ህብር ሬዲዮ መስከረም 11 ቀን 2007 ፕሮግራም
እንኳን ለህብር ሬዲዮ አምስተኛ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ!
<... የስኮትላንድ ሕዝብ መንገንጠልን አልፈልግም ማለቱ ሕዝቡ በአንድ ላይ ለመኖር ሲመርጥ መብቱም በእንግሊዝ ስር እያለ ራሱን በራሱ የማስተዳደር መብቱ ተከብሮ የተወሰኑት ነጻነቶቹ ተጠብቀው ነው። ከዚህ ኢትዮጵያውያን የሚያገኙት ትልቅ ትምህርት ምንድነው?... መንገንጠልን ድሮም የኦሮሞ ነጻነት ግንባር በፕሮግራሙ ያሰፈረው አይደለም እኛ የኦሮሞ ሕዝብ ብዙሃን ነው አይገነጠልም መገንጠል የጥቂቶች(ማይኖሪቲ) ጥያቄ ነው ...>
ዶ/ር ኑሩ ደደፎ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር( በጄ/ል ከማል ገልቹ የሚመራው) ቃል የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴና የኢንፎርሜሽን ጉዳይ ሀላፊ ስኮትላንዳውያን የሰጡትን የአንድነት ይሻላል ውሳኔ መሰረት በማድረግ ጠይቀናቸው ለህብር ሬዲዮ ከሰጡን ቃለ መጠይቅ የተወሰደ(ሙሉውን ያዳምጡት)
<...በስዊድን ለተቃውሞው ሰፊ ዝግጅት ስናደርግ ነበር የቆየነው እኛ እንደውም ያው ንዋይ ይገኛል ብለን ነበር የአምባሳደሯ መምጣት በሁዋላ የተሰማ ነው ሕዝቡ በቁጣ የገማ ዕንቁላልና አሳ በመወርወር በአገዛዙ በአገር ቤት የሚደርሰውን ግፍ ተቃውሞ እነሱም በየደረሱበት ሰላም እንደሌላቸው አሳይቷል። የወያኔን ዝግጅት ለማድመቅ የመጣው ንዋይ ግን ...>>
አቶ ግሩምጌታ ዘላለም በስዊድን የኢትዮጵያ ድምጽ ሬዲዮ አዘጋጆች አንዱ ስለ ቅዳሜው ማታ ጠንካራ የኢትዮጵያውያን ተቃውሞ አስመልክቶ ካደረግንለት ቃለ ምልልስ የተወሰደ(ሙሉውን ያዳምጡት)
የስኮትላንድ ሕዝበ ውሳኔኛ የዓለም ታላላቅ መሪዎች አስተያየት ስለ አንድነት (ልዩ ዘገባ)
(ልዩ ዘገባ)
ዜናዎቻችን
የጋምቤላ ንቅናቄ አገዛዙ ሰሞኑን በመዠንገር ብሄር አባላት ላይ ለፈጸመው ግድአ የበቀል እርምጃ እወስዳለሁ አለ
ኢትዮጵያ ዛሬም በኢቦላ ይጠቃሉ ከተባሉ አስር አገሮች ተርታ መሰለፉዋ ተገለጸ
በስዊድን ኢትዮጵያውያን በአገዛዙ አምባሳደርና አጃቢዎቻቸው ላይ የተበላሸ ዕንቁላልና አሳ በመወርወር ተቃውሟቸውን ገለጹ
መምህር ግርማ ወደ አሜሪካ ሊመጡ ነው ተባለ
መኢአድ አንድ አባሉ ሰሞኑን በወያኔ በጥይት ተደብድበው መገደላቸውን ገለጸ
የእንግሊዝ ፖሊሶች በአገሪቱ ከወራት በፊት ህገወጥ የሆነውን ጫት ሰሞኑን ያዙ
የተመድ የአገዛዙን በጸረ ሽብር ሕግ ስም የሚወስደውን የአፈና እርምጃ እንዲያቆም ጠየቀ
ሌሎችም ዜናዎች አሉ