ነገረ ኢትዮጵያ
ገዥው ፓርቲ በሚሰጠው የ‹‹አብዮታዊ ዴሞክራሲ›› ስልጠና በአካል ተገኝተው የማይሳተፉ በማህበር የተደራጁ ዜጎች በማህበራቸው ላይ እርምጃ እንደሚወሰድና የመስሪያ ቦታቸውንም ሊቀሙ እንደሆነ ተገለጸ፡፡
በተለይ ቅዳሜ መስከረም 10 ጀምሮ በማህበር ለተደራጁ ዜጎች ገዥው ፓርቲ በሚሰጠው የ‹‹አብዮታዊ ዴሞክራሲ›› ስልጠና የሚሳተፉት ሰርተፍኬት እንደሚሰጣቸውና በአካል ተገኝተው ያልተሳተፉት እርምጃ እንደሚወሰድባቸው ለማህበር አባላቱ የተሰራጨው ማስጠንቀቂያ ወረቀት ያመላክታል፡፡
ለማህበር አባላቱ የተሰራጨውን ማስጠንቀቂያ ሰነድ እንደሚከተለው አያይዘነዋል፡፡