የህብር ሬዲዮ ጥቅምት 30 ቀን 2007 ፕሮግራም !
<... የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብት ኮሚሽንን በኢትዮጵያ ውስጥ እየተፈጸመ ያለውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት በአማራው ብሔር ላይ የሚፈጸመውን የዘር ማጥፋት ወንጀል ላይ በማስረጃ የተደገፈ መረጃ አቅርቤ ምርመራ እንዲያደርግ ጠይቄ ነው በደብዳቤ ፈጥነው ምላሽ የሰጡት...በእርግጥ አማራው ሲነካ ኦሮሞው ዝም ማለት የለበትም ኦጋዴኑ ሲነካ ሌላውም አብሮ መቃወም አለበት ካልተባበርን በስተቀር ድምጻችን ጎልቶ አይሰማም...>
ዶ/ር አክሎግ ቢራራ የኢኮኖሚ ተመራማሪና የቀድሞ የዓለም ባንክ ኤክስፐርት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ለጻፉት ደብዳቤ የሰጣቸውን ምላሽ አስመልክቶ ከህብር ሬዲዮ ጋር ካደረጉት ቃለ ምልልስ የተወሰደ (ሙሉውን ያዳምጡ)
በደላሎች ከወላጆቻቸው ጉያ እየተነጠቁ ለአሜሪካና ሌሎች አገራት ለማደጉ የሚሰጡ ልጆች ዕጣ ፈንታ እና የማደጎው ሳምንት በአሜሪካ(ልዩ ጥንቅር)
አልማዝን እንርዳ ለወገን የቀረበ ጥሪ በመኪና አደጋ በአረብ አገር ጉዳት ደርሶባት በቅርቡ አገሯ የገባችውን ኢትዮጵያዊት ለመታደግ የተጀመረ ዘመቻ (ልዩ ዝግጅት)
ኡበር ወደፊት አሽከርካሪውስ? (ውይይት)
ሌሎችም
ዜናዎቻችን
በጎንደር በተቀሰቀሰ የሕዝብ ተቃውሞ በአራት ወረዳዎች ትምህርት ተቋርጣል
ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ኢህአዴግ በጭቆና ውስጥ ጸጥ ያለውን ሕዝብ መቆስቆሱ ለውጡን ያግዛል ለስርዓቱ መዘዝ ያመጣል አለ
ኢትዮጵያዊቷ በዱባይ የቀጣሪዎቿን ሶስት ልጆች ልትገድል ሞከረች ተብላ ዕድሜ ልክ ተፈረደባት
የተመድ የሰብኣዊ መብት ኮሚሽን የመርማሪዎች ቡድን ኢትዮጵያ ገብቶ የመብት ጥሰቶችን ለማጣራት የመንግስትን ፈቃድ እየጠበኩ ነው አለ
አንድነት በተጽዕኖ ከመድረክ ተገፍቼ ወጣሁ አለ
የፓርቲው ም/ቤት ከመድረክ ጋር ያለው ግንኙነት ላይ የመጨረሻ ውሳኔ ሰጠ
ተቋርጣ የቆየችው ፍኖተ ነጻነት ጋዜጣ ታትማ ወጣች
ከዳላስ የጠፋችው ኢትዮጵአዊት ወይዘሮ አስከሬንና ታሽከረክረው የነበረችው መኪና ተገኘ
ኦጋዴን ነጻ አውጭ ግንባር ከኤርትራ ምንም ድጋፍ አላገኝም ሲል የተመድን ሪፖርት ተቃወመ
የመን 12 አሳ አስጋሪዎቼ በኤርትራ የባህር ጠባቂዎች ተይዘዋል ስትል ወቀሳ አቀረበች
ሌሎችም ዜናዎች አሉ