(ሳተናው) የአንድነት ፓርቲ ጠቅላላ ጉባኤ በጥሩ ሁኔተ እየቀጠለ ነው። ምርጫ ቦርድ ሕጉ በሚጠይቀው መሰረት ጠቅላላ ጉባኤ ለመታዘብ አልተገኘም።
አቶ አለነ ማጸንቱ አቶ በላይ ፍቃዱን ኢንዶርስ አደርገው ራሳቸው ከ እጩነት አወጥተዋል። ምርጫዉ በአቶ ዳግማዊ ተሰማና በአቶ በላይ ፍቃዱ መሃከል ነው የሚደረገው።
የአንድነት ፓርቲ ዛሬ ጥር 3 ቀን ጠቅላላ ጉባኤዉን ያደርጋል። ምርጫ ቢቦርድ ከሕግ ዉጭ አንድነት ፓርቲ የሚወዳደርበትን የምርጫ ምልክት አልሰጥም በሚል፣ አንድነትን ከምርጫዉ ለማስወጣት ደፋ ቀና እያለ ነው። የአንድነት ፓርቲ ግን ምርጫ ቦርድ ያስቀመጠውን መሰናክል ለማለፍና ለምርጫ ቦርድ ቀዳዳዎችን ሁሉ ለመዝጋት በሚል ነው ስብሰባው የተጠራው። በዚህ ጠቅላላ ጉባኤ ምርጫ ቦርድ እንዲገኝ ጥሪ የቀረበለት ቢሆንም ሌሎች ግለሰቦች ጠቅላላ ጉባኤ ተጠርቷልና በሁለት ስብሰባዎች መገኝት አንችልም በሚል ታዛቢ እንደማይልኩ በደብዳቤ ገልጸዋል። ሆኖም የአንድነት ፓርቲ ምርጫ ቦርድ ኖረም አልኖረም ጠቅላላ ጉባኤዉን እንደሚያደርግ በመግለጽ ለምርጫ ቦርድ ምላሽ ሰጥቷል።
12፡30 PM አዲስ አበባ ሰዓት
በአንድነት የጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ ምርቭጫ ቦርድ በሕግ ታዛቢ የመላክ ግዴታ ነበረበት። ሆኖም ምርጫ ቦርድ ታዛቢ አላከም። በሕወሃት የተሰተዉን አንድነትን የ”ማገድ” የፖለቲክ ዉሳኔ ለማስፈጸም የቆረጠ ይመስላል።
12፡00 PM አዲስ አበባ ሰዓት
አቶ ዳግማዊ ተሰማ፣ የኦዲትና ኢንስፔክሽን ሰብሳቢ የነበሩ ሲሆን፣ ከሰብሳቢነታቸው ሪዛይን አደርገው ራሳቸውን ለሊቀመንበርነት ራሳቸው እጩ አድርገው አቅርበዋል። “እኔን ብትነርጡኝ አንድነት የበለጠ ትልቅ ደረጃ እንዲደርስ ለማድረግ እሰራለሁ።ኔን ብትመርጡኝ “በተሻለ አደረጃጀት ከተፎካካሪ በተሻለ ሁኔት ልመራ እችላለሁ” ሲሉ ጉባዬተኞች ድምጽ እንዲሰጧቸው ጠይቀዋል። ሶስት እጩዎች ቀረበው ፣ አንዱ አቶ አለነ አቶ በላይን ኢንዶርስ በማድረጋቸው፣ የቀሩት ተወዳዳሪዎች አቶ ዳግማዊ ተሰማና አቶ በላይ ፍቃዱ ናቸው።
11፡30 AM አዲስ አበባ ሰዓት
አቶ አለነ ማጸነቱ ንግግር እያደረጉ ነው። አንድነት ከሌሎች ፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በመተባበር ትግሉን እንደሚያሳድጉ ተናግረዋል። ምሁራን ወደ ትግሉ እንዲመጡ ትልቅ የማግባባት ሥራ እንደሚሰሩ ተናግረዋል። አቶ አለነ ስለ አት በላይ እየተናገሩ ነው። አቶ በላይ ያደረጉት አስተዋጾ በመጠቀስ ፣ “እኔን ለመምረጥ ያሰባችሁ አባላት በላይ በፍቃዱን እንድትመርጡ እርሳቸውን ኢንዶርስ አድርጊያለሁ” ብለው አቶ በላይን ኢንዶርስ አድርገዋል። አስመራጭ ኮሚቴ ሌላ እጩ ካለ መቅረብ እንደሚችል በገለጹት መሰረት አንድ አባል “የድርጅት ጉዳይ ማምለካ አሰገብቼ ነበር። ” በሚል አቤቱታ አቅርበው፣ የ እጩነት ፎርም እየሞሉ ናቸው።
11፡30 AM አዲስ አበባ ሰዓት
የአንድነት ፕሬዘዳንታዊ ምርጫ ሊደረግ ነው። አስመራጭ ኮሚቴ ተመርጦ ቦታዉን ይዟል። አስመራጭ ኮሚቴው ለፕሬዘዳነት ምርጫ በብሄራዊ ምርጫ የተቀመጡ መመስፈርቶችን አነበቡ። በመስፈርቱ መሰረት ማንኛውም አባል ራሱን እጩ ማድረግ እንደሚችል አስመራጭ ኮሚቴ ለጠቅላላ ጉባኤ ራሱን እጩ አድርጎ እያቀረበ ነው። ሁለቱ አባላት ራሳቸውን እጩ አድርገው አቅርበዋል። አቶ በላይ ፍቃዱ እና አቶ አለነ ማጸንቱ እጩ ሆነው ቀርበዋል።
አቶ በላይ ፍቃዱ ንግግር እንዲያደረጉ በመርጫ ቦርድ ተጠይቀው መናገር ጀምረዋል። አንድነት ባለፊት ሲስት ወራት በ ከ15 ብቢሮዎች በላይ እንደተከፈቱ፣ በአጠቃላይ አሁን ወደ 30 ቢሮዎች እንዳሉት ገልጸዋል። የትግሉ ንቅናቄ በቢሮውች እንዲመሩ እናደርጋለን ብለዋል አቶ በላይ። “ምርጫ 2007 ፖለቲክ ለዉጥ ካልመጠ መቼም አይመጣም፣ ለዉጥ እንዲመጣ ከናንተ ሆነ መደረግ ያለበት እናደርጋለን” ሲሊ ለጉባየተኞቹ አስረድተዋል።
11:00 AM አዲስ አበባ ሰዓት
ዲፕሎማቶች አንድነት በጠራው ጠቅላላ ጉባኤ ተገኝተዋል። “የአንድነት አባል በአንድ ፌሽካ በአንድ ቀን መገኘት ይችላሉ!” የተከበሩ አቶ ግርማ ሰይፉ
10፡30 AM አዲስ አበባ ሰዓት
ተወካዮች ቦታቸውን ይዘዋል። የድርጅቱ ሊቀመንበር አቶ በላይ ፍቃዱ መቀመጫቸዉን ይዘዋል። ከክፍለ ሃገር የመጡ በርካታ የጠቅላላ ጉባኤ ተወካዮች የተወሰኑቱ በዚህ መልክ ነበር በአንድነት ጽ/ቤት ውጁስጥ ያደሩት።
የኢትዮጵያውያን ነፃነት ለማስመለስ እስከደም ጠብታ ለመክፈል የተዘጋጀ የአንድነት አባል ውርጭና ብርድ አይበግረውም!!!
ለነዚህ የኢትዮጵያ ልጆች ክብር ይገባቸዋል!!
እነዚህ በፎቶው ላይ የምትመለከቷቸው የአንድነት ጉባኤተኞች ከመላው የኢትዮጵያ ክልሎች በአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ላይ በገዢው የኢህአዲግ መንግስትና በማደጎ ልጁ የምርጫ ቦርድ እንዲሁም ህሊናቸውን በገንዘብ ሽጠው አንድነትን ለመፈረካከስ ከተነሱ ጥቂት ሆድ አደር የማፊያ ቡድኖች እየተሰነዘረበት ያለውን ተከታታይና እልህ አስጨራሽ ደባ ለማክሸፍ በ24 ሰዓት ጥሪ ከሞቀ ቤታቸው ወጥተው፤…… በአንድነት ፅ/ቤት በ03/05/07 ዓ.ም የሚካሄደውን ጉባኤ ለመታደም የአንድነት የክተት ጥሪ ቆራጥ ታጋዮች ናቸው፡፡ ….በፎቶዎቹ ላይ እንደምታዩት እነዚህ የኢትዮጵያን እጣ ፈንታ ለመወሰን በመታገል ላይ ያሉ ሰላማዊ ታጋዮች፤ ……ቁርጥራጭ ወረቀትና ማዳበሪያ አንጥፈው፤…… ድንኳንና ማዳበሪያ ለብሰው፤….በቀዝቃዛው የአድስ አበባ አየር የሲሚንቶ ወለል ላይ በብርድ የሚጠበሱ ቆራጥ፤ለለውጥ የተነሱና ለኢትዮጵያውያን ክብር ከሞቀ ቤታቸው ወጥተው ውርጭ የሚጠጡ፤……ኢህአዲግን እንቅልፍ አሳጥተው የሚያቃዡ ጀግኖቻችን ናቸው!!! ……በእውነት ሁሉም ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ክብር ሊሰጣቸው ይገባል፡፡
==================
በኢትዮጵያውያን ህዝቦች ገንዘብ የኢህአዲግ ካድሬዎች በሊሙዚን መኪና እየተንፈላሰሱ፤……በአለም ላይ እጅግ የቅንጦት ሂወት በሚባል አኳኋን እየኖሩ፡፡ ……ውስኪና ቮድካ ጨብጠው ለቅጥረኞቻቸው በሚያስተላልፉት ቀጭን ትእዛዝ እልፍ የነፃነት አርበኞችን እያስገደሉ፤እያሳሰሩ፤እያሰደቱ…… በህዝብ ሀብት በሚንቀሳቀሰው የህዝብ ሚዲያዎች በቅንጦት ብቅ እያሉ የፍትህና ዴሞክራሲ ተረጋግጧል፤….ሀገሪቱ በሁለት ዲጂት አደገች….ምናምን እያሉ የሚደሰኩሩ አንባገነን የኢህአዲግ ባለስልጣናት ባሉበትና የኢትዮጵያውያንን ነፃነት በጠብ መንጃቸው ቁጥጥር ስር ያረጉትን ኢህአዲጋውያን፤…..ለመታገል ክብርና ነፃነታችንን ከአፈሙዛችሁ ስር ፈልቅቀን እናወጣለን ብለው በውርጭ ለሚጠበሱት የአንድነት አባላትና አመራሮች ስለእውነት የሚያስብ ሁሉ ክብርና አድናቆት ሊሰጣቸው ይገባል!!! ……ውድ የኢትዮጵያ እውነተኛ ልጆች!!! ….እመኑኝ አንድነትን ሊያቆመው የሚችል ሀይል የለም፡፡ ….የምንታገለው ምርጫን የመጨረሻ የትግል ሂደት አድርገን አይደለም፤…. በመሆኑም በነዚህ ብርቅዬ ታጋዮች ስም አንድነት ፓርቲ በተከታታይ ለሚወስናቸው ፖለቲካዊ ውሳኔዎችና የትግል ጥሪዎች አጋርነታችሁን እንድታረጋግጡ መልእክቴን አስተላልፋለሁ፡፡ ……በ2007 ኢህአዲግ የፈራው ለውጥ አይቀሬ ነው፤….ድል የህዝብ ይሆናል!!! ….ለለውጥ እንነሳ!!!