ጦርነትትን ሰርተን ድል እናመጣለን የሚለው ስልጣን ላይ ያላው አካል አይዶሎጂ እንደሆነ ይታወቃል። ቦንብ አፈንድቶ ንፁሀን ዜጎችን ፈጅቶ የስልጣን እድሜን ለማራዘም በብዙ አኳያ ሲጠቀሙበት እንደነበረም የሚታዋቅ ነው። ያገራቸውን ሁኔታ በቅርበት የሚከታታለ ዜጎች መንግስት ያደርጋል ብሎ ለማመን ቢከብድም ለመናገር የማይቻልበት ሁኔታ ውስጥ ባይሆኑም ይህን ማወቅ ግን ነበረባቸው። ቦንብ እያፈነዱ ብዙ ጊዜ አስርና አምስት ንፁሀን ዜጎች ተቀጥፈዋል። ታዲያ የከበደን የትኛው ለማመን የሚከብድ ሆኖ ነው?። ጢቢ ጢቢ እንደሚጫወቱበት ህዝብ በእምነቱ ወይ በዘሩ ጎራ ለይቶ ፀብ ውስጥ ቢገባስ ኖሮ?። አሪዬሳዊ በሆነው በዚህ ተግባራቸው አይደለም እሳት እዚህና እዚህ ብልጭ ድርግም ሲል እያየን ያለነው?። እንቅልፍ የሚነሳን እንድ ቀን ስንነሳ የሰደድ እሳት እንደሚሆን ማወቃችን አይደለም ወይ። ቦንበኛነቱን ለወደፊቱም የተበላ ነው ብለው ይተውታል ማለት ባልችልም እየተረቀቁበት ግን ሄደዋል። አሁን አሁን ህግ እያመረቱ ቦንብ እያፈነዱ ሲጠቀሙበት ለነበረ ጉዳይ እየተጠቀሙበት ነው?። ህጎቹ የተመረቱትም አንድና አንድ ለዚሁ አላማ ነው። ይህን ስለምናውቅ መሰሎኝ አምርረን የምንቃወመው።
ከዚህ መረዳት ተነስቼ አቶ ግርማ ሰይፉ በማክበር ተሳስተዋል። ስህተት የሆኑት በዚህ ህግ ሽብርተኛ ተብለው የታሰሩትን ዜጎችን ሁሉ የታሰሩበትን ጉዳይ ሁሉ ባያውቁም ማወቅም ባይጠበቅቦትም መንግስት ነኝ የሚለውንና እየታገሉት ያሉትን አካል ማወቅ ስለነበረቦት ነው። ቁጣ ያስነሳው የሚመስለኝ በዚህ ደረጃ የሚያውቁት ብዙዎች መሆናቸው ነው። እርሶም ያውቃሉ የሚል ግምት ስለነበረ ነው። ባጭሩ ንግግሮት ከኢትዬጵያ ውጪ የትም አገር ላይ አንድ ሰው ተናግሮት ቢሆን ሚዛናዊ ያሰኝው ነበር። በኛ ሁኔታ ግን ሀናን ማን ሺሻ ቤት ሂጂ አላት ብሎ እንደመውቀስ መሰለ። ለመጨመር አላማው ህዘብን ማሸበር ሲሆን እንጂ ቦንብ ማፈንዳት ሁሉ አሸባሪነት ነው ያለው ማነው። እኔም እንኳ ብችል አናታቸው ላይ እበትነው ነበር።
ያም ሆኖ መካበድ አለበት ወይ?። የሚካባድ ነገር የለውም። አቶ ግርማ ቆራጥ ታጋይ ነው ወይ? አንበሳ ታጋይ ነው። ወያኔ ነው ወይ?። ወያኔዎች ናቸው የሚሉት። ከአንድነት ፓርቲ ጋር ይያዛል ወይ?። ዲሞክራሲያዊ ድርጅት ምን እንደሆነ ካላወቅን አዎ። አንድነት ምርጫ ለመሳተፍ ከመወሰኑ ጋር ይገናኛል ወይ? በየትም በኩል።
ሌላው የይቅርታ ጉዳይ እኛ ፖለቲካ ውስጥ በተነሳ ቁጥር ያመኛል። መጀመርያ ይቅርታ ማለት አለበት። ወይ አለባቸው። በሗላ ሂሳብ እናወራርዳለን።ነብሴ ነው። ይቅርታ በለ ወይ በይ ሞቼ ነው። ብቻ ጠያቂውም እንቢ ባዩም ብዛቱ። ሁላችንም ሁሌም ማስታወስ የሚገባን ሰቃዬቹ አይደሉም እየሱስ ክርስቶስ ነው ፈቅዶ ይቅርታ ያለው።
ከማቆሜ በፊት ለዚህ ሁሉ ተጠያቂ የማደርገው አቶ ግርማ ሰይፉን አይደለም ግርማ ካሳን ነው። በተደጋጋሚ አይቼሀለው ለኳሽም ገላጋይም መስለህ ትሰራለህ። በቅርብ ባወጣህው ፅሁፍ አገዛዙ ግንቦት ሰባት እየለ ግፍ የሚፈፅማቸውን ዜጎች ታግሎ ላይታግል ደባ በሚመስል ጥፋቱ የግንቦት ሰባትና በእርግጥም ከታሰሩት ውስጥ አባል የነበሩ እንዳለ ፅፈሀል። ይህን ሀሳብ ወደህዝብ የገፋህበትን መረጃ አቅርብ። ማቅረብ ካልቻልክ መፃፍ አቁም። ለመከልከል ሳይሆን ተንኮልህ ይቆማል። ቲካ ቲካውንና መቀጠሉን ስለምትወደው ለመዝጋት የአርዬሶቹን ወይ የአርቲስት ደበበ እሸቱን ግፍ ያየንበትን ቪዲዬ አይነት መረጃ ግን ተቀባይነት የለውም።
ለማንኛውም ለመንበዛበዝ ጊዜ የለንም ወደፊት።
ዳዊት ዳባ