Neymar: Barcelona complete £49m signing of Brazil striker
ብራዜላዊው የፊት መስመር ተጨዋች ኔማር ለስፔኑ ሃያሉ ክለብ ባርሴሎና ለመጫወት በ48.6ሚሊዮን ኢሮ ከቀድሞው ክለቡ ሳንቶስ ተዘዋውሯል፡፡
የ21 ዓመቱ ብራዚላዊው ኔማር በባርሴሎና ለ5ዓመት ለመቆየት ተስማምቷል፡፡ ኔማር በሳኦ ፖሎ ቆይታው 229 ጭዋታ አድርጎ 138 ጎሎችን አስቆጥሯል፡፡ ለሀገሩ ብራዚልም በተሰለፈባቸው 33 ጭዋታዎች 20 ጎሎችን በስሙ አስቆጥሯል፡፡
ኔማር በአምስት ዓመት የባርሴሎና ቆይታ 190 ሚሊዮን ዩሮ ያገኛል፡፡ ኔማር ኑካንብ እስከሚደርስ ድረስ ለሳንቶስና የባለቤትነት መብት ላላቸው ሶስት ካንፓኒዎች 57ሚሊዮን ዩሮ ወጥቶበታል፡፡
ኔማርን ለማስፈረም የወጣው ወጪ ውድ መሆኑ ሌሎች ክለቦች የኔማር ፈላጊ ሆነው በመገኘታቸው ነው ብለዋል የባሴሎና ምክትል ፐሬዘዳንት ጆሴፕ ባርቶሚዩ፡፡
በተመሳሳይ ዜና ማንችስተር ሲቲ በሲቪያ የክንፍ ተጨዋች የሆነውን ጀሰስ ናባስን በ17 ሚሊዮን ዩሮ ለማዘዋወር ሁለቱ ክለቦች መስማማታቸውን የሲቪያ ድረ -ገፅ አረጋግጧል፡፡ የ27 ዓመቱ ናቫስ እ.ኤ.አ በ2010 በተካሄደው የአለም ዋንጫ የውጤታማው የስፔን የእግር ኳስ ቡድን አባል መሆኑ ይታወሳል፡፡