ከሊሊ ሞገስ
ሴቶች በየዕለቱ በህይወታቸው ውስጥ ከወንዶች ጋር ያላቸው ግንኙነት በተለያየ መልኩ ይገለፃል፡፡ ከዚህም አልፎ ከወንዶች ጋር ያላቸው ግንኙነት መልካም እንዲሆን የእነሱንም ፍላጎት የሚመችና የሚያረካቸው እንዲሆንላቸው ይፈልጋሉ፡፡ እስከ ትዳር የሚዘልቁም ሆነ ከትዳር በፊት ከትዳርም ውጪ ቢሆን የራሳቸውን ሰብዕና ጥሩ በሆነ መልኩ እየገነቡ የሚያሳዩዋቸው ባህሪያትንና ፍላጎቶቻቸውን ወንዶች እንዲረዱላቸው ይፈልጋሉ፡፡ በተለይም ሴቶች የውስጣቸውን ፍላጎት የሚረዳላቸው ብቻ ሳይሆን ተቀራርቦ አብሯቸው ካለና ፍላጎታቸውን ከተረዳላቸው ወንድ ጋር ረዥም ጊዜ መቆየትንና ደስ የሚል ህይወትን መምራት ይፈልጋሉ፡፡
ከዚህም በላይ የእነሱን ፍላጎት በጠበቀ መልኩ የሚንከባከባቸውንና የሚጠነቀቅላቸውን ወንድ አጥብቀው ይፈልጋሉ፡፡ ደስ ብሏቸው ከጥሩ ወንድ ጋር መልካም ህይወት ከጀመሩ በኋላ ፈፅሞ መራቅን አይመርጡም፡፡ አብሯቸው ጥሩ ግንኙነት ጀምሮ ወንዱ ሲርቃቸው ውስጣቸው በጣም ይጎዳል፡፡ ጥሩ ነው ብለው የሚያስቡትን መልካም ግንኙነት እየጠሉትም ከወንዶች ጋር እንደገና ጥሩ ግንኙነት ለመመስረት ይቸገራሉ ጥርጣሬ ውስጥም እንዲገቡ ያደርጋቸዋል፡፡
የጥናቱ አካል ከሆኑት መካከል ታዋቂዋ የጎልፍ ተጨዋች ሀና ራውሰን ስትናገር ‹‹በጣም የሚስብና ቆንጆ ነው ብዬ ካሰብኩት ወንድ ጋር ጥሩ የፍቅር ግንኙነት ጀምሬ ነበር፡፡ የሚያሳዝነው ከእኔ ጋር እየቆየ ሲመጣ እኔን የሚንከባከበኝ በመጥፎ ሁኔታ እየሆነ በመምጣቱ ልንለያይ ችለናል›› ብላለች፡፡ ንግግሯን ስትቀጥልም ‹‹በመለያየታችን ውስጤ ቢጎዳም ለሚቀጥለው ህይወቴ ብዙ ነገር እንድማርበትና ፍላጎቴን የሚጠብቅልኝን የተሻለ ወንድ ለማግኘት ይረዳኛል›› ስትል ነበር አስተያየቷን የገለፀችው፡፡
ራውሰን ቀጥላ ስትናገር ‹‹ወንዶች በጣም እንደማምርና ውብ እንደሆንኩኝ ይነግሩኛል፡፡ ለምን የምጫወተው የጎልፍ ጨዋታዬን እያዩም አያበረታቱኝም ትላለች፡፡ ውበቴን ቢያደንቁ የበለጠ ለውበቴ እንድጨነቅና እንዳምር ያደርገኛል እንጂ የጎልፍ ጨዋታ ውጤቴ ላይ የተሻለ ለውጥ እንዳመጣ አያደርገኝም፡፡ እኔ ሁሉን ፍላጎቴን እያደነቀና እያበረታታ ውስጤን የሚጠብቅልንን ወንድ ነው የምፈልገው፡፡ እነዚህን ፍላጎቶቼን አውቆ የበለጠ የሚጠብቅልን ሳገኝ ውጫዊው ሆነ ውስጣዊ ውበቴ እንዲጎላና የአካላዊም ሆነ የጭንቅላት ዝግጁነቴ ሙሉ ሆኖ ኮንፊደንስ ወይም በራስ መተማመን እንዲኖረኝ የማድረግ ኃይል ይኖረዋል›› ብላለች፡፡ አንፃራዊ በሆነ መልኩ ስለሌሎቹ ስትጠቅስም፡፡
በዚህ ጊዜና ሁኔታ ውስጥ ሁላችንም ሴቶች የበለጠ የምንስብ ውብ መሆንም እንችላለን፡፡ ወንዶች ይህን ከተረዱልንም የውስጣችንም ስሜትና ፍላጎት በቀላሉ ፈንድቶ እንዲወጣና እነሱንም የበለጠ በሚፈልጉት መልኩ ማርካት እንችላለን ትላለች የጎልፍ ተጨዋቿና ሞዴሊስቷ ራውሰን፡፡ ከዚህ በመነሳት የራሷን ልምድ በማካፈሏ በብዙ ሴቶች ላይ ያለውን ነገር ለማንፀባረቅ ችላለች፡፡ ራውሰን ስታክል ‹‹ወንዶች ልክ የምጫወትበትን የጎልፍ መምቻና እንቅስቃሴውን ይመስሉኛል፡፡ የጎልፍ መምቺያ ሁልጊዜ በሴቶችና በወንዶች መካክል መነሻ የሚሆነውን ፍላጎት የሚወክል ሲሆን ከመታውኝና ጥሩ ነጥብ ማስቆጠር የምችልበትን እንቅስቃሴ ሳደርግ ወንዶች የእኔን ፍላጎት ተረድተው አብረን እየተጓዙ ደስ የሚል ህይወት ውስጥ የምገባበት ሁኔታን ወክዬ አየዋለሁ›› ስትል ገልፃለች፡፡ በአጠቃላይ የሴቶችን ፍላጎት በመረዳትና ይህፍላጎታቸው የበለጠ ፈንድቶ እንዲወጣ የማድረግ ስራ የወንዶች ይሆናል እንደ ጥናቱ ገለፃ፡፡ ጥናቱ ወደ መጨረሻ የመደምደሚያ ሃሳብ ላይ ሲመጣም የሴቶችን ፍላጎት በመረዳት ወንዶች እንዴት ለበለጠ ጥሩ ግንኙነት እነሱን ማነሳሳት እንደሚችሉና የራሳቸው ሊያደርጓቸው እንደሚችሉ ጠቁመዋል፡፡
እነዚህ የሴቶች ፍላጎት የበለጠ እንዲፈነዳና የራሳቸው እንዲሆኑ ከወንዶች የሚጠበቁና ሴቶቹን ወደ ራሳቸው ለማምጣትና ለመምራት የሚያስችሉ ጥለቅ የሆኑ ተግባሮች የሚከተሉት ናቸው፡፡
1. ፍላጎቷን እስክታገኘው ደጋግመህ ጠይቅ
ብዙውን ጊዜ ሴቶችንም ሆነ ወንዶችን ከአንድ ጊዜ በላይ ወደሆነ የፍቅር ግንኙነት ውስጥ እንዲገቡ የሚያደርጋቸው ቶሎ የውስጣቸውን ፍላጎት ለማግኘት ስለሚቸገሩ ነው፡፡ በተለይም የሴቶች የውስጥ ፍላጎት ፈንድቶ እንዲወጣ ለማድረግ አስቸጋሪ ስሆነ ይህንን ለማድረግ ወንዶች በተለያየ አቅጣጫ ሴቶችን ደጋግመው መጠየቅ ይገባቸዋል፡፡ በጥያቄዎችህ ውስጥ መላመድህን እሷ እየወደደችው ስትመጣ ፍላጎቷን አውጥታ ትገልፅልሃለች፡፡ ሴቶች በብዙ ነገር ግንኙነት ውስጥ ስለሚፈሩና ስለሚጠነቀቁ ይህንን ተረዳው፡፡ ነካክቶ መተው ለአንተም ለእሷም ጥሩ አይደለም፡፡ ስለዚህም ጥንቃቄ ባለው መልኩ ሳታሰለቻት ደጋግመህ ለመጠየቅ ሞክር፡፡
2. ሴቶችን ወደተሻለ ደረጃ ለማምጣት ሞክር
ብዙ ሴቶች መልካምና ቀና የሚያስብላቸውን ወንድ ይፈልጋሉ፡፡ ነገር ግን እጅግ ሲበዛ ጀንትል ሆኖ የሚረጋጋ ወንድ አይመቻቸውም፡፡ ከዚህ ይልቅ ሴቶች የውስጣቸውን እየተረዳቸው በጣም የሚያነቃቃቸውን እንዲሁም የሚፈልጉትን ቶሎ ተረድቶ እርካታን የሚሰጣቸውን ወንድ ይፈልጋሉ፡፡ ለዚህም ወንዱ የተሻለ ደረጃ ላይ ሆኖ እነሱን የበለጠ የሚቆሰቁሳቸውና ትልቅ የንቃት ኃይል ወደ ውስጣቸው የሚጨምርላቸው እንዲሆን ይፈልጋል፡፡ ለዚህም የተሻለ ሆኖ ተገኘና የእነሱንም ፍላጎት አፈንድተህ ለማውጣትና የተሻለ ቦታ ላይ ለማምጣት ሞክር፡፡
3. ግንኙነትህን አጠንክረው
ወደ ፍቅር የሚሄደው ግንኙነትህ ያማረ እንዲሆን አስቀድመህ የእሷን ፍላጎት አፈንድተህ ለማውጣት ደጋግመህ መገናኘትን እንደ ጥሩ ዘዴ ተጠቀምበት፡፡ በዚህ ሂደት ውስጥ እሷ ለአንተ በጣም እንደምታስፈልግህ እየነገርካት እንደሆነ እሷም ፍላጎቷን እንድታወጣውና እየገፋፋሃትና እያሳወቃት እንደሆነ ትረዳለች፡፡
4. ከሴቶች ጋር ማንኛውም ነገር ለማድረግ ባቀድከው መንገድ ተጓዝ፡፡
ለሴቶች ልታደርግላቸው አንድ ነገር ስታስብ ፕሮግራምህን አትሰርዝባቸው፡፡ ሴቶች በተለይም ወደ ጥሩ ግንኙነት እየመጡ ከሄዱ በኋላ የቀጠሮ ሰዓትም ሆነ ሌሎች ነገሮችን ካሳወቃቸው በኋላ የምትሰርዝ ከሆነ ፍፁም ምቾት አይሰጣቸውም፡፡ ሊበሳጩም ይችላሉ፡፡ አንተም ፍላጎቷን ለማግኘት የነበረክ ሂደት ላይ ውሃ እንደመከለስ ስለሚቆጠር ጥንቃቄ አድርግ፡፡ ፍላጎቷን እየመራህ ለመሄድ ፕሮግራሞችህ ወጥና የማይለወጡ ይሁኑ፡፡
5. በእሷ ላይ ጥሩ አቋም ወይም አስተያየት ይኑርህ
አንተ እንደ ወንድነትህ ሌላ እሷ የምትጠረጥረውን ነገር ባታደርገውም እንኳን ንገራት፡፡ ታማኝ መሆንህ ለእሷ ፍላጎት ጎልቶ መታየት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያደርግልሃል፡፡ ነገር ግን ጥሩነትህን ጥንቃቄ በተሞላበት መልኩ እየገለፅክ በእሷ ላይ ጥሩ የሆነ አቋም እንዳለህ ንገራት፡፡
6. ጥንቃቄ በተሞላበት መልኩ አስፈላጊ ንክኪዎችን ተጠቀም
ልክ እንደምታወሩትና እንደምትተያዩት ሁሉ ጥሩ የሆኑ የእጅ መነካካትና መጨባበጥ ብሎም በእጅህ ትከሻዋን እቅፍ እያደረክ ጥሩ ጊዜ ማሳለፍን እንደ ትልቅ የፍላጎቷ ማውጫ መንገድ ተጠቀምበት፡፡ ከዚህም በላይ ጥንቃቄ የተሞላባቸው አስፈላጊ ንክኪዎች ሴቶችን በፍቅር የማሞቅ ከፍተኛ ኃይል አለው፡፡
በአጠቃላይ እነዚህን መሰረታዊ የጥናቱ የጨመረሻ ሃሳቦችን በመጠቀም ወንዶች የሴቶችን ፍላጎት በቀላሉ በመረዳትና ፈንድቶ እንዲወጣ በማድረግ ወደራሳቸው በማምጣት የሚፈልጓትንም በቀላሉ የራሳቸው በማድረግ ጥሩ ግንኙነት እንዲመሰረቱ ያደርጋቸዋል፡፡ አንተም ወንዱ ፍላጎቷን ጠብቅ ከዛም የበለጠ ራሷ አፈንድታው ትነግርሃለች፡፡ ያኔም የአንተ ትሆናለች፡፡ አንተም የእሷ ማለት ነው፡፡