የህብር ሬዲዮ መስከረም 4 ቀን 2007 ፕሮግራም
እንኳን ለአዲሱ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ!
<... የእኛ የኢትዮጵያውያን የቀን አቆጣጠር መለየት ከሌሎች ማነስ አይደለም። ህንድም ቻይናም የራሳቸው አቆጣጠር አላቸው ። እነሱ የራሳቸውን ትተው ወደ እኛ ይምጡ እንጂ የእኛነታችንን መለያችንን መተው የለብንም። የዓመተ ምህረት ልዘዩነቱም የመጣው...>>
ፕ/ር ጌታቸው ሀይሌ በቀን አቆጣጠራችን ላይ ለህብር ሬዲዮ ከሰጡት ቃለ ምልልስ ቃለ መጠይቅ የተወሰደ(ሙሉውን ያዳምጡት)
<<...ይህ ስያሜ እንዲሰየም ብዙ ደክመናል ። ይሄ ልዩ የእኛ መታዋቂያችን ነው....እዚህ በሎስ አንጀለስ የሊትል ኢትዮጵያ የዘንድሮ የኢትዮጵያውያን አዲስ ዓመት ክብረ በዓል የደመቀ ያማረ ነበር ከዚህ በፊት ሲበጠብጡን የነበሩት የስርዓቱ ባለሟሎችም አልነበሩም...>>
ወ/ት ሜሮን አሀዱ ሊትል ኢትዮጵያ ተብሎ እንዲሰየም ትልቅ አስተዋጽዎ ካደረጉት አንዱዋ የዘንድሮውን በዓል አስመልክታ ከሰጠችን ማብራሪያ
በቬጋስ የኢትዮጵያዊነት ቀን ለመጀመሪያ ጊዜ በአደባባይ ከልጅ እስከ አዋቂ ኢትዮጵአውያን በአንድ ላይ ታድመውበት ደምቆ ተከብሯል
ለኢትዮጵያዊነት ቀን የተደረጉት የእግር ኳስና የጠረጴዛ ቴኒስ ውድድሮች እንዲሁም የሩጫው ውድድር በሶስት ታዋቂ ኢትዮጵያውያንን ያስታወሰ ነው። የክቡር አቶ ይድነቃቸው ተሰማ መታሰቢያ፣የጋዜጠኛና ገጣሚ ሰለሞን ተሰማና በአበበ በቂላ ስም ነበር። በዓሉን አስመልክቶ ውይይት ከተሌአዩ እንግዶች ጋር
የስኮትላንድ ሕዝበ ውሳኔ ዋዜማና የእንግሊዝ ፖለቲካ (ልዩ ዘገባ)
ዜናዎቻችን
የኤርትራው ፕ/ት ኢሳያስ አፈወርቂ ወደ ግብጽ መሔድ ቅር አያሰኘንም ሲሉ አቶ ሀይለማርያም ተናገሩ
ኢትዮጵያዊው የፈውስ አባት መምህር ግርማ በስዊስ ፖሊሶች ታገዱ
የግንቦት ሰባት ሕዝባዊ ሀይል የፖለቲካ ሀላፊ ዘመኑ ካሴ በስዊዘርላንድ ለተደረገው ስብሰባ ንግግር አደረገ
በአገር ቤት በሚገኙ ተቃዋሚዎች ላይ የሚደረገው ጫና በአዲሱም ዓመት ቀጥሏል
የአኙዋክ ጭፍጨፋ ተፋራጆች የቀድሞ የክልሉ ፕ/ት ስርዓቱን ለመጣል እታገላለሁ ከማለታቸው በፊት ከዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍ/ር ቤት ሊቀርቡ ይገባል አሉ
በምዕራባውያን የሚደገፈው የኢትዮጵያው አገዛዝ የዜጎችን መሬት እየነጠቀ ሰብዓዊ መብት ጥሰት እንደሚፈጽም የኬኒያው ኔሽን ዘገበ
ሌሎችም ዜናዎች አሉ