Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

ከመላው አገሪቷ በአንድ ቀን፣ በአንድ ፊሽካ ጥሪ፣  የአንድነት ጉባኤተኞች ተሰባስበዋል

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) “አንድነትን ለመታደግ ከየአቅጣጫው እየተመመ ያለው የአንድነት የሰላማዊ ትግል ሰራዊት፣ በጊዜ በዋናው ጽ/ቤት ከትመዋል፤ ይሄው ታሪክ ሊሰራ፣ የምርጫ ቦርዱ አሳፋሪነት፣ የስርዓቱ ሽፍትነት ሊመሰክር፤ ይህን የአንድነት ልጆች ተጋድሎ ለልጅ ልጅ ሊነግር ታድመዋል።

unnamed (1)ይህ ትልቅ ታሪክ ሲፈፀም በቦታው ተገኝቼ ለመመልከት በመቻል ኩራት ነው የሚሰማኝ”  ሲሉ አስተያየታቸዉን የሰጡት የአንድነት ተጠባባቂ የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ሃላፊው አቶ አስራት አብራሃ፣   ነገ እሁድ በሚደረገው ጠቅላላ ጉባኤ፣  አባላት፣  በአራት ቀናት ጥሪ ፣ በቁጭትና በቁርጠኝነት፣  በልባቸው የነጻነትን ደዉል እያቃጨሉ መምጣታቸው እንዳኮራቸው ይናገራሉ።

 

“በአሁኑ ሰዓት ከመላ ሀገሪቱ በአንድ ቀን፤ በአንድ ፊሽካ ጥሪ የአንድነት ጉባኤተኛ አንድነት ፓርቲን በኢህአዲግ ከሚመራው ምርጫ ቦርድና ተላላኪ ወንበዴዎች ሴራ ለመታደግ ብሎም ቀጣይ የትግሉ ምእራፎች ላይ ለመምከር በአሁኑ ሰዓት በአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ዋና ፅ/ቤት ከተን ገብተናል” ሲሉ አንድ የአንድነት አባል አስተያየት ሲሰጡ ፣ ሌላው አባል ደግሞ  “ከተቋቋመበት ጊዜ አንስቶ አንድም ነፃና ፍትሀዊ ምርጫ አስፈፅሞ የማያውቀው የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ፣ ኢህአዴግ ምርጫ እንዲያጭበረብር በመፍቀዱ ሳቢያ ምርጫን ተከትሎ በሚነሱ አለመግባባቶች በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ደማቸው በየመንገዱ ፈሷል፡፡ ምርጫ ቦርድ ከገዳዮቹ ባልተናነሰ የእነዚህ ውድ ኢትዮጵያውያ የደም እዳ አለበት፡፡ ያለጥርጥር የምርጫ ቦርድ ሀላፊዎችም ከገዢው ቡድን ሹማምንት እኩል የደም ዕዳቸውን የሚያወራርዱበት ቀን ሩቅ አይሆንም፡፡” ሲሉ ምርጫ ቦርድ እያደረገ ባለው ነገር በታሪክ ተጠይቂ እንደሚሆን ገልጸዋል።

unnamed

“ምርጫ ቦርድ እየተባለ የሚጠራው የኢህአዴግ ተቀፅላ ተቋም አጅግ አስደማሚ ጠቅላላ ጉባኤ ባካሄድን ማግስት በአራት ቀናት ውስጥ ሌላ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ጠርታችሁ እንደገና ፕሬዚደንቱ ካላስመረጣችሁ የመጨረሻ እርምጃ እወስዳለሁ በማለት ሱሪ በአንገት በሆነ ሁኔታ በድጋሚ ሌላ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ እንድንጠራ ተገደናል፤ የጠቅላላ ጉባኤ አባላት ከየቦታው ከአራቱም የሀገሪቱ አቅጣጫዎች ክተት ብለው ሌሊትና ቀን ተጉዘው ፓርቲያቸው ለማዳን በጊዜ ደርሰናል” ሲሉ አንድ ሶስተኛ አባል ይናገራሉ።

 

ምርጫ ቦርድ ሕግ በሚጠይቀው መሰረት ታዛቢዎች እንዲልክ ደብዳቤ ቢደርሰውም፣ ራሱ ባደራጃቸው በነአየለ ስምኔህ፣ ዘለቀ ረዲ ቡድን “ሌላ ጠቅላላ ጉባኤ ተጠርቷል” በሚል እንደማይገኝ በደብዳቤ አሳውቋል። ሆኖም የአንድነት አመራር አባላት “ምርጫ ቦርድ ተገኝም፣ አልተገኝም፣ ጠቅላላ ጉባዬያችንን እናደርጋለን።  በድጋሚ እንደገና ከቀበና ጽ/ቤታችን የዲሞክራሲ፣ የለወጥና የነጻነት ደዉል እንደዉላለን” ሲሉ በአገር እና ከአገር ዉጭ ያለው ኢትዮጵይዊ ሁሉ በዚህ ወሳኝ ወቅት ከጎናቸው እንዲሁን ጥሪ አቅርበዋል።

 

“በዚህ ስርዓት ስር ለአንድ ሌሊት እንኳ ቢሆን በሰላም ተኝቼ ካደርኩኝ ቀኜ ይረሳኝ፤ የረገጠኩት መሬት ይክዳኝ” እንዳሉት የአንድነት የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ሃላፊው አቲ አስራት አብርሃ፣ በአንድነት አመራሮች፣ አባላትና ደጋፊዎች ዘንድ ትልቅ ቁርርጠኝነትና ወኔ እየተያ እንደሆነ የሚደርሰን ዘገባ ያመለክታል።

 

እሁድ ለሚደረገው የጠቅላላ ጉባኤ ከመላው አገሪቱ እየተመሙ የመጡ የአንድነት ተወካዮች በአንድነት ጽ/ቤት

 

 

 


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>