Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

ማሊዎች በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አውቶቡስ ላይ የድንጋይ እሩምታ አወረዱ

$
0
0

ምሽቱን በፖሊስ ታጅበው ወደ ሆቴል ያመሩት ዋሊያዎች ራዲሰን ሆቴልን ለቀው ወደ ኤርፖርት ሊያቀኑ ነው

*•* አዲስ አበባ ዛሬ ይገባሉ!

ethiopian national team mali
ኢትዮ ኪክ ኦፍ እንደዘገበው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ምሽቱን ካደረገው የማሊ ጨዋታ በኃላ በማኮ ስታዲየም የማሊ ደጋፊዎች ባስነሱት ሁከት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ለረጅም ሰአታት በመልበሻ ቤት እንዲሆኑ ተደርጎል። ሁከቱ ከጨዋታ ከማለቁ በፊት ተጎድቶ በወጣው ሳልሀዲን በርጌቾ ላይ እንዲሁም በተቀያሪ ቦታ ላይ የተቀመጡ የብሔራዊ ቡድኑ አባላት ላይ ድንጋይ ወርውረዋል።
የማሊ ፖሊስ ጨዋታ ካለቀ በኃላ የተፈጠረውን ሁከት አስለቃሽ ጭስ በመጠቀም ለመበተን ሞክሯል። በመጨረሻም የፀጥታ አስከባሪዎች የሁለቱ ቡድኖች ተጨዋቾች አውቶቢሶቻቸውን አጅበው ወደ ሆቴል አመርተዋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አውቶቢስ የድንጋይ እሩምታ ሲያጋጥመው አንድም የቡድኑ አባል አልተጎዳም።

በአሁኑ ሰአት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ካረፈበት ሆቴል አሁን ተነስቶ ወደ አውሮፖላን ማረፈያ ሊያመራ ነው። ቡድኑ ዛሬ አዲስ አበባ ይገባል።


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles