(ዘ-ሐበሻ) ከ2019 እስከ 2023 ድረስ የሚደረጉ የአፍሪካ ዋንጫዎችን የሚያዘጋጁ ሃገራት ዝርዝር ታወቀ። እነዚህን 3 የአፍሪካ ዋንጫዎች ማለትም የ2019 እና የ2021 የአፍሪካ ዋንጫን ለማዘጋጀትም አልጄሪያ፣ ካሜሩን፣ ጊኒ፣ ኮትዲቯር፣ጋቦን፣ ዲሞክራቲክ ኮንጎ እና ዛምቢያ በእጩነት ቀርበው ነበር።
የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌደሬሽን ወይም ትንሹ ሲጠራ “ካፍ” የ2019 እና የ2021 እና 2023 የአፍሪካ ዋንጫን እንዲያስተናግዱ የተመረጡ ሃገራትን ይፋ ሲያደርግ ጥያቄያቸው ውድቅ የሆነባቸው እጩ ሃገራት የማዘጋጀት አቅማቸውንና ፍላጎታቸውን የሚያሳይ እና የሚያስተዋውቅ የ30 ደቂቃ ቪድዮ በአፍሪካ አንድነት ድርጅት ከካፍ አባል አገራት ለተውጣጡ ተወካዮች ቀርቦ ነበር።
በዚህም መሰረት፡
– የ2019ን የአፍሪካ ዋንጫ ካሜሮን
– የ2021ን የአፍሪካ ዋንጫ አይቮሪኮሰት
– የ2023 የአፍሪካ ዋንጫም በጊኒ እንዲደረግ ወስኗል።
ኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋንጫን ለማሰዳዳት
የ2017ቱን የአፍሪካ ዋንጫ ለማስተናገድ ይሁንታን አግኝታ የነበረችው ሊቢያ ውድድሩን እንዳታስተናግድ መከልከሏን ተከትሎ፥ በርካታ ሀገራት ውድድሩን ለማዘጋጀት ፍላጎታቸውን ያሳዩ ሲሆን፤ ኢትዮጵያ በበኩሏ ውድድሩን ለማዘጋጀት ያላትን ፍላጎት ጨምሮ ፤ ለውድድሩ ብቁ የሚያደርጓትን ዝርዝር ነጥቦች በካፍ ቀነ ገደብ መሰረት በኢትዮጵያ እግርኳስ ፌደሬሽን በኩል እንደምታቀርብ ተገልጿል።