Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር በመተማ ገንዳ ውሃ ከተማ አንድ ባለስልጣን ገደልኩ አለ

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ለዘ-ሐበሻ በላከው መግለጫ በወያኔ አገዛዝ ባለስልጣናት ላይ የሚወሰደው እርምጃ አሁንም ተጠናክሮ እንደቀጠለ ነው አለ። ድርጅቱ በላከው መግለጫ መሠረት በመተማ ወረዳ ገንዳ ውሃ ከተማ አንድ የአገዛዙ ባለሥልጣን የተገደለ ሲሆን አንዱ ደግሞ ክፉኛ ቆስሏል ብሏል።

(የአርበኞች ግንባር ሠራዊት - ፎቶ ከፋይል)

(የአርበኞች ግንባር ሠራዊት – ፎቶ ከፋይል)


“የወያኔ አምባገነናዊ አገዛዝ መዋቅር አካል በመሆን ሕዝብን ኢ-ፍትሀዊ በሆነ መንገድ ሲያስሩ፣ ሲደበድቡና ሲገድሉ የኖሩትን ሹማምንቶች ከዚህ እኩይ ተግባራቸው ለማስቆም በተጀመረው እንቅስቃሴ፣ በምክር አልመለስ ያሉት ላይ እርምጃ የመውሰድ ሰፊ ዘመቻ እየተካሄደ መሆኑ ይታወቃል።” ያለው አርበኞች ግንባር “የዚህ ዘመቻ ዋና አስፈፃሚ የሆኑት የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር የውስጥ አርበኞች /ህቡዕ አባላት/ ሰሞኑን በወያኔ ቅጥረኞች ላይ ያነጣጠረ ተከታታይ ጥቃቶችን በመሰንዘር አስተማሪ እርምጃዎች መወሰዳቸው ይታወሳል። ይህ በውስጥ አርበኞች የተጀመረው ዘመቻ ተጠናክሮ በመቀጠል ማክሰኞ መስከረም 22 ቀን 2007 ዓ/ም በመተማ ወረዳ ገንዳ-ውሃ ከተማ ከጠዋቱ 12 ሰዓት ላይ በተወሰደው እርምጃ ሁለት የወያኔ አገዛዝ ባለሥልጣናት የጥቃቱ ሰለባ የሆኑ ሲሆን፤ በጥቃቱም የወረዳው ፖሊስ ኢንስፔክተር ዮሃንስ ይግዛው ሲገደል፣ ኮንስታብል ሻንበል አበበ በጥይት ተመቶ ክፉኛ ቆስሏል።” ሲል ለዘ-ሐበሻ ያደረሰው ዜና ይተንትናል:

“በዚህ የማጥቃት እርምጃ መደሰታቸውን የገለጹት የገንዳ-ውሃ ከተማ ነዋሪዎች እነዚህ እርምጃ የተወሰደባቸው ባለሥልጣናት፣ ሥልጣናቸውን ተገን በማድረግ ሕዝቡ ላይ ሲያደርሱ የነበረውን በደልና ግፍ በምሬት የገለጹ ሲሆን ሕዝብን በሚበድሉ የወያኔ ባለሥልጣናት ላይ እየተወሰደ ያለውን እርምጃ እንደሚደግፉና በማንኛውም መልኩ ከኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሠራዊት ጎን እንደሚቆሙ ተናግረዋል።” የሚለው የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር “ሀገርንና ወገንን እያጠፋ ካለ አምባገነን አገዛዝ ጋር ማበር ውጤቱ ሰሞኑን እየተወሰደ ያለው እርምጃ መሆኑን በመረዳት የወያኔ ሆድ አደር ባለሥልጣናት ከእኩይ ተግባራቸው ካልተቆጠቡ የተጀመረው የማጥቃት ዘመቻ ሰለባ እንደሚሆኑ በዜናው ላይ አሳስቧል።

አርበኞች ግንባር ገድልኩት ስላለው ባለስልጣን እና ፈጸምኩት ስላለው ጥቃት ከመንግስት ወገን የተሰጠ መግለጫ የለም።


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>