አቤ ቶኮቻው
አንጀሊና ጆሊ ኢትዮጵያ ውስጥ የሰራችው ”ድፍረት” ፊልም በፖሊሶች ድፈረት በርካታ ”ትላልቅ” እንግዶች በተገኙበት ሊመረቅ ሲል ታገደ፤ አርቲስቶች አዝነዋል እኛም የጥንቸሏን ተረት አስታውሰናል…
ሜሮን ጌትነት በመሪ ተዋናይነት ሰርታበታለች የተባለው ይህ ፊልም የታገደው በፖሊሶች ቀጭን ትዛዝ ነው። በርካታ አርቲስቶች የዚህ አይነት ነገር ሲያጋጥማቸው ለመጀመሪያ ግዜ መሆኑን ተናግረዋል። እኛ ግን የነጻ ጋዜጠኞች ማህበር ስብሰባ ፖሊስ በትኑ ሲል ሰምተን እናውቃልን እና፣ የተቃዋሚ ፓርቲዎችን ሰብሰባዎች ከተሰበሰቡ በኋላ ብዙ ጊዜ አምቦውሃው መንግስታችን ሲበትነው አየተናልና፣ የባለራዕይ ወጣቶችን ሰላማዊ ስብሰባ በተደጋጋሚ ያለምንም ሀጋዊ ከለላ ሲያገደው አየተናልና… የዳዊት ጸጋዬ ቲያትር ማስመረቂያ አጥቶ ከሰማያዊ ፓርቲዎች ጋር ቦታ ፍለጋ ሲነከራተት መሰንበቱን እናውቃለነና ኧረ ስንቱ…
(በነገራችን ላይ ዘ ዲክታተር የተባለው አስቂኝ ፊልም እንኳ፤ ባንድ ወቅት ርሳቸው ሬሳ ከመሆናቸው በፊት…(ውይ እኔ ደግሞ አንዳንዴ አበዛዋለሁ አቶ መለስ ”ከመሰዋታቸው” በፊት ማለቴ ነው… እና ያኔ ታግዶ ነበር።) ይሄንን ሁሉ ያልሰሙ አርቲስቶች ዛሬ ተደነቁ እንጂ መንግስታችን ማገድ ብርቁ አይደለም።
የጥንቸሏ ተረት ምን መሰላችሁ…
ዝሆን እና ጥንቸል ሲኒማ ቤት ተገናኙ አሉ፤ ከዛ ዝሆን ሆዬ ከጥንቸል ፊት ሄዱ ቁጭ ብሎ ከለላት አይገልጸውም…(ከፊልም ቤት አስወጣት ብንል ይሻላል…ሃሃ) እና ታድያ ጥንⶨሊት ዝሆንን በቡጢ እየደበደበች በሹክሹክታ ”እረ በናትህ ዝሆን አይደብርህም እንዴ ከለልከኝ እኮ…” እያለች ብትወተውት ብትወተውት አለሰማ አላት… (ዝሆን እኮ ጆሮው ትልቅ ነው እንጂ በተልቁ አይሰማም… ) ከዛ ብዚህ የተበሳጨችው ጥንቸል ከፊት ለፊቱ ሄዳ ቁጭ አለች እና ፊልሟን ኮመኮመች በማብቂያው ላይ ዞር ብላ ”አየህ አይደል የመከለል ነገር እንዴት እንደሚያበሳጭ” አለችው አሉ…
አርቲስቶቻችን የመታገን ነገር አያችሁት አየደል እንዴት እንደሚያበሳጭ… በፊልም እና ድራማ ስራ ተወጥራችሁ ልብ አላላችሁትም እንጂ እናንተ ላይ ሀዝቡ ላይ የደረሰው እገታ ዝሆኑ ጥንቸሏን ሲከልላት የነበረው አይነት ነው…!
ይሄንን እና ሌሎች እገታዎችን ለመቃወም እና መጪው አመት ብሩህ እንዲሆን ለመስበክ ነው#Blackweek ብለን እየዘከርን ያለነው፤
ለማንኛውም እንሆ ፊልሙ በፖሊስ ቀጭን ትዛዝ ሲታገድ የሚያሳይ ቪዲዮ!
Abe Tokichaw