ከ-ከተማ ዋቅጅራ
ወያኔ ማለት፡- ወይ ያኔ የሚለውን ፍቺ ይሰጠናል። ወይ ያኔ ደግሞ የቁጭት ቃል ነው። ይሄ የቁጭት ቃል ምስረታቸው ጋር ይወስደናል።ጥቂት ሆነው ወደ መሰረቱት ጋር ያኔ ነበር ስሩን ማድረቅ ያኔ ነበር በአንድ ቦንብ እህ ማለት የሚለውን የቁጭት ቃል ይነግረናል። ወያኔ (ወይ ያኔ) ያኔ ተመሰረቱ ለነሱ አላማ፣ ለነሱ ድብቅ እቅድ፣ ለነሱ የደም ማፍሰ እርካታ፣ ተመሰረቱ። ታዲያ ያንን ድብቅ አላማቸውን ለማሳካት የራሳቸው የቅርብ ሰው የሚባሉትን በአላማቸው ያልሄዱትን የፈጁ እና ያስፈጁ የማፊያ ግሩፕ ናቸው። ምስኪኑን የትግራይ ህዝብ በማያውቀ ለድብቅ አላማቸው ያለምንም ርህራሄ ዳር ቆመው ድብቅ ሴራቸው ለማስፈጸም ወገኑን በማያውቀው እንደ ቅጠል እንዲረግፉ ሲያደርጉ ልባቸው የደስታ እንጂ የሃዘን ስሜት አልነበራቸውም።
ወያኔ መሰረቱ ውሸት፣ ምሶሶው ውሸት፣ ግድግዳው ውሸት፣ ጣራውም ውሸት የሆነ የውሸተኞችና የማፊያ ግሩፕ ነው። አንድ ያነበብኩት ጽሁፍ ትዝ አለኝ፡ <<በኢሕአዲግ ዘምን የሚመረቁ ባለስልጣን እና ካድሬዎች ከአንድ ወፍጮ ቤት ተፈጭተው የወጡ እና እቤት ቁጭ ብለው ሁሉን ነገር በትእዛዝ የሚቀበሉ የወፍጮ ውጤቶች ምሩቆች ናቸው>> የሚለው ።በትክክል ይህ ሃሳብ ይገልጻቸዋል። ባለስልጣኑም ሆነ ካድሬው ወደ ወያኔ (ወይ ያኔ) ወፍጮ ቤት ይገባሉ 1ኛ ድግሪ 2ተኛ ድግሪ ማስተር ዶክተር ፕሮፌሰር እያለ የወፍጮ ውጤቶች የትምህርት ደረጃ ይሰጣቸዋል።ያልሆኑትን መሆን ያልሰሩትን ሰራን ማለት ተንኮል እና ውሸት ከመሰረቱ አይደለ። እናም ገና አፋቸውን ሲከፍቱ ማን ምን እንደሆነ ይታወቃል ወሬአቸው በሙሉ ዱቄት ዱቄት ይላል ምክንያቱም የአንድ ወፍጮ ፍጭት ውጤት ስለሆኑ ነዋ ! ምድረ ዱቄታም ሁሉ። አሁንማ ዱቄት ዱቄት የሚለውን ንግግራቸውን መስማት ህዝቡ ምን ያህል እንደሰለቸውና እንዳንገሸገሸው ቢያውቁት ዱቄት አፋቸውን በየመድረኩ በተገኘው አጋጣሚ አያቦኑብንም ነበረ።
ኢሕአዲግ ለህዝቦች እኩልነት የቆመ ድርጅት ነው ይሉናል ዋናዎቹ ካድሬዎች የወያኔ የወፍጮ ውጤቶች። እንዴት በምን አይነት መስፈርት በየትኛው ልኬት ነው ብለህ ስትጠይቃቸው በዱቄት አፋቸው ሳያፍሩ በዝርዝር ያቦኑታል እዚህ ዝርዝር ውስጥ አልገባም እኔም ዱቄት ማቡነን እንዳይሆንብኝ። ግን በትንሹ የህዝቡን ቁጥርና የስራ ድርሻቸውን እንቃኛለን። ለህዝቦች እኩልነት የቆመ ድርጅት ነው ስለሚሉ የቱ ጋር ነው እኩልነቱ ያለው የሚለውን ለማየት…. ኦሮሞ 34.5% አማራ 26.9% ሶማሌ 6.2% ትግሬ6.1% ሲዳማ 4.1% ጉራጌ 2.8% ወላይታ 2.3% ሃድያ 1.7% አፋር 1.7% ይሄንን የቁጥር አሃዝ ያገኘሁት ከgoogle wikipedia ላይ ነው። ታዲያ አሁን ወደ እውነታው ስንመጣ መከላከያ ሚኒስቴር በሃላፊነት ቦታ ያሉት 94% ወያኔ ነው ደህንነት ምንስቴር፣ የውጪ ጉዳይ ሚንስቴር፣ ጉምሩክ፣ ኢምግሬሽን፣ አየር መንገድ፣ አየር ሃይል፣ ቴሌኮሙንኬሽን፣ መብራት ኃይል ሌሎችም በሙሉ እድርና እቁብ እራሱ ሳይቀር በወያኔ ካድሬ ነው የተያዘው። ይሄንን ደግሞ አገር ቤትም ሆነ በውጪ ባለው ህዝብ የታወቀ ነው።
በዱቄት አፋቸው ኢሕአዲግ ለብሔር ብሔሮች ነጻነት አመጣ ብለው ዱቄታቸውን ያቦኑብናል።የቱጋር ነው የብሔር ብሔረሰቦች መብት የተከበረው ከታች እስከላይ ሃገሪቷን የተቆጣጠራችሁት እናንተ ያውም ያለ መስፈርት ምንም እውቀትና ችሎታ ሳይኖራቸው ሌላው ግን ችሎታ ኖሮት እውቀት ኖሮት አቅም ኖሮት በነጻነት መስራት ያልቻለ ስንት ዜጋ አለ ብለህ በምትናገርበት ግዜ በየቦታው የተቀጠሩት ካድሬዎች የወፍጮ ቤት ወሬአቸውን ይጀምራሉ አድጋለች ተመንድጋለች ይሄ ገባ ይሄ ወጣ ይሄ ሆነ…. ወዘተ ይሉናል መቼስ የወፍጮ ቤታቸውን ወሬአቸውን እንድደግምላችሁ እንደማትፈልጉ አውቃለው የወያኔን ባህሪ የማያውቀው ሰው የለም ያልተረዳቸውም ዜጋ የለም ስለዚህ ዱቄቱን በማቡነን ውድ ህዝቤን አላሰለቸውም።
አሁን ግዜው የሰፊው ህዝብ ነው የወያኔ የግፍ ጽዋ ሞልቷል ግፍ የሰሩና የሚሰሩ በአገራችን ምድር የሚነግሱበት ግዜ መቋጫው ደርሷል የሕወሓት ዋና ዋና የማፊያው መሪዎች እርስ በእርስ እየተባሉ ነው አውሬ አውሬን እንደሚበላው። የመከላከያው ሰራዊት ደግሞ ወታደሩ ከነ ሙሉ ትጥቁ እየካደው ነው። ህዝቡ ደግሞ ወያኔን ለመደምሰስ አጋጣሚውን እየጠበቀ ነው። ይሄ ነው ድል ከአሁን በኃላ የወይ ያኔ (ወያኔ) ድምጽ የሚሰማ የለም በፊት እንደ ፈለጉ ሲንሸራሸሩበት የነበረ አገር አሁን እንደፈለጉት መንሸራሸር ቀረ በፊት በውጪ ተዝናንተው ይኖሩ የነበረ አሁን ግን በውጪ የሚኖረው ዜጋ መፈናፈኛ አሳጥቶአቸዋል። በፊት እያሳደዱን እየደበደቡን እያሰሩን እያሰቃዩን እያንገላቱን እየገደሉን ይኖሩ የነበረ። አሁን ግን ነገሮች ሁሉ ተቀይሮ ግጥሚያው ፊት ለፊት ሆኗል። ህዝብን ያሸነፈ ማንም የለም ህዝብ ሁሌም አሸናፊ ነው። ከውስጥ እስከ ውጭ ከመሃል እስከ ዳር ከደቡብ እስከ ሰሜን ከምዕራብ እስከ ምስራቅ በአንድነት ተነሰተናል ወያኔ ከገባበት ቃሪያ ውስጥ ሰንጥቀን ፍሬአቸውን ለማራገፍ በቆራጥነት ተነስተናል። ወያኔ ሆይ ከአሁን በኋላ ገድሎ መፎከር የለም አቃጥሮ መኖርም የለም አሰቃይቶ መክረምም የለም ጥቂቶችን የሆኑ ወያኔዎች ከነ ወፍጮ በታቸው ለማጥፋት ቆርጠን ተነስተናል። ኦሮሞው ጋር ሂድ ቆርጦ ተነስቷል አማራው ጋር ሂድ ቆርጦ ተነስቷል ሱማሌው ጋር ሂድ ቆርጦ ተነስቷል ደቡቡ ጋር ሂድ ቆርጦ ተነስቷል አፋሩ ጋር ሂድ ቆርጦ ተነስቷል።
ወይ ያኔ (ወያኔ) ሆይ አርቀህ የቆፈርከውን የግፍ እና የመከራ ጉድጓድ ከነጭፍሮችህ በመቅበር ለድል ለነጻነት ለዲሞክራሲ ለእኩልነት ለእድገት የምንዘምርበት ግዜ ደርሷል። ህዝቤ ሆይ ወይ ያኔን(ወያኔ) እንደ ቃሪያ ፍሬ አራግፈን እናስወግደው::ነጻነት ፈላጊ ነጻነት ያመጣል።
ከ-ከተማ ዋቅጅራ
Email-waqjirak@yahoo.com