(ዘ-ሐበሻ) ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችሎት ያስገባው የይግባኝ ጥያቄን ለመስመት ስድስት ኪሎ የሚገኘው ፍርድ ቤት ተሰይሞ የነበረ ሲሆን ጉዳዩን ተመስገን እስር ቤት ሆኖ በፕላዝማ ተከታትሏል::
ከ’ፍሪ ተመስገን ደሳለኝ” የፌስቡክ ገጽ የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው ዛሬ ታህሳስ 23/2007 ጠቅላይ ፍረድቤት በዋለው ችሎት የጋዜጠኝ ተመስገን ደሳለኝን ይግባኝ ከሰማ በኋላ ጉዳዩ ለይግባኝ ያስቀርባል አያስቀርብም የሚለውን ለመወሰን ለታህሳስ 30/2007 ዓ.ም ቀጥሮ ሰቷል፡፡
ጋዜጠኛ ተመስገን ችሎቱን የተከታተለው ዝዋይ እስር ቤት ሆኖ በፕላዝማ ነው::