Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

በመርጫ “ለመሳተፍ” ጋዜጣዊ መግለጫ ለምን ? (ከይድነቃቸው ከበደ)

$
0
0
ይድነቃቸው ከበደ

ይድነቃቸው ከበደ

“አንደነት ፓርቲ” እንዲሁም ሌሎች የጉዳዩ ባለቤት የሆኑት አብዛኛው የተቃዋሚ ፓርቲዎች ከዚህ ቀደም ‹‹የፖለቲካ ምህዳሩ ጠቧል›› ከሚለው አልፈው ‹‹ ተዘግቷል›› ወደሚል ድምዳሜ መሸጋገራቸውን በተጨባጭ ማስረጃ ሲያጋልጡ እና ሲያረጋግጡ ከርመዋል፡፡እዚህ ደረጃ ላይ መድረሳችሁንም በተለያየ ወቅት በጋዜጣዊ መግለጫቸው ለሕዝብ አሳውቀዋል፡፡ “የፖለቲካ ምህዳር” ምርጫንም የሚያካትት ነው፡፡
ደካማ የመንግስት አስተዳደር ለመለወጥ ምርጫ ያስፈልጋል፡፡ይሁን እንጂ ነጻነት በሌለበት ፍትሃዊ ምርጫ ማካሄድ አይቻልም፡፡ የገዢው የወያኔ መንግስት ጉዳይ ፈጻሚው በሆነው፣ በምርጫ ቦርድ በኩል በተለመደው መንገድ፣ አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ ምርጫ ቢካሄድ የወያኔ መንግስት አሸናፊ ሆኖ የሚወጣበት እድሉ የሰፋ ነው፡፡ እንዲህ መሆኑን የተረዱ እውነተኛ የተቃዋሚ ፓርቲዎች በምርጫ ሥም ማጭበርበር ይበቃ !በማለት ትብብር መስርተው፣ ዘጠኝ ፓርቲዎች “ ነፃነት ለፍትሃዊ ምርጫ” የሕዝባዊ ትግል ፕሮግራም ይፋ አድርገዋል፡፡ ለነጻ፣ፍትሃዊ፣ ተኣማኒና አሳታፊ ዲሞክራሲያዊ ምርጫ፣ እንዲካሄድ በሠላማዊ ትግል አዎንታዊ ተጽዕኖ ለማሳረፍ ደፋ ቀና እያሉ ይገኛሉ፡፡
ሆኖም ግን በምርጫ ቦርድ እና በመንግሰት ላይ በሰላማዊ ትግል አዎንታዊ ግፊት ለማድረግ፣ በተጀመረው ህዝባዊ እንቅስቃሴ አጋር እና ደጋፊ ይሆናል ተብሎ ሲጠበቅ የነበረ ፓርቲ “እኔ በምርጫ እሳተፋለው” በማለት የይወቁልኝ እና የይድረሱልኝ ጥሪ ሳይገደድ በፍቃደኝነት ከወዲኹ ማስተላለፉ ምን የሚሉት ነገር ነው፡፡ወይስ የሚባለው ነገር እውነት ይሆን እንዴ ?
ለማንኛውም ነገሩን ግልፅ ለማድረግ ያህል ፤አንድ ፓርቲ በሕጋዊ መንገድ ሲቋቋም ስልጣን ሊይዝ የሚችለው በመርጫ እንደሆነ ይታወቃል፣ ይህ ማለት በምርጫ መሳተፍ የአንድ ፓርቲ መደበኛ ተግባሩ ነው፡፡ መደበኛ ተግባርን ለማከናወን የተለየ መግለጫ አያስፈልግም፡፡ከዚህ ይልቅ በምርጫ አልሳተፍም ማለተ የተሸለ የተለየ መግለጫ ያስፈልገዋል፡፡ ምክንያቱ ደግሞ የተሰጠ ተግባር ከማከናወን ይልቅ አለማከናወን በቂ ምክንያት የሚያስፈልገው በመሆኑ፡፡ለማንኛውም ይሄ በወፍ በረር ስለ ጉዳዮ ለምግለፅ ያህል ነው፣ወደፊት በሰፊው እመለስበታለው፡፡ እስከዚያው ቸር ወሬ ያሰማን !
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር !!!


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>