Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Health: ጓደኛሽ ሸንቃጣ የሆነችባቸው 20 ምስጢሮችን ላስተዋውቅሽ

$
0
0

ሊሊ ሞገስ

1. የሚጠጣ ውሃ ከእጃችሁ አትጡ
በማንኛውም ጊዜ ውሃችሁን ከቦርሳችሁ አውጥታችሁ መጎንጨት፣ ከጠማችሁም ጥማችሁን እስክትቆርጡ ድረስ መጠጣት ጥሩ ነው፡፡ ውሃ ብዙ አማራጭ ያለው መጠጥ ነው፡፡ ባዶውን ከጉሮሯችሁ አልወርድ ብሎ ያስቸግራችሁ እንደሆነ ሎሚ ወይም የሎሚ ጁስ ደባልቃችሁ ልትጠጡ ትችላላችሁ፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በቅርበት የምታገኙት ከሆነ ቫይታሚን ውሃ መጠጣትም ሌላኛው አማራጭ ነው፡፡ ንፁህ እና ኩልል ያለ ውሃን የመሰለ ነገር የለም፡፡
Nice ethiopian women body
2. የአካል ብቃት እንቅስቃሴ
የአካል ብቃት እንቅስቃሴን እንደ አንድ አስደሳች ድርጊት እንጂ እንደ አንድ መወጣት ያለባችሁ እለታዊ ግዴታ አትመልከቱት፡፡ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ሰውነታችሁ እና ህይወታችሁ ላይ ሊያመጣ የሚችለውን አዎንታዊ ለውጥ አስቡት፡፡ ቀጥሎ ምን መብላት እንደሚጠበቅባችሁ ከመጨነቅ ይልቅ ቀጥሎ ምን አይነት እንቅስቃሴ ልታደርጉ እንደምትችሉ አስቡ፡፡

3. የተመጣጠነ ምግብ ብሉ፡፡
አንዳንድ ምግቦች ምንም እንኳ ከስብ ነፃ ሆነው በአንፃሩ የፕሮቲን ይዘታቸው ከፍ ያለ ቢሆንም ዋና የካሎሪ ምንጭ ስለሚሆኑ ክብደት እንድትጨምሩ ሊያደርጓችሁ ይችላሉ፡፡ የምትመገቡት የቱንም ያህል የተመጣጠነ ምግብ ቢሆንም ዞሮ ዞሮ ተጨማሪ ካሎሪ ማለት ተጨማሪ ክብደት መሆኑን አትዘንጉ፡፡

4. የካፌይን አጠቃቀማችሁን ገደብ አበጁለት፡፡
ከሲጋራ በተዘዋዋሪ ከሚመጣ ጢስ እንኳን ቢሆን ራሳችሁን አርቁ፡፡
5. የአጭር ጊዜ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እቅድ ላይ ትኩረት አድርጉ፡፡
ዋናው ትኩረታችሁ መሆን ያለበት የለት ተዕለት ግባችሁን ዳር ማድረስ መሆን መቻል አለበት፡፡
6. በቀን ውስጥ በትክክል ምን ያክል እንደምትመገቡ ለመለየት የሚያስችላችሁን ዝርዝር መረጃ አነስተኛ ደብተር ወይ ማስታወሻ ላይ መዝግባችሁ ያዙ፡፡ በየካፌው የምትመገቡት ቺፕስ፣ ልጆቻችሁ መክሰስ ሲበሉ አብራችሁ የምትጎራርሱትን ነገር ሁሉ አካቶ መመዝገቡ አስፈላጊ ነው፡፡
7. አልፎ አልፎ ለምሳሌ በሳምንት አንድ ቀን እንዳሻችሁ ሁኑ (ሺ ዓመት አይኖር)፡፡ ይሁን እንጂ ሳምንት ሙሉ ወይም አንድ የዓመት ረፍት ጊዜ ሙሉ እንዳይሆን ጥንቃቄ አድርጉ፡፡
8. በዙሪያችሁ የሚገኙ ሌሎች ሰዎችም ጤናቸው የተጠበቀ እንዲሆን የምትችሉትን ሁሉ አድርጉ፡፡ አብሯችሁ ስፖርት የሚሰራ ጓደኛ ቢኖራችሁ መልካም ነው፡፡ ሌሎች በቅርበት የምታውቋቸውን ሰዎችም ስፖርት እንዲሰሩ አበረታቷቸው፡፡ ጠዋት ተነስቶ የእግር ጉዞ ማድረግ ወይም ዱብ ዱብ ማለት የሚወድ ጎረቤት ካላችሁ እናንተም መቀላቀል ትችሉ እንደሆነ ጠይቁ፡፡
9. መሰልቸት እንዳይገጥማችሁ በየጊዜው የምትሰሩትን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አይነት ቀያይሩ፡፡ ኤሮቢክስ፣ ብስክሌት መንዳት፣ ዋና መዋኘት፣ ዳንስ፣ የእግር ጉዞ ማድረግ ወዘተ እንደየሁኔታው እየለዋወጣችሁ ልትሰሯቸው የምትችሏቸው የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አይነት ናቸው፡፡
10. በጤና፣ የአካል ብቃት ወዘተ… ዙሪያ መረጃ የሚሰጡ መጽሔቶች እና ጋዜጦችን ‹‹ሰብስክራይብ›› በማድረግ ቢሯችሁ አሊያም ደግሞ ቤታችሁ ድረስ እንዲመጣላችሁ አድርጉ፡፡
11. አስፈላጊ የሆኑ አዳዲስ ንብረቶች ላይ ገንዘባችሁን አውጡ፤ ለስፖርት ምቹ የሆነ ጫማ፣ ቱታ፣ ሙዚቃ ማዳመጫ ኤምፒስሪ ወዘተ፡፡
12. አንዳንድ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አይነቶችን አዘውትራችሁ ለምሳሌ ለስድስት ወይም ለሰባት ቀናት መደዳውን በተከታታይ አንዳንዴም ጠዋትና ማታም ጭምር ለመስራት አቅዱ፡፡
13. ሰውነታችሁን ከሌሎች ሰውነት ጋር አታነጻጽሩ፡፡ በምትኩ የራሳችሁ ምርጥ ለመሆን ጥረት አድርጉ፡፡
14. አመጋገባችሁ ያልተመጣጠነ ከሆነ የተመጣጠነ ለማድረግ ጥረት አድርጉ፡፡ በየዓለቱ ቫይታሚን እና ሚኒራል እየወሰዳችሁ መሆኑን አረጋግጡ፡፡
15. የአካል ብቃት እንቅስቃሴያችሁን ደረጃ እና ክብደት በየጊዜው ለማሻሻል ስራ ስሩ፡፡
6. ዝም ብላችሁ ከጊዜ ለጊዜ እና አጋጣሚ ውሳኔውን ከመተው ይልቅ አንድ ቀን ቀደም ብላችሁ በማግስቱ የምትሰሩትን የእንቅስቃሴ አይነት አቅዱ፡፡ ከኩባንያ መሪዎች እስከ ቤት እመቤቶች እና የሀገር መሪዎች ድረስ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ለማድረግ ጊዜ ይኖራቸዋል፡፡ እናንተም ጊዜ የምታጡበት ምክንያት የለም፡፡
17. ክብደት መቀነስ ከሚለው ክልል ወጥታችሁ ሁለገብ አካላዊ ብቃት መፍጠር ወደሚለው ሽግግር አድርጉ፡፡ ስኬታችሁን ልብሳችሁ ምን ያህል ልክክ እንደሚልባችሁ በመመልከት ወስኑ፡፡
18. ያለማቋረጥ ልትከተሉ የምትችሉት የአመጋገብ ልምድ ይኑራችሁ፡፡ የቱንም ያህል የአካል ብቃት እንቅስቃሴ የምታደርጉ ቢሆንም የ‹‹ካሎሪ›› ይዘታቸው ከፍተኛ የሆኑ ምግቦችን እስከ አዘወተራችሁ ድረስ ሸንቀጥቀጥ ለማለት ፈተና ይገጥማችኋል፡፡
19. በቂ እንቅልፍ ተኙ፡፡ ስፖርት የሚሰሩ ሰዎች በጊዜ የመተኛት እና እጅግ ጥሩ እንቅልፍ የማግኘት ልማድ አላቸው፡፡
20. የአልኮል መጠጥ አወሳሰዳችሁን በተለያዩ የበዓላት እና ልዩ ልዩ ዝግጅቶች ወቅት ብቻ ወስኑ፡፡


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>