የኖርዌይ አፍሪካ የንግድ ማህበር በኦክቶበር 16, 2014 ባዘጋጀው ሴሚናር ላይ ለመካፈል በማህበሩ ተጋባዠ በመሆን ወደ ኖርዌይ የመጡ የውያኔ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶር ቲዮድሮስ አድሃኖም እና በስዊዲን የኢትዮጲያ አምባሳደር የሆኑት ወይንሽት ታደስ እንዲሁም ሌሎች ተላላኪ የወያኔ ባለ ስልጣናት በዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ የድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ በተጠራው የተቃውሞ ሰልፍ ላይ ፣ በኖርዌይ ኦስሎ እና በአካባቢው የሚኖሩ የድርጅቱ አባሎችና ደጋፊዎች በተገኙበት ታላቅ ተቃውሞ ገጠማችው::
በስፍራው ቁጣቸውን ለማሰማት ቁጥራችው በርከት ያሉ ኢትዮጲያውያኖች ከጠዋቱ 7 ስአት ጀምሮ በግዜው የነበረው የወቅቱ ዝናብና ብርድ ሳይበግራችው ከልማት በፊት ስብአዊ መብት ይከበር በሚል መሪ ቃል ሴሚናሩ በተደረገበት አዳራሽ ፊት ለፊት በመገኘት የተለያዩ መፈክሮችን በማሰማት ቁጣቸውን ገልጸዋል ::
በጊዜው የነበረው የተቃዋሚዎች ብዛትና ቁጣን የተቀላበት ተቃውሞ ያሰጋው የኖርዌይ ፖሊስ በርካታ የፓሊስ ሀይልን ብማ ስማርት እና አካባቢውን በመዝጋት ተቃውማውን ለመግታት ሲምክሩ ታይተዋል።
በተጨማሪም ሴሚናሩን ያዘጋጀው አካል ከተቃውሞ አስተባባሪ ጊዚያዊ ግብረሃይል የቀረበውን ተደጋጋሚ ጥያቄ ለመቀበል ፈቃደኛ ባልመሆናችው በዴሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጲያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ የተዘጋጀውን ደብዳቤ በተወካዩ አማካኝነት ለኖርዌይ የንግድ ማህበር የመረጃ ክፍል ሃላፊ ለሆኑት ለሚተር ሩነ አስረክበዋል ።
በመጨረሻም ተቃውሞዋችውን ሲገልጥጹ የነበሩ ኢትዮጲያውያኖች ተቃውሞዋችው በዚሁ ሳይገታ በሴሚናሩ ላይ ራሳችውን ስውረው ሲሳተፉ የነበሩ የወያኔ ልኡካን አባላት በድብቅ ወደ ማረፊያ ሆቴላችው ሲያመሩ ለተቃውሞ ተዘጋጅተው በነበሩ ሀገር ወዳድ ኢትዮጲያውያኖች ቁጣችውን እንቁላል በመወርወር ውርደትን አከናንበዋቸዋል።