Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

የሰላማዊ ሰልፍና ስብሰባ ማሳወቂያ ክፍል በፖስታ የተላከውን የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር ደብዳቤ አልቀበልም አለ

$
0
0

(ነገረ ኢትዮጵያ) የአዲስ አበባ አስተዳደር የሰላማዊ ሰልፍና ስብሰባ ማሳወቂያ ክፍል 9ኙ ፓርቲዎች ህዳር 21 ለሚያደርጉት የአደባባይ ህዝባዊ ስብሰባ በፖስታ ቤት የተላከለትን ደብዳቤ አልቀበልም ማለቱን የስብሰባው አስተባባሪ የሆነው የመኢዴፓ ፀሀፊ አቶ ዘመኑ ሞላ ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡
postal service ethiopia
የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር ህዳር 21/2007 ዓ.ም ለሚያደርጉትና መኢዴፓ ለሚያስተባብረው ስብሰባ ረቡዕ ህዳር 10 የመኢዴፓ አመራሮች ደብዳቤውን ለማስገባት ሄደው የነበር ቢሆንም አቶ ማርቆስ ብዙነህ እና እሳቸውን ተክተው ሲሰሩ የነበሩት አቶ ፈለቀ ታመዋል በሚል የከንቲባ ጉዳይ የካቢኔዎች ኃላፊ አቶ አሰግድ ጌታቸው ማሳወቂያ ደብዳቤውን አንቀበልም ማለታቸው ይታወቃል፡፡

በተመሳሳይ ህዳር 12 ወደ ሰላማዊ ሰልፍና ስብሰባ ማሳወቂያ ክፍሉ ያቀኑት የትብብሩ አመራሮች ደብዳቤውን የሚቀበላቸው ሲያጡ ጠረጴዛ ላይ ጥለውት የመጡ ሲሆን በፖስታ ቤት በሪኮመንዴ eg156846735et እንደላኩ የትብብሩን ፀኃፊ አቶ ግርማ በቀለን ጠቅሰን መዘገባችን ይታወሳል፡፡

ለአዲስ አበባ አስተዳደር የሰላማዊ ሰልፍና ስብሰባ ማሳወቂያ ክፍል በፖስታ የተላከውን ደብዳቤ ቢደርስም አመራሮቹና ሰራተኞቹ ደብዳቤውን ለመቀበል ፈቃደኛ እንዳልሆኑ ፖስታ ቤት ድረስ በመሄድ እንዳረጋገጡ አቶ ዘመኑ ሞላ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ የሰላማዊ ሰልፍና ስብሰባ ማሳወቂያ ክፍል ሰራተኞችና አመራሮች ፖስተኛው ደብዳቤው የሚሰጥበትን ቢሮ ሲጠይቅ ለማሳየት ፈቃደና እንዳልሆኑና በስተመጨረሻም ‹‹ተቀባይ የለውም ብለህ መለስ፡፡›› እንደተባሉት አቶ ዘመኑ ሞላ ገልጸዋል፡፡


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>