Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

ታላቅ አገር አቀፍ የማኅበረ ቅዱሳን አጋርነት መረሃግብር እሁድ ጥቅምት 9 ቀን 2007 ዓም በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል

$
0
0

††† #እኔምለእምነቴ #ድምጻችንይሰማዘኦርቶዶክስ †††

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

የፊታችን እሁድ በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ቤተክርስቲያን ማኅበረቅዱሳንን በመደገፍ ታላቅ እና ደማቅ የአጋርነት ንቅናቄ እንደ እግዚአብሔር ፍቃድ ይከናወናል፡፡የዕለቱም መረሃ ግብር ብልሃት እና ብስለት የተሞላበት እንዲሆን የሁላችንም ግዴታ ነው፡፡

በመሆኑም እሁድ ጥቅምት 9 ቀን 2007 ዓም በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ቤተ/ክ ከሥርዓተቅዳሴ በኋላ፤ ፓትርያርክአባማትያስ፣ በአገርውስጥ እና በውጪ የሚገኙ በሙሉ ብፁዓን ሊቃነጳጳት፣ የአዲስ አበባ ሀገረስብከት ገዳማትና አድብራት አስተዳደሪዎች እና ፀሐፊዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው የውጪ ሀገር ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በሚገኙበት ታላቅ መንፈሣዊ ፕሮግራም ይካሄዳል፡፡
Mhbere Kidusan
በዚህም መሠረት የዕለቱ መረሃግብር እንደሚከተለው ይሆናል፡፡

1ኛ.የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታይ የሆን እንዲሁም ዓላማውን የምንደግፍ ፣ የማህበራዊ ድረገፅ ተጠቃሚ የማኅበረቅዱሳን አርማ የፕሮፋይል ገፃችን ምስል እናድርግ፡፡

2ኛ. የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታይ የሆን፣ የፊታችን እሁድ ጥቅምት 9 ቀን 2007 ዓ.ም በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ቤተክርስቲያን ሐይማኖታዊ አለባበሳችን ጠብቀን ፣ የተዋሕዶ ልጆች በዝተን እና አምረን እንደ እግዚአብሔር ፍቃድ በንፁ ልቦና አምልኮተ እግዚአብሔር በሚፈፀምበት ስፍራ መገኘት፡፡

3ኛ.ስለ ቅድስት ቤተክርስቲያናችን እና ስለአባቶቻችን አንደነት ፣ እርቀሰላም እንዲወርድ የህሊና ፀሎት ማድረግ፡፡

4ኛ. ነጭ መአረብ ወይም ሶፍት አሊያም ነጠላዎቻችንንና የመሳሰሉትን ነገሮች ማውለብለብ፡፡

5ኛ. ሴቶች በእልልታ ወንዶች በጭብጨባ ለ3 ደቂቃ በአንድነት እና በህብረት ማካሄድ፡፡

እነዚህ ከላይ የተገለፁት መረሃ ግብሮች የሚከናወኑት ሥርዓት ቅዳሴ ተፈፅሞ “ዝክረ አቦ ሊቀነጳጳሳት” መረሐ ግብር ከመጀመሩ በፊት ነው፡ የእለቱን ሰላማዊ ጥያቂያችን ከፈፀምን በኋላ፤ “ዝክረ አቦ ሊቀነጳጳሳት” መርሐ ግብር በአግባቡ እንዲካሄድ አስፈላጊውን ትብበር በማድረግ ሐይማኖታዊ ግዴታችን በመወጣት ወደመጣንበት በሰላም መመለስ፡፡

ይህ ለማኅበረ ቅዱሳን የምናሳየው አጋርነት በዕለቱ ለሚገኙት፤ ፓትርያርክ አባማትያስ፣ በአገር ውስጥ እና በውጪ የሚገኙ ብፁዓን ሊቃነጳጳት፣ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ገዳማትና አድብራት አስተዳደሪዎች እና ፀሐፊዎች ፣ በማኅበረ ቅዱሳን ላይ የተሳሳት ውሳኔ እንዳያስተላልፉ በእግዚአብሔር ስም ለመጠየቅ እና ለመማፀን ነው፡፡

ወስብህትለእግዚአብሔር !!!


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>