ነብዩ ሲራክ
ትናንትም ሆነ ዛሬ በሊባኖስ የኢትዮጰውያን የኮንትራት ሰራተኞች ጉዳይ የታዋቂ መገናኛ ብዙሃንና የነዋሪው መነጋገሪያ ከሆነ ቆይቷል ። ትናንት በዋና ከተማዋ በቤሩት በአንድ መኖሪያ መንደር አንዲት ኢትዮጵያዊት ከፎቅ ላይ ተንደርድራ ስትወድቅ የሚያሳየውን ተንቀሳቃሽ ምስል ይዞ የቀረበው ዜና እጅግ አሳዛኝ ነበር ።
መረጃው በአየር ከተለቀቀ በኋላ ጉዳዩን ለማጣራት ባደረግኩት ብርቱካን በሚል ስም የታወቀችው እህት ከሶስተኛ ፎቅ ላይ ስትዘል የወደቀችው ከፎቁ ስር ከነበረ መኪና ላይ በመሆኑ ለመትረፍ መቻሏን ለመረዳት ችያለሁ። ይህችው እህት መካስድ በተባለ ሆስፒታል ICU ላይ ሆና ህክምና አየተሰጣት መሆኑን መረጃዎች ከነምስሉ ደርሶኛል። በጉዳዩ ዙሪያ በሊባኖስ ነጋገርኳቸው ነዋሪዎች ሰቅጣጩን ምስል በዜና እወጃ ሰምተው ማዘናቸውን ገልጸውልኛል። ነዋሪዎች በማከልም ጠንካራ ባለመሆናቸው በሊባኖስ መንግስት በኩል ብዙም ክብር የማይሰጣቸው በሊባኖስ ኢትዮጵያ ቆንስል ሃላፊዎች የወደቀችውን ኢትዮጵያዊት ማንነትና የድርጊቱን መንስኤ ጉዳዩን በቅርብ መከታተል ቢችሉ መልካም ነበር ብለዋል። በአደጋው ዙሪያ ያነጋገርኳቸው ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ በሊባኖስ የኢትዮጵያ ቆንስል ባልደረባ በበኩላቸው አደጋ መድረሱ የሰሙት በቴሌቪዥን የሰሙ ሰዎች ወደ ቆንስሉ ለግልጋሎት በመጡ ሰአት በመሆኑን የገለጹልኝ ሲሆን ስለአደጋው ከሊባኖስ መንግስትም ሆነ ከሆስፒታል የደረሳቸው ምነም አይነት መረጃ እንደሌለ ጠቁመውኛል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ከአንድ ወር በፊት ” ኢትዮጵያውያቷ የቤት ሰራተኛ የአሰሪዎቿን ልጅ አፍና ገደለች ” ብለው በፍርድ ቤት የተያዘውን ጉዳይ ህግን ጥሰው ይፋ ማድረጋቸው ይታወሳል ። ብዙም ሳይቆይ ግን ቀረበው መረጃ ላይ ኢትዮጵያዊቷ በታማኝነት ማገልገሏን ከመሳየት ባለፈ ከሳሽ የሟች አባት ታልታወቀ የክትባት አይነት ከወሰደች በሁለተኛው ቀን የሞተች ልጁን ሬሳ ሳያስመረምር መቅበሩ ፣ ክትባት የሰጠው ጓኛየ ነው ያለውን ዶር ስምና ማንነት ይፋ አላደርግም ማለቱ ጉዳዪን የተገለባበጠ እንዲሆን ማድረጉን ሊባኖሳውያን ሳይቀር ምስክርነት መስጠታቸው አይዘነጋም። ይህም ጉዳይ ለኢትዮጵያዊቷ መብት የሚቆም ቢገኝ ከሳሽን ወደ ተከሳሽነት የሚቀይር ሁኔታ ሊፈጠር እንደሚችል ሲነገር በነዋሪው ዘንዳም ሰፊ የመነጋገሪያ ርዕስ ሆኖ ተስተውሎ አደንደነበር ይታወሳል።
እስኪ ቸር ያሰማን !
ነቢዩ ሲራክ