አንድነት በጥቂት ቀናት ውስጥ የጠራው ጠቅላላ ጉባኤ በስክት ተጠናቋል፤ የፓርቲው ተ/ም/ፕሬዝዳንት አቶ ተክሌ በቀለ የጉባኤውን የመዝጊያ ንግግር በማድረግ ላይ ናቸው፡፡ አቶ ተክሌ በንግግራቸው አንድነት በብሔርም ሆነ በህብረብሔር ፓርቲዎች ጋር አብሮ ለመስራት መዘጋጀቱን እንዲሁም ከአንድነት ጋር ተመሳሳይ ፕሮግራም ላላቸው ፓርቲዎች ሁሉ የውህደት ጥያቄ አቅርበዋል፡፡ አቶ ተክሌ አክለውም አንድነት የ2007 ምርጫን በአሸናፊነት ለመወጣት እየሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡
አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ከትላንት ጀምሮ እያካሄደ ባለው ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ስልጠና እየተሰጠ ነው፤ በዛሬው መርሀ ግብር በሀገሪቱ ነባራዊ ሁናቴዎች(የአርሶ አደሩ ፤የከተማው ነዋሪ፤የባለሐብቱ ሁናቴ) በዳግማዊ ተሰማ የተማሪውና የምሁሩ ሁናቴ በጋዜጠኛ አናንያ ሶሪ የአንድነት የምርጫ ስትራቴጂ ግብ በፓርቲው ፕሬዝዳንት አቶ በላይ ፈቃዱ ቀርቦአል፡፡ በመቀጠልም የስልጠናው ተሳታፊዎች ጥያቄና አስተያየት በመስጠት የጠዋቱ ስልጠና ተጠናቆ፣ የአንድነት ፓርቲ ም/ፕሬዝዳንት የተከበሩ አቶ ግርማ ሰይፉ በምርጫ ስትራቴጂ ዙሪያ ስልጠና ሰጥተዋል፡፡ በመቀጠልም የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የህግና ሰብአዊ መብት ምክትል ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ገበየሁ ይርዳው የአባላት መብትና ግዴታ ከፓርቲው ደንብና ከፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ አዋጅ አንጻር ስልጠና ሰጥተዋል ነው፡፡ በአሁኑ ሰዓት መድረኩ ለውይይት ክፍት ሆኖ ውይይት እየተደረገ ይገኛል፡፡
የጉባኤውን መዝጊያ በማስመልከት የተለያዩ የሙዚቂ ዝግጅቶች እየቀረቡ ነው፡፡
በአሁኑ ሰዓት ጉባኤው ለጋዜጠኞችና ለክብር እንግዶች ክፍት ሆኗል፡፡ አንድነት ፓርቲ ለዞንና ለወረዳ አመራሮች ያዘጋጀው ስልጠና በስኬት ተጠናቋል፡፡ በአሁኑ ሰዓት ጉባኤው ለጋዜጠኞችና ለክብር እንግዶች ክፍት ሆኗል፡፡