Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

ሰይፈ ነበልባል ራድዮ ስርጭቷ በአቅም ማነስ ምክንያት ሊቋረጥ ነው

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) ላለፉት3 ዓመታት ትኩረቷን በተለይ በኦሮሞ ሕዝብ ላይ እንዲሁም በሌሎች ሃገራዊ ጉዳዮች ላይ በማድረግ ትሰራጭ የነበረችው ሰይፈ ነበልባል ራድዮ በአቅም ማነስ ምክንያት ከዚህ ሳምንት ጀምሮ አገልግሎቷ እንደሚቋረጥ የራድዮዋ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ እዮብ ባይሳ ለዘ-ሐበሻ አስታወቀ።
SeifeNebelbal2014
“የኦሮሞን ሕዝብ ትግል በመደገፍና ትግሉንም በመዘገብ ላለፉት 3 ዓመታት በአየር ላይ የተለያዩ መረጃዎችን ስናቀርብ ቆይተናል” ያለው ጋዜጠኛ ኢዮብ ራድዮኑ እስካሁን የተወሰነች ድጋፍ ከሕዝብ ያገኝ የነበረ ቢሆንም ይህ በቂ ባለመሆኑና የገንዘብ እጥረት ስላለበትም ራድዮኑን ለማቆረጥ መገደዱን አስታውቋል።

እስካሁን ራድዮኑን ሲረዱ ለነበሩ ወገኖች ምስጋና ያቀረበው ጋዜጠኛ ኢዮብ ባይሳ ራድዮውን በገንዘብ አቅም ማነስ ምክንያት ለማቋረጥ ቢገደድ፣ የሚያደርገውን ትግል ግን እንደሚቀጥል አስታውቋል።

ሰይፈነበልባል ራድዮ በዚህ ሳምንት የመጨረሻዋን ስርጭት የምታካሂድ ሲሆን የገንዘብ ድጋፍ ካገኘች ግን አገልግሎቷ ሊቀጥል ስለሚችል አዘጋጆቹን በስልክ ቁጥር 832 245 3864 በመደወል ማግኘትና መረዳት የሚቻል መሆኑን ዘ-ሐበሻ ጥቆማዋን ታደርሳለች።


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>