Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Sport: በዚህ ወር የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የፊፋ ደረጃ ተሻሻለ: * ከኡጋንዳ ጋር የወዳጅነት ጨዋታ ያደርጋል

$
0
0

ፊፋ በየወሩ በሚያወጣው የዓለም ሃገራት የ እግር ኳስ ደረጃ ኢትዮጵያ በዚህ ወር ካለፈው ወር የተሻለ ደረጃን አስመዘገበች:: የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በፊፋ ወርሀዊው የአገሮች ደረጃ ከባለፈው ወር 132ኛ ደረጃውን ወደ 111ኛ አሻሽሏል::
ethiopia
Afcon2015 በማጣሪያ ጨዋታ ማሊን በሜዳው 3- 2 ማሸነፉ ደረጃውን በ21 ከፍ እንዲል እንደረዳው የዘገበው ኢትዮኪክ የማሊ ብሔራዊ ቡድን ከ59ኛ አንድ ነጥብ አሻሽሎ 58ኛ ይዟል::

ይህ በ እንዲህ እንዳለ ኢትዮ ኪክ እንደዘገበው የዮጋንዳ እግርኳስ ፌዴሬሽን ዛሬ ይፉ ያደረገውን መግለጫ ጠቅሶ ሁጋንዳ በአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ ጋናን በሜዳዋ November 15 ከማስተናገዷ በፊት ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጋር የወዳጅነት ጨዋታ [November -9 ] በማንዴላ ብሔራዊ ስታዲየም ለማድረግ መታሰቡን ተገልፆል።

አፍሪካንፉትቦል ድህረገፅ የዮጋንዳን እግርኳስ ፌዴሬሽን ከፍተኛ የስራ ኃላፊ ኤጋር ዋትስን ጠቅሶ እንዳስነበበው የወዳጅነት ጨዋታውን ከፌዴሬሽኑ ጎን በተባባሪነት የዮጋንዳ የጤና ሚኒስቴር የተዘጋጀ ሲሆን በተለይም የጤና ቢሮው በወዳጀነት ጨዋታው ወቅት የስፖርት ቤተሰቡ ስለ HIV ስርጭት ትምህርት እና ፍቃደኛ ለሆኑት የነፃ የHIV ምርመራ ለማድረግ የሚችሉበት አጋጣሚ እንደሚኖር ኃላፊው ተናግረዋል።

በሌላ በኩል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ማሪያኖ ባሬቶ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጋር ስራቸውን እንደሚቀጥሉ እና የፊታችን እሮብ በፖርቱጋል የነበራቸውን እረፍት ጊዜ ጨርሰው ከቤተሰቦቻቸው ጋር ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመለሱ ከፌዴሬሽኑ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>