆን አምባገነናዊ ባህሪን የሚያሳይ ነዉ፤ ስለዚህ ኢህአፓ አብቦና አፍርቶ ለማየት የምንፈልግ ሁሉ ነገሩን በአንክሮ ተመልክተን መወያየትና ለችግሮችም መልስ መሻት ተገቢ ነዉ እንላለን፤፤
ለነገሩማ በአመራር ቦታ ብዙ ጊዜ መቆየት ድርጅትን የግል ንብረት አድሮጎ የማየትንአባዜ ያስከትላል፤ ተመክሮአችን ሁሉ የሶሻሊስት ፍልስፍና ሆነና፤ ሁላችንም ከድርጅት የስልጣን ኮረቻ መዉረድን ወይም ለሚገባዉ ሰዉ ስልጣን መልቀቅ ተገቢ ስርአት አድሮጎ መቀበል ተስኖን፤ እንደወያኔዉ አምባገነን መሪ ሞት ካልወሰድን በስተቀር የሙጥኝ ማለቱን ተያይዘነዋል፥ ድርጅቱን የግል ንብረት አድርጎ መቁጠር ብቻ ሳይሆን አንዳንዶቻችን የድርጅት አባላትም ጭምር የመለኮትን ያህል እንዲያመልኩን እንሻለን፤ በቅርቡ ከወያኔ አገዛዝ በራሱ ፈቃድ ጥሎ የወጣዉ አቶ ኤርሚያስ ለገሰ፤ የመለሰ ቱርፋቶች በሚለዉ መጣጥፉ፤ ምን ያህል የወያኔዉ ድርጅት የአቶ መለሰ ዜናዊ የግል ንበረት እንደሆነና፤ አቶ መለሰም በድርጅቱ ላይ የነበራቸዉን ያልተገደበ ፍጹማዊ ስልጣን አመላክቷል፤ ስለዚህ እንደዚህ አይነት በድርጅት ዉስጥ የሚፈጠሩ ግለሰብ አምላኪነትና ያልተገደበ ስልጣን መኖርን፤ ሁላችንም ለዲሞክርሲ፤ ለፍትሕና ለእኩልነት የምንታገል ሁሉ ልናወግዘዉ ይገባል፥ በአመራር ቦታ የሚቀመጡ መሪዎች የስልጣን ጊዜያትና ገደብም እንዲኖራቸዉ የግድ ይላል፤ ድርጅቶችም ይህን በተመለከት ህግ ማዉጣት ብቻ ሳይሆን ለተግባራዊነት መታገል አለባቸዉ፤በድርጅት ዉስጥ የታቀፉ አባላትም፤ ከግለሰብ አምላኪነትና ከቡድንነኝት ነጻ በሆነ መንፈስ ሃላፊነታቸዉን መወጣት ይኖርባቸዋል፤ ማንኛዉን አይነት አምባገነናዊ ባህል ማስወገድና በምትኩ የተለያዩ ሀሳቦች ሊሸራሸሩበትና አባላት ያለምን ስጋት ያላቸዉን ልዩነት ሊያሰሙበት የሚችል መድረክ መፍጠር ተገቢ ነዉ፤፤

የአምባገነን ባህል አሜን ብሎ የተቀበለ፤ ስልጣንን ከሃላፊነትና ከተጠያቂነት ማጣመርየተሳነዉና፤ መመረጥንም ሆነ ስልጣን መልቀቅን ማቀናጀት የማይችል ድርጅት እንኳን ህዝብንና አገርን ነጻ ሊያወጣ ይቅርና እራሱንም ነጻ ማዉጣት አይችልም፤ አጋጣሚ ሰጥቶትም ስልጣን ላይ ቢቆናጠጥ ለህዝብ ነቀርሳ እንጅ መፍትሔ እንደማይሆን ወያኔ በአሁኑ ሰአት በኢትዮጵያ ህዝብ የሚያደርሰዉ ግፍ በቂ ምስክር ሊሆነን ይገባል፤ ስለዚህ የአባላቶች ንቁ ተሳትፎ፤ አዙሮ መመልከትን ብሎም ተላምጦ የተሰጠን ብቻ ከመዋጥ ይልቅ እራስም ማኘክን መልመድ፤ ድርጅትንም ሆነ አገርን ከጥፋት ያድናል፤ አለበለዚያ ግን እነዚያ እንደመልኮት ሲታዩ የነበሩ አመራሮች መምራት ሲያቅታቸዉ ወይም በሞት ሲለዩ ድርጅቱ ሞተሩ እንደተበላሸ ተሽከርካሪ መቆሙ የማይቀር ይሆናል፤፤

ከዚህ ባሻገር በቅርቡ ስለወጣዉ የኢህአፓ-ዴ እና እርማት እንቅስቃሴ ስለ ተባለዉ ቡድን የጋራ መግለጫ በኢንተርኔት ድረገጽ ተመልክተናል፤ በጥቅሉ ጅማሬዉንና፤ ጽንሰ ሃሳቡን የምንደግፈዉ ቢሆንም በ አሰራሩ ላይ ግን ልዩነት አለን፤ በቅድሚያ በጥሪዉ ሆነ በመሰናዶዉ የኢህአፓ ጉዳይ ይመለከታቸዋል የተባሉትን ሁሉ ማሳተፍ ተገቢ ነዉ፤ በተለይም በአሁኑ ሰአት የተለያዩ ቡድኖችም ሆነ ግለሰቦች ኢህአፓን አንድ ለማድረግ በሚንቀሳቀሱበት ጊዜ ከወዲሁ እነሱን ማማከርና በሂደቱ እንዲሳተፉ መጋበዙ ተገቢ ሆኖ እያለ፤ አንዱ ቡድን ሌላዉን ጥሎ ለማለፍ የሚያደርገዉ ግብግብ ዉጤታማ ሊሆን አይችልም፤ ትንሳኤም የተነሳለት አላማ ግብግቡ ቀርቶ ሁሉም ጓዶች በሰከነና አስተዋይነትበተሞላበት ሁኔታ ችግሩን በአንክሮ ተመልክተዉ መፍትሔ ላይ እንዲደርሱና አንድ ኢህአፓን ይዘዉ እንዲወጡ ስለሆነ አላማችን፤ ከወዲሁ አሰራሩ ሁሉንም እንዲያቅፍ እናሳስባለን፤፤
ኢህአፓ በተባበረ ክንዳችን ይጠናከራል፦
የኢትዮጵያ ህዝብ ያቸንፈል፦


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>