(ዘ-ሐበሻ) የዘ-ሐበሻ የአዲስ አበባ ዘጋቢዎች እንደሚናገሩት ከሆነ የዘንድሮው አዲስ ዓመት በዓል ገበያን የዋጋ ውድነቱ አቀዝቅዞታል። በአዲስ አበባ የተለያዩ የገበያ ቦታዎች እየተዟዟሩ ገበያውን የተመለከቱት ዘጋቢዎቻችን እንደሚሉት አንድ ከትንሽ ትልቅ በግ ከ1500 እስከ 3000 ብር ድረስ የሚሸጥ ሲሆን ዶሮ ከ150 ብር እስከ 200 ብር ድረስ እንደሚሸጥ ዘግበዋል።
ቂቤ እስከ 180 ብር ድረስ እየተሸጠ እንደሚገኝ የነገሩን ዘጋቢዎቻችን ሽንኩርት በኪሎ ከ12 ብር ጀምሮ ይሸጣል ብለዋል። ቲማቲም በኪሉ ከ12 ብር ጀምሮ ዘይት በሊትር ከ60 ብር ጀምሮ የሚሸጡ ሲሆን የቃሪያ ገበያ በእጅጉ እንደናረ ነግረውናል። 5 ፍሬ ቃሪያ እስከ 5 ብር ድረስ እንደሚሸጥ የዘገቡት የዘ-ሐበሻ ወኪሎች ለወጥ የሚሆን ሥጋ በኪሎ ከ120 ብር ጀምሮ፣ ለቁርጥ የሚሆን ሥጋ ከ200 ብር ጀምሮ እንደሚሸጥ ዘግበዋል። በተጨማሪም ፍየል ከ5 ሺህ ብር ጀምሮ የሚሸጥ ሲሆን ምስር ክክ በኪሎ ከ30 ብር ጀምሮ ይሸጣል ብለውናል።
↧
የአመት በዓል ገበያ በአዲስ አበባ – (የዶሮ፣ የበግ፣ የሽንኩርት፣ የቂቤ…. ዋጋዎችን ይዘናል)
↧