በመላው አለም ለምትገኙ ኢትዮጽያዊያኖች ሁሉ ፤ በተለያዩ ግዜያት ሰብአዊ መብታችን ይከበር ዘንድ ፤ ከምድር ሱዳን የሲቃ ጮኸታን ሰምታችሁ በተቻላችሁ መጠን ትታደጉን ዘንድ ደጋግመን በፁሁፍ አሰምተናል ፤ እንሆ በአሁኑ ሰአት ወያኔ ከምንግዜውም በላይ በከፋ መልኩ ፤ ካርቱም ውስጥ ስደተኛውን አንደተለመደው እያሳፈሰ ፤ ወዳልታወቀ እስር ቤት እያሳወሰደ ይገኛል ፤ በተለይ ጀዋዛት እየተባለ በሚገኘው እስር ቤት ውስጥ ፤ በሸህ የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ታጉሮው ይገኛሉ ፤ ከእነዚህም ውስጥ ለልደት ደሮ ለመግዛት ገበያ የሔዱ እህቶቻችን ከነደሮቸው ፤ ልደትን መድሀኒአለም ቤተክርስትያን አክብረው የሚመለሱ ነጭ የለበሱ ወገኖች እስር ቤቱን ሞልተውታል ፤ በተጨማሪ ዴም እየተባለ ከሚጣረው ሰፈር ውስጥ አንድ ወጣት ሀለፎም አዲሱ ተካልኝ የተባለ የአንገት መስቀሉን በጥሰው መኪና ላይ ጭነው እስር ቤት አጎረውት ይገኛል ፤ መታወቂያ ለማውጣት እድሜው የማይፈቅድ ወጣት ሳይቀር ያለ አንዳች እርህራሔ አስር ቤት ይገኛል ፤ ይህን ወጣት እንደምሳሌ ተጠቀምንበት እንጅ በርካታ ወጣቶች መኖራቸውን አናሳስባለን;;
ዛሬ አንባገነኑ ወያኔ ፤ በከፍተኛ መረበሸ ውስጥ አንዳለ ፤ እድሜው እያጠረ ፤ የቆመበት መሬት እየከዳው መሆኑን እንገነዘባለን ፤ ለዚህም ሱዳን ሀገር የሚኖረውን ስደተኛ ፤ ከኤርትራ በኩል ከሚንቀሳቀሱትና ከሌሎች በነፍጥ ከሚታገሉት ጋር ግንኙነት አላቸው ብለው ስለሚየምኑና ፤ እንዲሁም ሰሞኑን በሱዳን አጎራባች አርማጭሆ አካባቢ በተፈጠረው ሁኔታ በመስጋት ፤ ካርቱም የሚኖረውን ስደተኛ ሕጋዊ የሰደተኛ መታወቂያ ፤ በየሶስት ወር የሱዳን መንግስት ሲያድስ የነበረውን፤ ኢትዮጽያዊ ስደተኛ የለም በማስባል ፤ መታወቂያችን ወያኔ ከፍተኛ ገንዘብ በመክፈል መታወቂያ እንዳይታደስ አስደርጎል ፤ ይህም ማለት ፤ የሚፈልጉትን ስደተኛ በአፈሳ መልክ አፍነው እንዲወስዱ ያስችላቸዋል ፤ ባሳለፈነው ወር የወያኔ ምክር ቤት ያፀደቀወን በአሸባሪና ወንጀለኛን ስም ስደተኛውን አሳልፍ በመስጠት የተደረገውን የትብብርን ውል ልብ ይሎል ፤ በተጨማሪ ጀዋዛት እየተባለ በሚገኘው እስር ቤት ውስጥ የታጎሩትን የስደተኛ መታወቂያ የያዙትን እያሳነጠቁ ፤ ወያኔ ከሱዳን መንግስት ጋር በመመሳጠር ፤ አለማአቀፍ የስደተኞችን ህግ በመጣስ ፤ ስደተኛ መብትን በመንፈግ ሕገ ወጥ በሆነ አሰራር መታወቂያ አስር ቤት ውስጥ አስገድደው ፎቶ እያስነሱ ስደተኝነትን የማይገልፅ መታወቂያ በመሰጠት ላይ መሆናቸውን አጥብቀን እንናስገነዝባለን ;;
ባሳለፍነው ወር የወያኔን መሰሪ ተንኮል ማጋለጣችን ይታወቃል ፤ ይኸውም ስደተኛውን ማህበረሰብ ቅጥ ባጣ አፈሳ በማስመረር በወያኔ ሰላዮች አማካኝነት የወያኔ ኢንባሲ ካርቱም ውስጥ በ28/11/2014 ሰላማዊ ሰልፍ አስደርገውል ፤ የሰልፉም አላማ የኢሳትን ሚዲያ በመጠቀም ፤ ወደ ሀገራች አንግባ የሚለውን መልእክት ለማስተላለፍ የታቀደ ነበር ፤ እነዚህ ሰብአዊ ክብር ያልፈጠረባቸው ቅጥረኞች በግፍአን እንባ አንዳላገጡ እንረዳል ፤ በተጨመማሪ እነዚህ በደል የበዛባቸው ወገኖቻችን ፤ለጥያቂቸው መልስ የሚያገኙ መስሎችው ተመልሰው ወያኔ ኢንባሲ በሳምንቱ ሔደው ማንም ሳያናግራቸው በመጡበት አኾሖን ተመልሰዋል;;
ውድ ወገኖቻችን ፤ ሱዳን ሀገር ውስጥ የሚደረሰውን በዝምታ የማይታለፍ በደል ከከፈ ደረጀ ከመድረሱ በፊት ፤ በመላው ዓለም የምትገኙ ለሰብአዊ መብት መከበር የምትታገሉ አለም አቀፍ ትብብር የፈጠራችሁ ወገኖች ሁሉ ፤ዛሬም ጨኻታችን ጣራ አልባ እንዳይሆን ፤ ለሱዳን መንግስትና ለዩ ኤን ኤች ስ አር በተቀነባበረ መልኩ ሰብአዊ መብታች ይከበር ዘንድ ፤ በሱዳን ሀገር የምንገኝ ኢትዮጽያዊያን ልሳን ትሆኑን ዘንድ በአክብሮት እንማፀናለን ;; ባሳለፍነው ወር 2000 ወገኖቻችን የ ኤች አይቭ ና የሀቢታይትስ በሸተኞች ናቸው ተብለው ፤ ገንዘብ ንብረታቸውን ሳይውሰዱ ከሱዳን ሲባረሩ አንድም ተቆርቆሪ ዜጋ የነዚህ ግፍአን ልሳን ሳይሆን በመቅረቱ ልብን ያደማል ፤ አሁንም ፤ አሁንም ፤ ይኽ የወያኔ ተንኮል በሰፊው ሳይደገም አፋጣኝ ወገናዊ ትብብራችሁን አንጠይቃለን;;
አጥናፉ መሸሻ