Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Sport: ማንችስተር ዩናይትድ 379 ሚሊዮን ፓውንድ ዋጋ ያላቸው ተጨዋቾች አሉት

$
0
0

ማንችስተር ዩናይትድ በያዝነው የውድድር ዘመን የዋንጫ ተፎካካሪ መሆን ካልቻለ ሉዊስ ቫን ሃል ለሰበብ ምክንያት አይኖራቸውም፡፡ በፕሪሚየር ሊግ ከፍተኛ ዋጋ ያለውን የተጫዋቾች ስብስብ ይዘዋልና፡፡

ከክረምቱ የተጫዋቾች ዝውውር ግርግር በኋላ ‹‹ሜይል ኦን ሰንደይ›› ባደረገው ጥናት የማንችስተር ዩናይትድ የዘንድሮ ስብስብ 379.4 ሚሊዮን ፓውንድ ድምር ዋጋ እንዳለው ተረጋግጧል፡፡ ይህም በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ውዱ ስብስብ ያስብለዋል፡፡ የማንችስተር ሲቲው ማኑኤል ፔሌግሪኒና የቬልሲው ጆዜ ሞውሪንሆ ስብስቦች እንኳን ይህን ያህል ዋጋ አያወጡም፡፡
Manchester united
ሰር አሌክስ ፈርጉሰን ከአንድ ዓመት በፊት በጡረታ ከተገለሉ በኋላ የማንችስተር ዩናይትድ ጎረቤቶች ማንችስተር ሲቲ ለተጫዋቾች ግዢ 215 ሚሊዮን ፓውንድ አፍስሰዋል፡፡ ይህም በሊጉ አናት ላይ ለመቆየት ከነበራቸው ዕቅድ ነበር፡፡ ማንችስተር ዩናይትድ ከፍታውን በመልቀቁ ወደ ኃያልነቱ ለመመለስ ተመሳሳይ እርምጃ ወስዷል፡፡

በቅርቡ በተዘጋው የብሪታኒያ የተጨዋቾች ዝውውር መስኮት እንኳን አንሄል ዲ ማርያ፣ አንደር ሄሬራ፣ ሉክ ሾው፣ ማርኮስ ሮሆ እና ዴሊይ ብሊንድን በቋሚ ዝውውር ካስመጣ በኋላ ፋልካኦን ከሞናኮ በውሰት ለማግኘት 5 ሚሊዮን ፓውንድ ከፍሏል፡፡ ሌላው የሊግ ተወዳዳሪ በርንሌይ ጆርጅ ቦይድ የተባለውን ተጨዋች በ3 ሚሊዮን ፓውንድ በማስፈረም የክለቡን የዝውውር ሪከርድ ሰብሯል፡፡ ዩናይትድ ግን ቢያንስ 10 ሚሊዮን እና ከዚያም በላይ የከፈለባቸው 16 ተጨዋቾችን ይዟል፡፡ ቡድኑ ከፍተኛ ዋጋ የተከፈለባቸው የማጥቃት ባህሪይ ያላቸው ተጨዋቾች አሉት በሚል ትችቶች ቢሰነዘሩበትም ቫን ሃል ግብ ጠባቂው ዴቪድ ዴ ሂያ፣ ተከላካዮቹ ፊል ጆንስ፣ ክሪስ ስሞሊንግ፣ ራፋኤል፣ ሮሆ፣ ሾው እና ብሊንድን የመሳሰሉ 104.7 ሚሊዮን ፓውንድ የወጣባቸው ተጨዋቾችም አሉትት፡ ዩናይትድ ለተከላካዮች ግዢ ብቻ ያወጣው ዋጋ 15 የፕሪሚየር ሊግ ክለቦች ለመላ ስብሰባቸው ካወጡት ይልቃል፡፡

የፕሪሚየር ሊጉ የተጨዋቾች ግዢ ፀባይ የተቀየረው በሮማን አብራሞቪችና በሼህ መንሱር ዘመናት ምክንያት ነው፡፡ እነዚህ ከበርቴዎች እርምጃቸውን ከአውሮፓ እግርኳስ ማህበር የፋይናንስ ጨዋነት ደንብ ጋር ለማስተካከል በሚታትሩበት በዚህ ሰዓት የማንቸስተር ዩናይትዱ ምክትል ሊቀመንበር ኢድ ውድወርድ ክለባቸው በሊጉ በሰባተኛ ደረጃ ቢያጠናቅቅም አሁንም ከአውሮፓ ሃያላን አንዱ መሆኑን ለማሳየት እየሞከሩ ነው፡፡ ከቻምፒዮንስ ሊግ ውጭ የሆነው ዩናይትድ ከሱፐር ስታሮችና በክለቡ አካዳሚ ባደጉ ተጨዋቾች ቡድን የመገንባትን ሞዴል ይዘዋል፡፡ ሪያል ማድሪድ በጋላክቲኮስ ዘመን ከተሉት ከነበረው ሞዴል ጋር ይመሳሰላል፡፡

በአሌክስ ክፍለ ሀገር ተወልደው ፍራንክ ላምፓርድ በተማረበት የህዝብ ትምህርት ቤት የተማሩት አካውንታት ውድወርድ ከቀድሞው የማንቸስተር ሲቲ ቺፍ ኤግዚኪዩቲቭ ጋሪ ኩክ የተለየ የረጋ ሰብዕና ቢኖራቸውም የሁለቱ ሰዎች ራዕይ ግን ይመሳሰላል፡፡ ባለፈው ዓመት ውድወርድ ከጋሪት ቤል ወይም ክርስቲያኖ ሮናልዶ ግዢ የዓለም ሪከርድን ለመስበር ዝግጁ መሆናቸውን ሳይቀር ተናግረው ነበር፡፡ የዓሊያን ባይሰብሩም የብሪታኒያን ሪከርድ በአንሄል ዲ ማሪያ ግዢ ጨብጠዋል፡፡ በመጪው ጃንዋሪም ለኬቭን ስትሩትማንና ከፍ ያለ ደረጃ ላይ ለሚገኝ አንድ ተከላካይ ለመግዛት ተዘጋጅተዋል፡፡ በሚቀጥለው ዓመት ክረምትም 45 ሚሊዮን ፓውንድ በመክፈል ፋልካኦን በቋሚ ዝውውር የማስቀረት ምርጫም አላቸው፡፡

የፋይናንስ ትንተና የሚያቀርበው ኩባንያ ዴሎይት ማንቸስተር ዩናይትድ ባሳለፍነው የዝውውር መስኮት በግርድፉ ከዚህ ቀደም ያልታየ ከፍተኛ የዝውውር ወጪ ማውጣቱን አረጋግጧል፡፡ ለአዳዲስ ከዋክብት ግዢ በክረምቱ ወቅት ቀይ ሰይጣኖች 150 ሚሊዮን ፓውንድ ፈሰስ አድርገዋል፡፡ ከፕሪሚየር ሊጉ ክለቦች አጠቃላይ ግርድፍ ወጪ 18% ያህሉን ይዘዋል፡፡ ፈርጉሰን ዩናይትድ ባሰለጠኑባቸው የመጀመሪያ ዓመታት ለተጨዋቾች ግዢ እንዲሁ ተከታታይ ሪከርዶችን ሰብረው ነበር፡፡ ጋሪ ሊስተር፣ ሮይ ኪን እና አንዲ ኮል ለዚህ ተጠቃሾች ናቸው፡፡ ግሌዘሮች ከመጡ በኋላ ግን የግዢ ወጪያቸው ዝቅ በማለቱ ማንቸስተር ሲቲ በገበያው ላይ የበላይነቱን ይዞ ቆይቷል፡፡

አሁን መዘውሩ ወደ ማንችስተር ዩናይትድ ተመልሷል፡፡ ዩናይትድ ከቻምፒዮንስ ሊግ ከአንድ የውድድር ዘመን በላይ ርቆ መቆየት አይፈልግም፡፡አለበለዚያ ታላላቅ ተጨዋቾችን መሳብ አይችልም፡፡ በእግርኳስ ስፖርት ከፍተኛ ወጪ የሚያወጣ ክለብ ተብሎ ሲወሰድ የቆው ማንቸስተር ሲቲ እንኳን ዘንድሮ ከዩናይትድ በ26 ሚሊዮን ፓውንድ ነሰ ስብስብ ይዟል፡፡ 353.7 ሚሊዮን ፓውንድ ማለት ነው፡፡ ሞውሪንሆ የ301.3 ሚሊዮን ፓውንድ ተጨዋቾችን ሰብስበው ቡድን ሰርተዋል፡፡ እንደ ፈርናንዶ ቶሬስና ማርኮ ቫን ጊንኬል የመሳሰሉት ተጨዋቾቻቸው በውሰት በመለቀቃቸው ዘንድሮ ሊጠቀሙባቸው አይችሉም፡፡

በአጠቃላይ ክለቦች ሊያገኙት ያቀዱት ስኬት መጠን ለዝውውር ከሚያወጡት ወጪ ጋር በቀጥታ ተያይዞ ይታያል፡፡ በፕሪሚየርሊጉ ስድስት ክለቦች ማለትም ዩናይትድ፣ ሲቲ፣ ቼልሲ፣ ሊቨርፑል፣ አርሰናል እና ቶተንሃም ከተቀሩት የሊጉ ተወዳዳሪዎች ጋር ሰፊ የወጪ ልዩነት ፈጥረዋል፡፡ በሰባተኛ ደረጃ ውድ ስብስብ ያለው ኤቨርተን ሲሆን በድምሩ 96 ሚሊዮን ፓውንድ ይሆናል፡፡

በዚህ ሳምንት በፕሪሚየር ሊጉ ሰንጠረዥ ከመጨረሻዎቹ ሶስት ደረጃዎች ላይ በሁለቱ ላይ የተቀመጡት በርንሌይ እና ክርስታል ፓላስ እንዲሁ በዝውውር ወጪ የመጨረሻዎቹን ደረጃዎች ይዘዋል፡፡

በተጨዋቾች ግዢ ወጪ መሪነቱን የያዘው ዩናይትድ ዘንድሮ አንድም የሊግ ጨዋታ ሳያሸንፍ በሰንጠረዡ 14ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡ አዳዲሶቹ ዝውውሮች ተሟልተው ለጨዋታ ዝግጁ በመሆናቸው በመጪው እሁድ ከኪውፒአር ጋር በሚደረገው ጨዋታ ነገሮች ሊቀየሩ ይችላሉ፡፡ ሌላው መታየት ያለበት ስዋንሲ ሲቲ ነው፡፡ የዌልሱ ክለብ በመጀመሪያ ቡድኑ ውስጥ ያሰባሰባቸው 25 ተጨዋቾችና ሊያጫውታቸው ፍቃድ ያገኘባቸው ከ21 ዓመት በታች ተጨዋቾች በድምር ያላቸው ዋጋ አነስተኛ ነው፡፡ 44.6 ሚሊዮን ፓውንድ መሆኑ ነው፡፡ ሆኖም ባለፉት ሁለት የውድድር ዘመናት በከፍተኛው ዲቪዚዮን ውስጥ አንፃራዊ ስኬትን እየተቀዳጁ ይገኛሉ፡፡ አሁንም ከሶስት ጨዋታዎች በኋላ የፕሪሚየር ሊጉን መሪነት በጥምረት ይዘዋል፡፡

የተጨዋቾች ግዢ ላይ የሚወጣው ገንዘብ እየናረ በሄደ ቁጥር የሊጉ የፉክክር ሚዛን በየጊዜው ይዛነፋል የሚል ስጋት አለ፡፡ ይህም በርካቶቹን ክለቦች ሊያጠፋቸው ይችላል፡፡ ባለፈው ሳምንት አዲሱ ፈራሚ ብሊንድ የሆላንድ ኮከብ ተብሎ በጋዜጠኞች ከተመረጠ በኋላ ቫን ሃል በሰጡት አስተያየት አሁን በከፍተኛ ጫና ላይ መገኘታቸውን አምነዋል፡፡ ክለባቸው ማንቸስተር ዩናይትድ የፋይናንስ ጡንቻውን በማሳየት የሚፈልጓቸውን ተጨዋቾች አሰባስቦላቸዋል፡፡ አሁን ተራው የቫን ሃል ነው፡፡ ተፎካካሪ የመሆን 379 ሚሊዮን ግዴታዎች ውስጥ ገብተዋል፡፡

 

የ2014 – 15 የፕሪሚየር ሊጉ ቡድኖች ድምር ዋጋ እና (ውድ ተጨዋቾቻቸው)

  1. ማንችስተር ዩናይትድ

– 379.4 ሚ.ፓ-አንሄል ዲ ማሪያ – 59.7 ሚ.ፓ

  1. ማን.ሲቲ

– 353.3 ሚ.ፓ – ሰርጂዮ አጉዌሮ – 38 ሚ.ፓ

  1. ቼልሲ

– 301.3 ሚ.ፓ – ኤደን ሃዛርድ/ዊልያን ዲ ኮስታ 32 ሚ.ፓ

  1. ሊቨርፑል

– 253.8 ሚ.ፓ – አዳም ላላና – 25 ሚ.ፓ

  1. አርሰናል

– 242.7 ሚ.ፓ – ሜሱት ኦዝል – 42.5 ሚ.ፓ

  1. ስፐርስ

– 178 ሚ.ፓ – ኤሪክ ላሜላ – 25.8 ሚ.ፓ

  1. ኤቨርተን

– 95.7 ሚ.ፓ – ሮ ሉካኩ – 28 ሚ.ፓ

  1. ሳውዛምፕተን

– 90.4 ሚ.ፓ – ሼን ሎንግ – 12 ሚ.ፓ


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>