14 ዓመት ተፈርዶበት እስር ላይ የሚገኘው ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ የጻፈው “የነፃነት ድምጾች፤ ከማዕከላዊ እስከ ዝዋይ ግዞት” መጽሐፍ በገበያ ላይ መዋሉን ከአዲስ አበባ ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ አመከተ።
በዝዋይ ጨለማ እስር ቤት ውስጥ እንደጻፈው በሚነገው በዚህ መጸሐፍ ጋዜጠኛው ክስ ከተመሰረተበት ጊዜ አንስቶ እስከአሁን ድረስ የገጠመውን ውጣ ውረድ ዘርዝሮ ጽፎታል።
በአራት ም ዕራፎች እንደተከፈለ በተነገለጸለት በዚህ “የነፃነት ድምጾችን ከማዕከላዊ እስከ ዝዋይ ግዞት” መጽሐፉ ስለእስረኞች አያያዝ፣ ከፖሊሶች ጋር ስላለው መስተጋብር፣ ስለሰብአዊ መብት ጥሰት፣ የአገሪቱ ትልልቅ ባለስልጣናት ከነበሩ እስረኞች ጋር ስላደረገው ቃለ ምልልስና ስለታሰረባቸው ወህኒ ቤቶች ገጽታ ያስቃኛል ተብሏል፡፡ መጽሐፉ በኢትዮጵያ በ50 ብር ከ60 ሳንቲም እየተሸጠ ነው።