አንዳንዴ ሰውነታችን አደገኛ ላልሆኑ ንጥረ ነገሮች በመቆጣት(በአለመቀበል) መልስ ይሰጣል። እነዚህ የመቆጣት መልሶች የሚቆረቁር አይን፣ ንፍጥ የሚወርድበት አፍንጫ፣ የሚከረክር ጉሮሮ፣ የቆዳ ሽፍታ፣ ማሳከክ፣ ማበጥ እና ውሃ መቋጠርን ሊያጠቃልል ይችላል። እነዚህ የሰውነት መቆጣቶች ሊያነሳሱ ከሚችሉት ንጥረ ነገሮች ምግብ፣ የጽዳት ኬሚካል፣ አየር ላይ የሚገኝ የአበቦች ፈሳሽ (ፖለን)፣ አቯራ እና እንስሶች ይገኙበታል።
ብዙ ሰዎች በሳር፣ የቢርችን ተክል እና ሌሎች ዛፎች ፈሳሾች ምክንያት የሰውነት መቆጣት ያጋጥማቸዋል። ከእነዚህ አትክልቶች የሚወጣው ፈሳሽ በፀደይ እና በበጋ ወቅቶች በብዛት ይታያል። በተለያዩ ጊዜአት የሚበቅሉ የተለያዩ የአበባ አትክልቶች እንደዚሁም ንፋስ እና የአየር ሁኔታ ለፈሻሾቹ መስፋፋት ወሳኝ ናቸው። ስለዚህም ስለ ፈሳሾቹ ማሰጠንቀቂያ ለማወቅ በአካባቢያችሁ የሚታተሙ ጋዜጦችን ማንበብ ጥሩ ሃሳብ ሊሆን ይችላል።
ከኖርዌይ ህዝብ 40 በመቶ የሚሆነው የሰውነት መቆጣት (አለርጂ) አለበት። እነዚህን የሰውነት መቆጣት ወይም አለርጂ ለመቆጣጠር የተዘጋጁ መድሃኒቶች አሉ። አንዳንድ መድሃኒቶችም የሀኪም ትዕዛዝ አያስፈልጋቸውም። ትክክለኛውን መድሃኒት ለመግዛት በአንደኛ የመድሃኒት መደብር በመሄድ እርዳታ ለማግኘት ይቻላል። ሌሎች መድሃኒቶች ግን የሀኪም ትዕዛዝ ያስፈልጋቸዋል። ስለ እነዚህ ሁለት መድሃኒቶች ተመለከተ መረጃ ለማግኘት ወደ ዶክተር መሄድ ጥሩ ነው። አንዳንድ መድሃኒቶች ለምሳሌ ክኒኖች ለሰውነት መቆጣት (አለርጂን) ይቀንሳሉ። ሌሎች ለምሳሌ ወደ አፍንጫ የሚረጩ ወይም የአይን ጠብታዎች ምልክቶቹን ይቀንሳሉ።
ወደ አዲስ ቦታ ሲጓዙ ቀደም ሲል አጋጥሞአችሁ የማያውቅ የሰውነት መቆጣት (አለርጂ) ሊያጋጥሙአችሁ ይችላሉ። እነዚህም በአካባቢ የሚገኙ ያልለመዳችሁት ነገሮች ወይም አዲስ ምግብ በማግኘታችሁ የሚከተሉ ሊሆኑ ይችላሉ።