በአፋር ህዝብና በዒሳ ብሄረሰብ መሀከል ለብዙ ዘመናት የቆየው የብዙ ሰዎች ህይዎት ያለፈበት የድምበር ግጭት በብዙ መንግስታት ዘላቂ መፍትሄ ሳያገኝ ለዚህ አሰከፊ ደረጃ ላይ ደርሷል። ይሁንና የአፋር ህዝብና ሶማሊኛ ተናጋሪው የዒሳ ብሄረሰብ አሁንም በኢህአዴግ መንግስት ዘላቂ መፍትሄ አላገኘም። ባለፉት ሁለት አስር አመታት የደቡብ አፋር ነዋሪዎችና ዒሳዎች መሃከል በተከሰተው ደም አፋሳሽ በሆነው ግጭት ከሁለቱም ብሄሮች ብዙ ሰዎች ሞተዋል። ከሶማሌ ክልል ከሺኒሌ ዞን በኮንትሮባንድ ስራ ወደ አፋር ክልል እየተጠጉ እዛ አካባቢ ሲኖሩ የነበሩ የአፋር ነዋሪዎችን በማሸበር የአፋር መሬትን በሃይል መያዛቸውን የሚነገርላቸው ዒሳዎች ከዚህም ባለፈ የብዙ አፋሮችን ግመሎች፣ ከብቶችና ንብረቶች ዘርፈዋል።
ዒሳዎች ቅዱስ ቁርአንን በእጁ ይዞ እኔ ነጹህ ሰው ነኝ አትግደሉኝ ብሎ የለመናቸውን ያልታጠቁ ሙኢምንን ጨምሮ ዕድሜና ፆታ ሳይለዩ የብዙ አፋሮች ህይወት ለሞት ዳረገዋል። ይህ ሁሉ ሲደርስብን ሰላም የሚያስከብርልን መንግሰት በማጣታችን በጣም አዝነናል፣ የኢህአዴግ መንግስትም ሆነ የአፋር ክልል መንግስት እንደ አንድ መንግስት ህብረተሰቦችን በማወያየት ዘላቂ መፍትሄ መስጠት ሲጠበቅበት ግን አልቻለም። አሁን ይባስ ብሎ ለዒሳዎች በአፋር ክልል ውስጥ ልዩ ቀበሌዎች መስጠቱን ሰምተናል። ይህ መላው አፋርን ከጫፍ እስከ ጫፍ ያስቆጣው ወሰን አጥበቀን እንቃወምለን ። ወያነ ለዚህ ወሳኔ ያስፈረማቸውን የአፋር ክልል መሪዎች የአፋር ህዝብን አይወክሉም አናውቃቸውም። የወያኔ መንግስት እስካሁን ድረስ በአፋር ህዝብ ላይ ያየውን ትዕግስት እንደ ፍራቻ ወይም አለማወቅ ወሰዶታል።
በትናንትናው ዕለት ታሕሳስ 2/2007 በአዋሽ የተደረገው ስምምነት የአፋር ሕዝብ መሬቱንም ሆነ አገሩን ማጣቱ እና ለኢሳ የተሰጠ መሆኑን በኢህአዴግ የተረጋገጠ ሰነድ ላይ የአፋርን ሕዝብ የማይወክሉ የአብዴፓ ባለስልጣኖች የፈረሙበት የትልቅ ታሪክ አዋራጆች ቀን ብለን ሰይመነዋል። የአፋር ክልል ማንኛውም ኢትዮጲያዊ በሰላም የሚኖረበት ክልል መሆኑን የሚታወቅ ሲሆን፣ ከወራት በፊት ዒሳዎች በአፋር ክልል በሰላም እንዲኖሩ ተፈቅዶላቸው እኛ የአፋር መሬት ወደ ሶማሌ ክልል ካልተካለልን አሸባሪ እንሆናለን ብለው እየፎከሩ ለነበሩ ዒሳዎች ዛሬ ወያነ እነርሱን ፈርቶ የአፋር መሬት ከሰጣቸው እኛም ሰላም ባጣንበት አገራችን ወያነም ሆነ ነፍሰ ገዳይ የሆኑት የአልሸባብ ተላላኪ ዒሳዎች በአናታችን በሰላም እንዲኖሩ አንፈቅድም!!!!
መብታችን ማስከበር ሽብር ከሆነ እንሆናለን!!
የሚያስተዳድረን ፍትሃዊ መንግስት ከሌለ ሁላችንም ለሞት እንዘጋጃለን!!
ፍትህ ለተጨቆኑ የኢትዮጵያ ህዝቦች!!