(ዘ-ሐበሻ) የአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይል ንቅናቄ በገንዳ ውሃ /ሸኸዲ/ ከተማ ድንገተኛ ጥቃት በመፈፀም ድል መጎናጸፉን ለዘ-ሐበሻ በላከው ዜና አስታወቀ። እንደ ንቅናቄው ጋዜጣዊ መግለጫ ከሆነ ዛሬ መስከረም 22 /2007 ከጠዋቱ 3 ሰዓት ላይ የአ.ዴ.ኃ.ን ልዩ ኃይሎች በወሰዱት የተጠና
ጥቃት የሸኸዲን ወረዳ ህዝብ ሲያሰቃዩና ሲጨቁኑ የኖሩትን፣ 1ኛ. የወረዳው ፖሊስ አዛዥ የነበረውን መ/አ ዮሃንስ ገብሬ 2ኛ፣ የወረዳው ፖሊስ ወንጄል መከላከል ሃላፊ የነበረውን አስር አለቃ ሻንበል ተሰማ፣ ላይ በተወሰደው እርምጃ ሁለቱም ተገድለዋል።
ንቅናቄው ለዘ-ሐበሻ በላከው መረጃ መሠረት ከሁለቱ ባለስልጣናት መካከል በቦታው አብሮ የነበረው የሸኸዲ ወረዳ የወያኔ የደህንነት አመራር ሞላልኝ አገኘው አቁስያለው ብሏል። “ኃይሎቻችን ጥቃቱን ፈፅመው ወደ ቦታቸው የተመለሱ ሲሆን ከመካከላቸው አንድ ደጉ ጉቸ የተባለ ጓዳችን ቆስሎ በጠላት ቁጥጥር ስር ውሏል።” ያለው ንቅናቄው ይህንን የጀመረውን ትግል አጠናክሮ እንደሚቀጥል በዚሁ አጋጣሚ እየገለፀ መላው የኢትዮጵያ ህዝብም ከጎኑ እንዲቆም ጥሪው ያቀርባል።
የአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይል ፈጽሜዋለሁ ላለው ጥቃትና ገደልኳቸው ስላላቸው ባለስልጣናት ከገዢው ፓርቲ በኩል የተሰጠ ምንም መረጃ የለም። ዘ-ሐበሻ ጉዳዩን ከሶስተኛ ወገን እንዲሁም ከራሱ ከኢሕአዴግ መከላከያ ሰራዊት አካባቢ ለማጣራት ያደረገችው ጥረትም አልተሳካም።