Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

መተቸት መብት ነው- ግን መረጃ እየያዝን (መልስ ለአቶ ይድነቃቸው) –ግርማ ካሳ

$
0
0

አቶ ይድነቃቸው የሰማያዊ ፓርቲ ከፍተኛ አመራር ናቸው። አንድነት ፓርቲ ላይ ያነጣጠረ ሁለት ጽሁፎችን በቅርቡ ለቀዋል። እንደ አንድነት ደጋፊ አንድነት ላይ ትችት መቅረቡን አልቃወምም። ሆኖም ትንሽ የመረጃ ክፍተት ሳይኖርባቸው እንደማይቀር በመገመት እንደሚከተለው ምላሽ ስጥቻለሁ፡

ወንድም ይድነቃቸው፡

“እኔም ሆንክ ሌሎቻችን በሰጠነው ትችት እና አስተያየት አንድነት ፓርቲ ጉዳዩን ለማጥረት በዛሬው ዕለት “አንድነት የፀረ ሽብር አዋጁ ተቀብሎትም አያውቅም፤ አይቀበለውም!” በማለት ያዋጣው መግለጨ የሚበረታታ እና የሚደነቅ ነው፡፡” ብለ በጻፉት ላይ አስተያየት እንድሰጥ ይፍቀዱልኝ።

unnamed (2)ይመስለኛል አንድነት በጸረ-ሽብርተኝነት ሕግ ላይ ያልጠራ ነገር እንደነበረዉና አሁን በመግለጫው እንዳጠራው የሚገልጽ እድምታ ያለው ሐሳብ መሰለኝ ያስቀመጡት። አስተያየቶትን በነጻነት ለመጻፍና ለመናገር መብትዎትን እየተለማመዱ መሆንዎትን አደንቃለው። ማንም የተቃዋሚ ድርጅት ሆነ የተቃዋሚ መሪዎች ሁልጊዜ ቻሌንጅ ሊደረጉ ይገባል። ቻሌንጂን የሚፈሩ አምባገነን ባህርሪ ያላቸው ብቻ ናቸው ።

ሌላው “ አቶ ግርማ ሰይፉ “……ሁሉ ጊዜ ከመንግስት ጋር “እንትን” የምንለው በኢትዮጵያ ሰላም እና ፀጥታ፣ ችግር ይፈጥራሉ ብሎ የሚባል ነገር ካለ እኛም የበለጠ ያጋባንል….” ያሉትን ጠቅሰዉ “ይቺ ናት ጨዋታ” ብለዉም ጽፈዋሃል።

ይመስለኛል የሕግ ባለሞያ ሳይሆኑ አይቀሩም። የናንተ የሰማያዎችን አቋምን አላውቅም። አንድነት ግን ጠንካራ ጸረ-ሽብርተኛ አቋም ያለው ድርጀት ነው። እንደ አልካይዳ፣ አልሻባብ የመሳሰሉ ድርጅቶችን ለመዋጋት የሚደረገዉን አለም አቀፍ ጥረት ይደጋፋል። በተለይም አል ሻባብ የአካባቢያችን ትልቅ ጠንቅና ካንሰር እንደሆነም ያምናል። እንደ አይሳስ፣ ቦኮ ሃራም ያሉትን ይቃወማል። ይህን አቋም መያዝከህወሃት/ኢሕአዴግ ጋር መመሳሰል አይደለም።

ስለዚህ አቶ ግርማ ሰይፉ እንዳሉት በአገራችን ሰላምን ለማናጋት የሚሞክሩ ኃይላት ካሉ የአገር ሰላምና ጸጥታ አንድነትን ያገባዋል። ወንድሜ እኔ እስከሚገባኝ የአንድነት አላማና ራእይ ኢትዮጵያን ማዳን ነው። የእንግሊዘኛ አባባልን ልጠቅምና “ Andinet ( UDJ) is not against anyone ; but is FOR Ethiopia”.

unnamed (1)ጸረ-ሽብርተኝነት እና ሽብርተኛ የሆነው የጸረ-ሽብርተኝነት ህጉ የተለያዩ ነገሮች ናቸው። አንድነትን የሚተቹት “ለምን ሽብርተኝነት ላይ ጠንካራ አቋም ያዘ  ? “ ብለው ከሆነ ይንገሩን ። ይሄን ይላሉ ብዬ አላስብም። አርስዎም እንደ አይሰስ ያሉ ሽብርተኞችን አጥብቀው የሚቃወሙና የሚከሱ መሆንዎታን  ስለማወቅ።
አንድነትን የሚተቹት “የጸረ-ሽብርተኝነት ሕጉን ይደግፋል” ብለው ከሆነ ደግሞ መረጃ ያቅርብልን። እኛም ትችትዎትን እንድነጋራ። ግን የሚያቀርቡት መረጃ አይኖርም። ለምን የአንድነት ፓርቲ በስራው አቋሙን ያስመሰከረ ነውና። የአንድነት ፓርቲ ሕዝብ አደራጅቶ በይፋ በአደባባይ የጸረ-ሽብርተኝነት ህግን ተቃዉሞ፣  ሲንቀሳቀስ ለማየት የሚከተሉትን ፎቶውፖች መመለክቱ ብቻ ይበቃል። መቃወም፣ መተቸት መብት ነው። ግን በተቻለ መጠን አገናዝበንና መረጃ ይዘን ብናደርገውው ደግሞ የበለጠ ጥሩ ይሆናል።

ከዚህ በታች ያሉት ፎቶዎች እንደሚያሳዩት፣ አሁን ለሕሊና እስረኞች ተቆርቋሪ ነን የሚሉቱ ጡሩምባ ከመንፋታቸው በፊት፣ አሁን የጸረ-ሽብርተኝነት ሕጉ የሚቃወሙ ፊታወራሪዎች ከመነሳታቸው በፊት፣ የአንድነት ፓርቲና አንድነቶች ናቸው ለሕሊና እስረኞች አጋርነት በማሳየት፣ እስረኞች እንዲታሰሩበት ምክንያት የሆነው የጸረ-ሽብርተኝነት ሕግ እንዲሰረዝ፣ ከሶሻል ሜዲያዉና ከመግለጫም ባለፈ፣ ህዝብ ጋር በመዉረድ፣ ህዝብን በማስተባበር ሲጮሑ የነበሩት። ከአንድ አመት በፊት በአዲስ አበባና ከአዲስ አበባ ዉጭ ባሉ ከተሞች በተደረጉ ሰልፎች የነበረዉን በጥቂቱ ይመልከቱ። “የጸረ-ሽብርተኝነት ሕግ ሕግ መንግስቱን የጣሰ ነው” ወዘተረፈ የሚሉ መፈክሮችን ያንብቡ። ሐቁ እንግዲህ ይሄ ነው።

ዉድ አቶ ይድነቃቸው፤

unnamedበርግጥ የጸረ-ሽብተኝነት ሕግ እንዲሰረዝ፣ ለዉጥ እንዲመጣ፣ የሕሊና እስረኞች እንዲፈቱ ፍላጎት ካልዎት እንደ አንድ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ በሶሻል ሜዲያ ያለፈ ህዝብን የማደራጀት ሥራ እርስዎና ድርጅትዎ ለመስራት ሞክሩ። የአንድነት ፓርቲ በቅርቡ ባባህር ዳር፣ በአዳማ፣ በመቀሌ በመሳሰሉ ጽ/ቤቶችን በአዲስ መልክ አጠናክሮ በየከልሉ ህዝቡ ጋር ወርዶ እያደራጀ ነው። በአዲስ አበባ በ23ቱም ወረዳዎች በአሥሩም ክፍለ ከተማው መዋቅሩን ዘርግቶ ወደ ህዝብ እየወረደ ነው። እናንተ እዚያ ላይ በርቱ።
አንድነት ፓርቲ ምርጫዉን ለመሳተፍ በወሰነው ዉሳኔ ላይ  ባቀረቡት ትችት ላይ ደግሞ፣ የርስዎ ድርጅት የምርጫ ምልክት ከጥቂት ቀናት በኋላ እንደሚወስድና እንደማይወስድ ካየን በኋላ መልስ የምንሰጥብት ጉዳይ ይሆናል። ሰማያዊ ፓርቲ የምርጫ ምልክት ከወሰደ በኦፊሴል ምርጫዉን ለመወድዳደር ወስኗል  ማለት ነው። የምርጫ ምልክት ለምርጫ ለመወዳደር እንጂ ግድግዳ ላይ ሊሰቅል የሚወሰድ ባለመሆኑ።

 

 

 


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>