Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

ወሲብ እና ሁለንተናዊ ጤንነት

$
0
0

ሁላችንም ወሲብ አስደሳች እንደሆነ እናውቃለን፤ ይሁን እንጂ ለጤና ጠቃሚ ነው ወይ የሚል ጥያቄ አንስተን እናውቅ ይሆናል፡፡ መልሱ እጅግ በጣም የሚል ነው፡፡ ነዋሪነታቸውን ኒውዮርክ ከተማ ያደረጉ እና “She Comes First.” በሚል መጽሐፍቸው የሚታወቁት የወሲብና ወሲብ ነክ ጉዳዮች አማካሪ አየር ኬርነር #የወሲብ ህይወታችን ጤና የአጠቃላይ ጤና ነፀብራቅ ነው፡፡$ይላሉ፡፡

sex11በወሲብ ዙሪያ ጥልቅ ጥናትና ምርምር ያደረጉ ባለሙያዎች ወሲብ ለራሳችን የሚኖረንን አመለካከት (self-esteem) ከማሻሻል ጀምሮ ለውስን በሽታዎች የሚኖረንን ተጋላጭነት እስከ መቀነስ ድረስ ብዙ ጥቅም እንደሚሰጥ ያስረዳሉ፡፡ በአንፃሩ፣ እምብዛም ወሲብ የማይፈፅሙ ከሆነ ችግር ሊኖር ይችላል፡፡
እነዚህን ችግሮች ለይቶ መፍታት አስፈላጊ ነው ይላሉ ኬርነር፡፡ ምክንያቱም የወሲብ ህይወታችን በብዙ መልኩ ከልዩ ልዩ የሕይወት ክፍሎቻችን ጋር ቀጥተኛ ቁርኝት አለው፡፡ ለአብነት ያህል፣ የወሲብ ፍላጎትዎና አፋፃፀምዎ አናሳ ከሆነ ምንአልባት የድብርት ተጋላጭ ሊሆኑ ይችላሉ፣ ክብደትዎ ከልክ በላይ ሊሆን ይችላል፣ የተመጣጠነ ምግብ አይበሉ ይሆናል፣ ውጥረት ውስጥ ይገኙ ይሆና ወ.ዘ.ተ፡፡

ወሲብ ተከታዮቹን በመድሀኒት መልክ ሊገኙ የማይችሉ ጤና ነክ ጥቅሞች ይሰጣል፡-

የልብ ጤንነትዎን ሊያሻሽል ይችላል

ጥናቶች እንደሚጠቁሙት የብልት መጠንከር ከልብ መጠንከር ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት አለው፡፡ በ2008 ዓ.ም የአሜሪካን የልብ ህክምና ጆርናል ላይ ይፋ የተደረገ ጥናት እንደሚያብራራው የብልት መቆም እና መጠንከር ችግር (erectile dysfunction (ED)) ከልብ ጥንካሬ ማጣት ጋር ግንኙነት አለው፡፡

ተመራማሪዎች 2300 ወንዶች ላይ ባደረጉት ምርምር መሠረት የብልት መቆም እና መጠንከር ችግር ያለባቸው ወንዶች ለልብ ህመም ያላቸው ተጋላጭነት ችግሩ ከሌለባው ይልቅ በ 58% ከፍ ነው፡፡

ለፕሮስቴትካንሰርየሚኖራአችሁተጋላጭነትሊቀንስይችላል

በ2004 ዓ.ም የአሜሪካ ህክምና ባለሙያዎች ማህበር ጆርናል ላይ 24000 ወንዶችን አሳትፎ ይፋ የተደረገ ጥናት እንዲሚጠቁመው በአንድ ወር ውስጥ 21 ጊዜ ወሲብ የሚያደርጉ ሰዎች በወር ውስጥ ከ4 – 7 ጊዜ ያህል ወሲብ ከሚያደርጉ ሰዎች ይልቅ ኋላ ላይ ለፕሮስቴት ካንሰር የሚኖራቸው ተጋላጭነት በእጅጉ ይቀንሳል፡፡

ለሥራይጠቅማል

ሔለን ፌሸር የሚባሉ ኦንትሮለፖሎጂት ወሲብ የፈጠራ አቅምን፣ ችግር የመፍታት ችሎታን እና የመግባባት ክህሎትን እንደሚያሻሽል ይገልፃሉ፡፡ ይህንን ሁሉ ነገር ሊያሻሽል የሚችልበት አብይ ምክንያት ወሲብ ስንፈፅም አንጎላችን ዶፓሚን እና ኦክሲቶሲን አካ የሚሰኙ የደስታ ስሜትን የሚያጎናፅፉ ኬሜካሎችን በብዛት አምሮቶ ስለሚያሰራጭ ነው፡፡

የወጣትነት መልክዎና ቁመናዎ ተጠብቆ እንዲቆይ ይረዳል

ስኮትላንድ ውስጥ 3500 አሜሪካውያንን እና አውሮፓዊያንን ያሳተፈ አንድ ጥናት ተካሂዶ ነበር፡፡ ጥናቱ ለአስር አመት ያህል ቢያንስ ቢያንስ ከ7 – 12 አመት ከእድሜቸው ይልቅ ወጣት የሚመስሉ ሰዎችን አፈላልጎ ማግኘትና የጋራ ጠባያቸውን ማጥናት ነበር፡፡ ታዲያ እነዚህ ሰዎች ታስሰው ከተገኙ በኋላ ጥናቱ የእነዚህን ሰዎች የጋራ መለያ ጠባይ ምን እንደሆነ ለመረዳት እና ለመተንተን ሙከራ አድርጓል፡፡ በግንባር ቀደምነት እነዚህን ወንዶች የሚያመሳስላቸው ነገር መደበኛ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ መቻላቸው ነው፡፡

ሁለተኛው የጋራ መለያ ጠባያቸው በመደበኛነት ወሲብ መፈፀም መቻል ነበር፡፡ ከሞላ ጎደል ሁሉም ከ 2 – 3 ጊዜ በሳምንት ከፍቅር ወይም ትዳር አጋራቸው ጋር ወሲብ ይፈፅማሉ፡፡

ውጥረትን ያረግባል

ሴቶች የእርካታ ጣሪያ ላይ ከመድረሳቸው ጥቂት ቀደም ብሎ በከፊል ንቁ በከፊል ንቁ ያልሆነ ሁኔታ ውስጥ ይገባሉ፡፡ በዚህ ወቅት ውጥረትን የመቀነስ እና የማርገብ ሚና የሚጫወተው የአንጎላቸው ክፍል ስራ ይጀምራል፡፡

አንጎልን ያነቃቃል

ዘወትር ወሲብ የመፈፀሚያ ተለምዷዊው መንገድ አስፈላጊ እንደሆነ ሁሉ አእምሮአችንን በወሲብ ሀሳብ ማነቃቃትም እንዲሁ አስፈላጊ ነው፡፡ ኬርነር የወሲብ ፍላጎት መነቃቃት የአካልና አእምሮ በጋራ መነቃቃት ነው ይላሉ፡፡ እኚህ ባለሙያ ብዙ ጊዜ አእምሮአችንን ማነቃቃት የሚችለው ሀሳብ ወሲብ ውስጥ ድርሻ ሊኖረው እንደሚገባ እንዘነጋለን ይላሉ፡፡

ኬርነር፣ ከዚህ በተጨማሪ ሁሉም የስሜት ህዋሳት ወሲብ ሲፈፀም ቦታ እንዲኖራቸው ማድረግ አስፈላጊ ነው ይላሉ፤ እይታ፣ ድምፅ፣ ንክኪ፣ ጣዕም፣ እና ጠረን፡፡

ስለዚህ፣ ቢያንስ ቢያንስ በሳምንት አንድ ቀን ወሲብ መፈፀም ብቻ ሳይሆን በተቻለ መጠን ሁሉንም የስሜት ህዋሳት እና ሁኔታወች ያካተተ አይነት ወሲብ መፈፀምን ያበረታታሉ፤ ምቾት፣ አዳዲስ ነገሮችን መሞከር እና ሁሉንም የስሜት ህዋሳት ተሳታፊ ማድረግ፡፡

ወሲብን የሚደግፉ እና የሚያበረታቱ ጥናቶች ቁጥር ስፍር የላቸውም፡፡ ስለዚህ የወሲብ አምሮታችሁ እና አድራጎታችሁ አናሳ ከሆነ ከዚህ ልምምድ ልትወጡ የምትችሉበትን ነገር ለማድረግ ሞክሩ፡፡

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የወሲብ ፍላጎታችሁ ማሽቆልቆል ከጀመረ ይህ ለምን ሊሆን እንደቻለ ለመረዳት ሞክሩ፤ የሳይኮሎጂ እና የህክምና ባለሙያ እንደየችግሩ ሁኔታ እገዛ ሊያደርጉላችሁ ይችላሉ፡፡ አለበለዚያ የተመጣጠነ ምግብ በመመገብ፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በማድረግ፣ ለአካላችሁ እና አለባበሳችሁ ቦታ በመስጠት ቀላል የማይባል ለውጥ ማምጣት ትችላላችሁ፡፡ ኬርነር፣ ሰዎች ጤናማ ወሲብ ከፍቅር አልያም ትዳር አጋራቸው ጋር ማድረግ ሲችሉ ሕይወታቸው ይበልጥ ይደምቃል ይላሉ፡፡ ክብደታቸውን ለማስተካከልና ለመቆጣጠር ይበልጥ ተነሳሽነት ውስጣቸው ይፈጠራል፣ ራሳቸውን መንከባከብ ያዘወትራሉ፣ እንደተፈቀሩ ይሰማቸዋል፣ እርካታቸው ይጨምራል፣ ስራ ቦታ መነጫነጭም ሆነ መጋጨት ይቀንሳሉ፡፡ በጥቅሉ ወሲብ ለሁለንተናዊ ጤና መሻሻል በብዙ መልኩ አስተዋፅዖ ያበረክታል፡፡

ምንጭ፡ upwave.com

 


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>