Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

ኢትዮጵያ ከዓለም እግር ኳስ በ20 ደረጃዎች አሽቆለቆለች

$
0
0

walia
የዓለም አቀፉ እግር ኳስ አስተዳዳሪ /ፊፋ/ በየ ወሩ በሚያወጣው የሀገራት የእግር ኳስ ደረጃ ኢትዮጵያ በያዝነው ወር 20 ደረጃዎችን አሽቆልቁላለች፡፡

ፊፋ በየወሩ የሚያወጣው የዓለም ሃገራት የእግር ኳስ ደረጃን ይፋ አደረገ። በዚህም መሠረት ባለፈው ወቅት 112ኛ ደረጃ ላይ የነበረችው ኢትዮጵያ በዚህ ወር ወደ 132ኛ ደረጃ ወርዳለች።

አስልጣኝ ሰውነት ቢሻውን አሰናብቶ በውድ ክፍያ የውጭ ሃገር አሰልጣኝ የቀጠረው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተደጋጋሚ ሽንፈቶችን እያስተናገደ ሲሆን ይህም ለደረጃው መውረድ ዋናው ምክንያት እንደሆነ የስፖርት ተንታኞች ለዘ-ሐበሻ ይገልጻሉ።
standing world soccer
ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ያደረገቻቸውን ጨዋታዎችን በሽንፈት መጀመሯ ተስፋ አድርጎ የነበረውን የስፖርት ቤተሰብ እጅጉን ያሳዘነ መሆኑን ከተለያዩ ሶሻል ሚዲያዎች ከሚሰጡ አስተያየቶች መገንዘብ ይቻላል።

በፊፋ ደረጃ መሰረት ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ሃገራት 37ኛ ደረጃን ያገኘች ሲሆን አልጄሪያ ከአፍሪካ አንደኛ እንዲሁም ከዓለም 20ኛ ሆናለች። በሴፕቴምበር የዓለም እግርኳስን ደረጃ ጀርመን፣ አርጀንቲና እና ኮሎምቢያ ይመሩታል።


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>