Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Health: በሴቶች ላይ በብዛት የሚከሰተው የኩላሊት ኢንፌክሽን

$
0
0

በሊሊ ሞገስ

በሀገራችን እንደ ቀላል በሽ የሚታዩ፣ ሆኖም ቀስ በቀስ ለተወሳሰበ የጤና ችግር አልፎ ተርፎም ለሞት የሚደርጉ ብዙ በሽታዎች ያሉ ሲሆን፣ የኩላሊት ኢንፌክሽን ከእነዚህ ትኩረት ከማይሰጣቸው አደገኛ በሽታዎች ውስጥ ይመደባል፡፡ የኩላሊት ኢንፌክሽን ኩላሊታችንን ከጥቅም ውጪ ሊያደርገው የሚችል ስለሆነ ማንኛውም ታማሚ ከፍተኛ የሆነ ክትትል በማድረግ ለበሽታው መፍትሄ ማግኘት ይገባዋል፡፡ ከፍተኛ ህክምና ያልተሰጠው ወይም ክትትል ያልተደረገበት የኩላሊት ኢንፌክሽን ለከፍተኛ ስቃይ የሚዳርግ ኢንፌክሽን ከማስከተሉ በተጨማሪ በደም ቧንቧችን በመሰራጨት ለአደገኛ ጉዳት ይዳርጋል፡፡
የኩላሊት ኢንፌክሽን ማለት በሽንት ቧንቧ ላይ በሚደርስ ችግር የሚከሰት ህመም ሲሆን፣ ይህ በኩላሊት አካባቢ የሚገኘው የሽንት መሽኛ ቧንቧ ጉዳት በሚደርስበት ወቅት ህመሙ ይከሰታል፡፡ የሽንት ቧንቧ ከፊኛ እስከ ኩላሊት ድረስ ተዘርግቶ የሚገኝ ሲሆን ባክቴሪ ወደ ቧንቧው አልፎ በሚገባበት ወቅት ሰዎች ለኩላሊት ኢንፌክሽን ይጋለጣሉ፡፡ ኩላሊት ኢንፌክሽን የሚያመጣው ባክቴሪያ ወደ ሽንት ቧንቧ ከገባ በኋላ ለጥቂት ጊዜ ራሳቸውን በማራባት በሽታው በቶሎ እንዲባባስ ያደርገዋል፡፡ የበሽታው ባክቴሪያ ከተለያዩ የሰውነት ክፍሎች የሚመጡ ሲሆን፣ ይህም የሰውነት ክፍል በባክቴሪያ ምክንያት በኢንፌክሽን የተጠቃ ይሆናል፡፡ ባክቴሪያው ወደ ፊኛችን ከመሰራጨት አልፎ ወደ ኩላሊታችን በመዝለቅ የኩላሊት ኢንፌክሽን ያስከትላል፡፡ ከዚህ ውጪም በአርቴፊሻል የሰውነት አካል ምክንያት እንዲሁ አልፎ አልፎ በቀዶ ጥገና ወቅት በሽታው ሲከሰት ይስተዋላል፡፡
kedney infaction and women
የኩላሊት ኢንፌክሽን በተለያዩ ምክንያቶች ሊባባስ ወይም ሊቀሰቀስ ይችላል፤ ከእነዚህም ውስጥ የሴቶች የሰውት ቅርፅ አቀማመጥ፣ የኩላሊት ጠጠር፣ የሽንት ቧንቧ መዘጋት የመሳሰሉት በዋነኝነት ይጠቀሳሉ፡፡ ጾታ በኩላሊት ኢንፌክሽን ህመም ላይ የራሱ የሆነ ተፅዕኖ አለው፡፡ በዚሁ ምክንያት ሴቶች ከወንዶች የበለጠ በኩላሊት ኢንፌክሽን ህመም የመጠቃት ወይም የመያዝ እድላቸው ከፍተኛ ነው፡፡ ይህም የሚሆንበት ዋናው ምክንያት ደግሞ የሴቶች ሽንት ቱቦ ከወንዶች ጋር ሲነፃፀር በጣም አጭር በመሆኑ ነው፡፡ ይህ አጭር ቁመት ባለው የሽንት ቧንቧ ወደ ፊኛ ለመድረስ ጥቂት ጊዜ ብቻ እንዲጓዝ ያደርገዋል፡፡

በሴቶች የሽንት ቧንቧ በብርቶችና በመቀመጫ መካከል ከፍተኛ ቅርበት በመኖሩ ባክቴሪያ ወደ ፊኛ በቶሎ እንዲገባ ያደርጋል፡፡ በዚህም ምክንያት በሽታው ከወንዱ ይልቅ ሴቶች ላይ ያለው ተጋላጭነት ያመዝናል፡፡ ሌላው ለኩላሊት ኢንፌክሽን የሚያጋልጥ ነገር የሽንት ቧንቧ መዘጋት ነው፡፡ ማንኛውም ነገር የሽንት ቧንቧን ሊዘጋ እንደሚችል ጥናቶች ይጠቁማሉ፡፡ ይህ ቱቦ በሚዘጋበት ወቅት የሽንት ጉዞን ይገታል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ሽንትን ሙሉ በሙሉ ከፊኛ እንዳይወጣ ያግዳል፡፡ ይህ ታዲያ ኩላሊታችንን ለኢንፌክሽን ሊያጋልጠው ይችላል፡፡ የሽንት ቧንቧ ቅርፅ ትክክል አለመሆን የመሳሰሉት ችግሮችም የኩላሊት ኢንፌክሽንን ሲያፋጥኑ፣ የተዳከመ የበሽታ መከላከያ ህዋስ መኖር ኩላሊትን ለኢንፌክሽን ያጋልጠዋል፡፡ እንደሚታወቁት አንዳንድ ህመሞች የበሽታ መከላከያ ህዋስን ያዳክማሉ፡፡ ለምሳሌ ካንሰር፣ ስኳር፣ ኤች.አይ.ቪ ዋነኞቹ የበሽ መከላከያ ህዋስን በማዳከም የሚታወቁ ናቸው፡፡ በእነዚህ ችግሮች ምክንያትም የኩላሊት ኢንፌክሽን ሊባባስ ይችላል፡፡

የኩላሊት ኢንፌክሽን እንደማንኛውም በሽታ የራሱ የሆነ የታወቁ ምልክቶች ያሉት ሲሆን በዋነኝነት ትኩሳት፣ የጎን ህመም፣ የሆድ ህመም፣ በተደጋጋሚ ሽነት መሽናት፣ ሽንት በሚሸናበት ወቅት ቃጠሎ፣ እንዲሁም ከሽንት ጋር የሚወጣ ደም ይጠቀሳሉ፡፡ የኢንፌክሽኑ ምልክት ከዕድሜ እና ከፆታ አኳያ የሚለያ ሲሆን በዕድሜ ሲታይ በታዳጊ ህፃናት ላይ በሽታው ሲከሰት በዋነኝነት ምልክቶቹ የሚሆኑት ተቅማጥ፣ የምግብ ፍላጎት መቀነስ፣ ማቅለሽለሽ፣ ማስመለስ፣ ራስ ምታት የመሳሰሉት ናቸው፡፡ በወጣቶች ደግሞ የበሽታው ዋና ምልክት የሆድ ህመም፣ ከደም ጋር የተቀላቀለ ሽንት፣ ሽንት ቢመጣም ለመሽናት አለመቻል በዋነኝነት ሊጠቀሱ ይችላሉ፡፡ እነዚህ የተጠቀሱትን ምልክቶች በማስተዋል ወደ ሐኪም መሄድ መልካም አማራጭ ነው፡፡ በሽታውን ከታከሙ በኋላም ዳግም ምልክቱ ከታየም ወደ ሆስፒታል በመሄድ የበለጠ ሕክምና መውሰድ አስፈላጊ ነው፡፡ ምክንያቱ ደግሞ የኩላሊት ኢንፌክሽን ከፍተኛ ደረጃ ከደረሰ ወደ ተወሳሰበ የጤና ችግር ሊያደርስ ስለሚችል ነው፡፡
kidney infection causes
ሰዎች በሚታመሙበት ወቅት የሰው ሰራሽ ሽንት መሽኛ ሲገጠምላቸው እንመለከታለን፡፡ ይህ ሰው ሰራሽ መሽኛ ምንም እንኳን ጠቃሚ ቢሆንም ለብዙ ጊዜ በተከታታይ በሽተኛው ከተጠቀመ ግን ሌላ የጤና ችግር ይዞ ሊመጣ ይችላል፡፡ ቱቦው በሰዎች ላይ ለብዙ ጊዜ የሚቆይ ከሆነ ለባክቴሪያ ተጋላጭ ከመሆኑም በላይ፣ ባክቴሪው ደግሞ ለኩላሊት ኢንፌክሽን ሊያጋልጥ ይችላል፡፡ ሽንት ከፊኛ ተነስቶ ወደ ሌላ አቅጣጫ መጓዝ ሌላው የኩላሊትን ኢንፌክሽን የሚያመጣ ምክንያት ነው፡፡ ጥቂት መጠን ያለው ሽንት ከፊኛ ወጥቶ መልሶ ወደ ኩላሊት ወይም ወደ ቱቦ መመለስ ለበሽታው አጋላጭ ይሆናል፡፡ ኩላሊት በሰውነታችን ውስጥ ያለውን ቆሻሻ ደም በማጣራት ወደ ሰርኩሌሽን እንዲመለስ ያደርጋል፡፡ በዚህ ወቅት አንድ ሰው በኩላሊት ኢንፌክሽን የተጋለጠ ከሆነ ኩላሊት ውስጥ ለመጣራት የሚመጣው ደም በባክቴሪያ እንዲበከል ያደርገዋል፡፡ ይህም በሰውነታችን የሚሰራጨው ደም ላይ ችግር ይፈጥራል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በወቅቱ ህክምና ያላገኘ የኩላሊት ኢንፌክሽን ሴቶች ልጅ በሚወልዱበት ወቅት እንዲቸገሩ ያደርጋል፡፡ የሚወለደው ልጅ ኪሎው ትንሽና ጤነኛ እንዳይሆን ሊያደርግም ይችላል፡፡

ማንም ሰው የተለያዩ ደረጃዎችን የጠበቁ ህክምናዎችን በመውሰድ ራሱን ከኩላሊት ኢንፌክሽን መጠበቅ እንደሚችል ጥናቶች ያስረዳሉ፡፡ በእርግጥ ኩላሊት የራሱ የሆነ ምርመራ በላብራቶሪ የሚደረግለት ቢሆንም ያልተጠናከረ ወይም ያልተወሳሰበ የኩላሊት ኢንፌክሽን በምልክቶቹ ብቻ መታወቅ የሚቻል ሲሆን፣ እነዚህን ምልክቶች በመንተራስ ህክምና ማግኘት ይችላል፡፡ በምልክት ብቻ ለታወቀ የኩላሊት ኢንፌክሽን ህመም የተለያዩ አንቲባዮቲክ መድሃኒቶች የሚታዘዙ ሲሆን፤ መድሃኒቶቹም ለአጭር ጊዜ የሚወሰዱና በአፋጣኝ የሚያድኑ ናቸው፡፡ ህመሙ ሳይጠናከር ወደ ሆስፒታል መምጣት ከቻሉ ሰዎች መካከል ከ50 ፐርሰንት በላይ በጥቂት ቀን ውስጥ ያለ ተጨማሪ ህክምና ለመዳን ችለዋ፡፡ ያልጠነከረ ወይም ያልተዋሰበን ኢንፌክሽን ትራይሞቶፍሪም እና ሲልፋሜታክሳዝል የተባሉትን መድሃኒቶች በመውሰድ ብቻ መፈወስ ይቻላል፡፡

ጥናቶች እንደሚጠቁሙት ከሆነ ጡት ማጥባት በከፍተኛ ሁኔታ ህፃናቶች ለኢንፌክሽን እንዳይጋለጡ ማድረግ ሲችል፣ ሌሎችም በርከት ያሉ ቅድመ የመከላከያ መንገዶች ከጤና ባለሙያዎች ይሰጣሉ፡፡ በእርግጥ የመከላከያ መንገዶቹ መቶ በመቶ በሽታውን የሚያመጣው ባክቴሪያ እንዳይከሰት የማድረግ አቅም ባይኖራቸውም እንዳይጠናከር ግን አስተዋፅኦ ያደርጋሉ፡፡ ለአብነት በሽተኞች በየቀኑ የሚወስዱትን ፈሳሽ በከፍተኛ ሁኔታ መጨመር ይገባቸዋል፡፡ ውሃን በከፍተኛ መጠን በየቀኑ መጠታት ኢንፌክሽኑን ይከላከላል፡፡ በከፍተኛ ሁኔታ ፈሳሽ መውሰድ ሽንት ቶሎ ቶሎ እንዲመጣ ሲያደርግ ከሽንት ጋርም ባክቴሪያዎች አብረው በቆሻሻ መልክ እንዲወገዱ ያደርጋል፡፡ ውሃ በብዛት መጠጣት ሽንትን እንደፈለጉ እንዲቋጥሩ አያስችልም፡፡ ሽንት መቋጠር ባክቴሪያ እንዲከማች የሚያደርግ ሲሆን፣ ብዙ ውሃ የሚጠጣ ከሆነ ግን ይህን ማድረግ አያስችልም፡፡ ስለዚህም በቱቦ የሚከማቹት ባክቴሪያዎች እንዲወጡ ይገደዳሉ፡፡ አንዳንድ ባለሙያዎች ጁስ መጠጣት በጣም ጠቃሚ መሆኑን የሚናገሩ ሲሆን፤ ይህ የሆነው ግን መድሃኒት በሚዋጥበት ወቅት መሆን እንደማይገባው ያስረዳሉ፡፡

የግል ንፅህናን መጠበቅ ወይም በፊት ከነበረው የንፅህና አጠባበቅ የተሻለ የንፅህና አጠባበቅ መከተል ሌላው ህመሙን የመከላከያ መንገድ ነው፡፡ ሽንት ከተሸና በኋላ መታጠብ ተገቢ መሆኑን ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡ የብልትን አካል ማጠብ ባክቴሪያ በብልት ወይም በሴት ማህፀን በኩል ወደ ኩላሊት እንዳይገባ ይከላከላል፡፡ የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን ፆታዊ ግንኙነትን ተከትሎ የመከሰት ዕድሉም የሰፋ ነው፡፡ ምክንያቱም ከግንኙነት በኋላ ባክቴሪያው ወደ ቱቦው በቀላሉ ሊገባ ስለሚችል ነው፡፡ ስለዚህም ከግንኙነት በኋላ በአስቸኳይ ሽንት መሽናት ተገቢ ሲሆን ይህን ማድረግ ባክቴሪያው ከሽንት ጋር አብሮ እንዲወጣ ያደርጋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ከግንኙነት በፊት ብልትን ማፅዳት የማስፈለጉን ያህል ሽቶና ዲዮደራንት የመሳሰሉትን ኬሚካል ያላቸውን ቅባቶች በብልት አካባቢ ፈፅሞ መጠቀም አያስፈልግም፡፡

የኩላሊት ኢንፌክሽን በተለያየ ደረጃ ህክምናው የሚሰጥ ሲሆን፣ ከቀላል ህክምና እስከ አልጋ ማስያዝ ያደርሳል፡፡ ቀላሉ ያልተወሳሰበ የኩላሊት ኢንፌክሽን ችግር በአንቲባዮቲክ እንደሚድን ሁሉ የተወሳሰበና ቶሎ ህክምና ያላገኘ ህመም ሆስፒታል እስከማስተኛት ለከፋ ችግር ያደርሳል፡፡ አደገኛ ደረጃ የደረሰ የኩላሊት ኢንፌክሽን ህመም በማንኛውም ሐኪም ሳይሆን ከፍተኛ ክትትል ስለሚያስፈልገው በስፔሻሊስቶች መታየት ይገባል፡፡ በይበልጥ ዳግም እንደገና ለተነሳ (ላገረሸ) የኩላሊት ኢንፌክሽን ህመም ከፍተኛ ክትትል ስለሚያስፈልግ ወደ ስፔሻሊስት በመሄድ ማማከር ጠቃሚ መሆኑን የህክምና ባለሙያዎች ያስረዳሉ፡፡ የከፋ ኩላሊት ኢንፌክሽን እስከ ኦፕራሲዮን ሊያደርስም ይችላል፡፡

የኩላሊት ኢንፌክሽን ከወንዶች ይልቅ ሴቶች ላይ በብዛት የሚከሰት ሲሆን በርካታ ሴቶች ቢያንስ ቀላል የኩላሊት ኢንፌክሽን በወጣትነት ጊዜያቸው ሊያጋጥማቸው እንደሚችል ጥናቶች ይጠቁማሉ፡፡ ወንዶች ከሴቶች ጋር ሲነፃፀሩ በኢንፌክሽን የመያዝ ዕድላቸው ከፍተኛ ከመሆኑ በተጨማሪ ወጣት ወንዶች ከ50 ዓመት በላይ ካሉ ወንዶች ጋር ሲነፃፀር የመያዝ ዕድላቸው ዝቅተኛ ነው፡፡ በወንዶች ላይ በኢንፌክሽኑ የመያዝ ዕድሉ ሲሰፋ የሚስተዋለው ዕድሜያቸው ከ50 ዓመት በላይ ባሉት ላይ ነው፡፡ በሰለጠኑ ሀገራት ህመሙ በወጣት ተማሪዎች ላይ እየጨመረ ሲገኝ፣ ሴቶች ተማሪዎች ከወንድ ተማሪዎች የበለጠ እየተጠቁ ይገኛሉ፡፡ በትምህርት ቆይታቸው ወቅት ቢያንስ ከአምስት ሴቶች አንዷ በኩላሊት ኢንፌክሽን እንደምትጠቃም ተገልጿል፡፡

Zehabesha.com


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>