Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

‹‹የግብፅ የውኃ ድርሻ እንደማይጐዳ ኢትዮጵያ በሰነድ እንድታረጋግጥ እንፈልጋለን›› የግብፅ ፕሬዚዳንት አልሲሲ

$
0
0

የግብፁ ፕሬዚዳንት አብዱልፈታህ አልሲሲ ኢትዮጵያ የግብፅ የውኃ ድርሻ እንደማይጐዳ በሰነድ እንድታረጋግጥ እንፈልጋለን አሉ፡፡ ፕሬዚዳንቱ እ.ኤ.አ. በጃንዋሪ ወር መጨረሻ ላይ ኢትዮጵያን ይጐበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

fad1600bf474567af7ce16118055d7d2_Lፕሬዚዳንቱ ባለፈው ሰኞ ከሦስት የግብፅ መንግሥት ጋዜጦች ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፣ በኢትዮጵያና በግብፅ መካከል በአሁኑ ወቅት መልካም ግንኙነት መኖሩን አስረድተዋል፡፡

እ.ኤ.አ. በጃንዋሪ 2015 ፕሬዚዳንቱ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ከሚያደርጉባቸው አገሮች መካከል ኢትዮጵያ አንዷ መሆኗን ገልጸዋል፡፡ ከኢትዮጵያ በተጨማሪ ፕሬዚዳንቱ ኩዌትን፣ ባህሬንና የተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስን እንደሚጐበኙ አስታውቀዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ ኢትዮጵያን በሚጐበኙበት ወቅትም በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ ውይይት እንደሚደረግ በሰጡት ቃለ ምልልስ ገልጸዋል፡፡ ‹‹እኛ የምንጠይቀውና የምንፈልገው ኢትዮጵያ ግድቡ የግብፅን የውኃ ድርሻ እንደማይጐዳ በቃል የሰጠችውን ዋስትና በሰነድ እንድታረጋግጥ ነው፤›› ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ፐብሊክ ዲፕሎማሲ ቡድን ከሳምንት በፊት ግብፅን ሲጎበኝ፣ ኢትዮጵያ በዓባይ ወንዝ መጠቀምንና የህዳሴው ግድብ በግብፅ ላይ ጉዳት እንደማያደርስ መግለጹ ይታወሳል፡፡ ፕሬዚዳንቱም አገራቸው ግብፅ የኢትዮጵያን ከድህነት መላቀቅና መልማት እንደምትፈልግ ገልጸው፣ ግብፅ በውኃ እጥረት እንዳትጎዳ ጥንቃቄ እንዲደረግ ጠይቀዋል፡፡ በተጨማሪም የኢትዮጵያን ግድብ መገንባት እንደማይቃወሙም መናገራቸው አይዘነጋም፡፡

የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ቡድኑ መሪ አፈ ጉባዔ አባዱላ ገመዳ የግብፅ ፕሬዚዳንት ኢትዮጵያን እንዲጐበኙና በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ለኢትዮጵያ ሕዝብ ንግግር እንዲያደርጉ በድጋሚ ጋብዘዋቸዋል፡፡ ፕሬዚዳንት አልሲሲ ኢትዮጵያን እንዲጐበኙ ጥሪ የቀረበላቸው በጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ አማካይነት ባለፈው መስከረም ወር መሆኑ ይታወሳል፡፡

ፕሬዚዳንቱ በቃለ ምልልሳቸው፣ ‹‹ኢትዮጵያ የግብፅን የውኃ ድርሻ እንደማትጐዳ በቃል የሰጠችውን ዋስትና በሰነድ እንድታረጋግጥ እንፈልጋለን፤›› ቢሉም፣ ኢትዮጵያ ግን የግብፅ የውኃ ድርሻን በተመለከተ የሰጠችው የሰነድ ዋስትና አለመኖሩን ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡

የዓባይ ተፋሰስ አገሮች በኡጋንዳ የተፈራረሙትና ኢትዮጵያና ሩዋንዳ በፓርላማቸው ያፀደቁት የዓባይ ተፋሰስ የትብብር ማዕቀፍ ስምምነት (CFA)፣ የተፋሰሱ አገሮች ውኃውን በሚጠቀሙበት ጊዜ በሌላው የተፋሰስ አገር ላይ ጉልህ ጉዳት ማድረስ የሌለባቸው መሆኑንና ኢትዮጵያ የምትከተለውም ይህንኑ መሆኑን ባለሙያዎቹ ጠቁመዋል፡፡

የግብፅ ፕሬዚዳንት በሰጡት ቃለ ምልልስ ላይ የሩሲያው ፕሬዚዳንትና የጃፓኑ ጠቅላይ ሚኒስትር በዚሁ በጃንዋሪ ወር ግብፅን የሚጐበኙ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ ፕሬዚዳንት አልሲሲ መንግሥታቸው ከኳታር ጋር ዕርቅ ማውረዱንና ለዚህም የሳዑዲ ዓረቢያ መንግሥት የተጫወተውን ሚና አድንቀዋል፡፡

Source:: Ethiopian Reporter


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>