(ዘ-ሐበሻ) በአዲስ አበባ ግዮን ሆቴል ከዛም በአሜሪካ የተለያዩ ግዛቶች የተሳካ የሙዚቃ ኮንሰርቶችን ያቀረበው ቴዲ አፍሮ “70 ደረጃ” የተሰኘውን ነጠላ ዜማ ከለቀቀ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በአውሮፓ 7 የተለያዩ ከተሞች የሙዚቃ ኮንሰርቶቹን እንደሚያቀርብ ከድምጻዊው ሥራ አስኪያጅ ያገኘነው መረጃ አመለከተ::
ቴዲ ዲሴምበር 6 በፊላንድ ሄልሲንኪ
ዲሴምበር 13 በፈረንሳይ ፓሪስ
ዲሴምበር 20 በኖርዌይ ኦስሎ
ዲሴምበር 27 በስዊድን ስቶክሆልም
ለፈረንጆች አዲስ ዓመት ዋዜማ ዲሴምበር 31 በጀርመን ፍራንክፈርት
ለፈረንጆች አዲስ ዓመት ጃንዋሪ 3 በስዊዘርላንድ ጄኔቫ ሥራዎቹን ያቀርባል::
በአውሮፓ ቴዲ ኮንሰርቶቹን እንደሚያቀርብ ከተሠማ በኋላ ብዙዎች ቀኖቹን በጉጉት እየጠበቁት እንደሆነ ከተለያዩ የመረጃ ምንጮች ያገኘናቸው መረጃዎች ይጠቁማሉ::
70 ደረጃ ለተሰኘው ነጠላ ዜማ አዲስ የሙዚቃ ክሊፕ እየተሠራለት እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን ብዙዎች ይህን በጉጉት እንደሚጠብቁት ይታወቃል::