(ዘ-ሐበሻ) በደቡብ ጎንደር ደብረታቦር ከተማ ለሰዓታት በጥይት ስትታመስ መቆየቷን ምንጮች ለዘ-ሐበሻ አስታወቁ::
ከግብር ጋር በተያያዘ ተነሳ በተባለው በዚሁ የጥይት ተኩስ ሶስት አርሶ አደሮች መቁሰላቸው የተዘገበ ሲሆን የሞተ ሰው ግን እንደሌለ የዘ-ሐበሻ ምንጮች አስታውቀዋል::
በሌላ በኩል ምኒልክ ሳልሳዊ በደቡብ ጎንደር ደብረታቦር ከተማ ከግብር ጋር በተያያዘ ክፈል ሌላው ቀደም ሲል ከፍያለሁ በሚል በተነሳው ጸብ ፓሊሰ በአሰቃቂ ሁኔታ አርሶአደሩን በመደብደቡ ገበያ ላይ የነበረው ሰው ህግ ፊት አቅርበህ እንዲቀጣ ታደርጋለህ እንጂ አትገድለውም በማለቱ የተነሳ ደብረታቦር ከተማ ለሰዓታት መናወጧንም ዘግቧል::
በዛሬው ዕለት በተነሳው በዚሁ ግጭት የአንድ አርሶ አደር እጅ መቆረጡን የዘገበው ምኒልክ ሌሎች ሶስት አርሶአደሮችም በጽኑ መቁሰላቸውን ዘገቧል:: ተኩስ ያነሳው ፖሊስም ወደ ደበረታቦር ሆስፒታል የተወሰደ መሆኑን የሚናገሩት የአይን እማኞች ሕይወቱ በአስጊ ደረጃ ላይ እንደምትገኝ ጠቁመዋል::