Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Health: የዘር ፈሳሼን ቶሎ ማፍሰስ /Premature Ejaculation/ የትዳሬን መፍረስ ምክንያት ሊሆን ደርሷል፤ እባካችሁ እርዱኝ (የዶ/ሩ ምላሽ)

$
0
0

እባካችሁ የዘር ፈሳሼን ቶሎ የመጨረስ ወይም የወሲብ ፈሳሽ ቶሎ የማፍሰስ ችግር አለብኝ እና በዚህ ምክንያት ትዳሬም ሊፈርስ ነው፡፡ እኔም በከፍተኛ ችግር ውስጥ ነኝ ከአሁን ከአሁን ይሻላል ብልም ያተረፍኩት ልክ እንደ ሩጫ ውድድር በየጊዜው የቀድሞውን ሪኮርዴን ማሻሻል ብቻ ነው፡፡ ምን ይሻለኛል ከጉድ አውጡኝ፡፡
እውን አበበ

Premature Ejaculation 1
ብዙ ወንዶች አንዳንድ ጊዜ ራሳቸውን ወይም የወሲብ ጓደኛቸውን ከምትፈልገው ቀደም ብለው ሊጨርሱ/Ejaculate/ ይችላሉ፡፡ አንዳንዴ ብቻ ከተከሰተ ብዙም የሚያሳስብ ችግር አይደለም፡፡ ነገር ግን በተደጋጋሚ ወይም ሁልጊዜ የሚከሰት ከሆነ እንደ ጠያቂያችን አቶ እውን አበበ በህክምና ቋንቋ ፕሪ ማቹር ኢጃኩሌሽን/premature ejaculation/ ወይም ወቅቱን ያልጠበቀ እርካታ ችግር አለ ማለት ነው፡፡

ወቅቱን ያልጠበቀ እርካታ/ማፍሰስ/ በጣም በስፋት የሚታይ የወሲብ ችግር ነው፡፡ ግምቱ ቢለያይም ከሶስት ወንዶች መካከል አንዱ የዚህ ችግር ተጠቂ እንደሆነ ጥናቶች ይጠቁማሉ፡፡ ምንም እንኳን ብዙ ወንዶች አፍረት ስለሚሰማቸው ስለዚህ ችግር ከሐኪሞቻቸው ጋር አይነጋገሩም፡፡
በፊት በፊት ይህ ችግር የሳይኮሎጂ ችግር ብቻ ተደርጎ ይታይ ነበር፡፡ አሁን አሁን ግን የውስጥ ችግርም የዚህ ችግር ምንጭ እንደሆነ ጥናቶች ጠቁመዋል፡፡ በአንዳንድ ወንዶች ይህ ችግር በብልት መነሳሳት ችግር ምክንያት እንደሚመጣም ታውቋል፡፡
አንድ ወንድ ለማፍሰስ ምን ያክል ጊዜ መውሰድ አለበት የሚል የወጣ ስታንዳርድ በህክምና የለም፡፡ ነገር ግን የዚህ ችግር ዋናው ምልክት ሁለቱ የወሲብ ጓደኞች ከሚፈልጉት በፊት የሚከሰትና ለሁለቱ አሳሳቢ ሆኖ ሲገኝ ነው፡፡ ይህ ችግር በማንኛውም የወሲብ ጨዋታዎች ሊከሰት ይችላል ማለትም ራስን በማዝናናት ወይም ከወሲብ ጓደኛ ጋር በሚደረግ መዝናናት ወቅትም ሊከሰት ይችላል፡፡

በህክምና ይህ ችግር ፕራይመሪ ፕሪማቹር ኢጃኩሌሽን/Primary premature ejaculation/ ሲባል ይህ ማለት አንድ ሰው ወሲብ ከጀመረ ጊዜ ጀምሮ ይህ ችግር የሚታይበት ሲሆን ነው፡፡
ሌላው አይነት ደግሞ ሰከንደሪ ፕሪማቹር ኢጃኩሌሽ Secondary Primary premature ejaculation ሲባል በፊት ጥሩ የወሲብ ሁኔታ ያለው ወንድ የኋላ ኋላ የመጣ ቶሎ የማፍሰስ ችግር ሲገጥመው ማለት ነው፡፡
የዚህ ችግር መንስኤ ገና እየተጠና ሲሆን በፊት በፊት የሳይኮሎጂ ችግር ብቻ ነው ተብሎ ሲታሰብ የቆየ ሲሆን አሁን ግን መንስኤው ውስብስብና የሳይኮሎጂክና የአካላዊ /ባየሎለጂካላዊ/ ችግሮች ጋር በጥምረት የመጡት ችግሮች ነው፡፡ ወደዚህ መላምት በመግባት አንባቢን ግራ ከማጋባት እቆጠባለሁ፡፡
በርካታ ሁኔታዎች የዚህን ችግር መከሰት ያባብሳሉ፡፡ ከዚህም ውስጥ የወሲብ አካል አለመነቃቃት ለምሳሌ የተነቃቀው የወሲብ አካል ሊቀዘቅዝ ይችላል ብሎ ከመስጋት ቶሎ ወደ መጨረስ መሯሯጥ ሊከሰት ይችላል፡፡ ቶሎ የማፍሰስ ችግር ካላቸው ሶስት ሰዎች መካከል አንዱ የወሲብ ንቃታቸውን እንዲነቃቃ ማቆየት ያቅታቸዋል፡፡ በግብረ ስጋ ግንኙነት ጊዜ ችግር ይፈጠራል ተብሎ የሚገመት በሽታ ለምሳሌ የልብ በሽታ ችግሩ ያለበት ሰው ተጣድፎ የመጨረሽ አዝማሚያ ሊያሳይ ይችላል፡፡ የአዕምሮ መዳከም ወይም ጭንቀት ቶሎ ለማፍሰስ ሊያጋልጥ ይችላል፡፡ ይህም በግብረ ስጋ ግንኙነት ጊዜ ዘና ብሎ ተመስጦ መተግበርን በመቀነስ ነው፡፡ አንዳንድ መድሃኒቶችም ለዚህ ሊያጋልጡ ይችላሉ፡፡

ሐኪም ጋር ሲቀርብ ሐኪሙ የተሟላ የግብረ ስጋ ግንኙነት ታሪክ ሊያስፈልጋቸው ይችላል፡፡ አካላዊ ችግር የለም ብለው ሊያስፈልጋቸው ይችላል፡፡ አካላዊ ችግር የለም ብለው ከገመቱ ወይም የሳይኮሎጂ ችግሩን ድርሻ ለማወቅ ከፈለጉ በዚህ ችግር ላይ ሰፋ ያለ ግንዛቤ ወዳላቸው ባለሙያዎች ተጨማሪ ትንተና ለማግኘት ሊልኩዎት ይችላሉ፡፡ ሌሎችም ምርጫዎች ሊያዙ ይችላሉ፡፡

በዚህ ችግር ማለትም ቶሎ በማፍሰስ ችግር ምክንያት እንኳን ሌላ የጤና ችግር ባይመጣም በግል ህይወት ውስጥ ጭንቀት ይፈጠራል፡፡ ዋና ዋና የዚህ ህመም ተጓዳኝ ችግሮች በትዳር ላይ ልክ ጠያቂያችን ያስቀመጡት አይነት ጭንቀት መከሰት ሊሆን ይችላል፡፡ በዚህ ጊዜ ለህክምና ሲመጡ ከባለቤትዎ ወይም ከወሲብ አጋርዎ ጋር ቢመጡ ጠቀሜታው የጎላ ነው፡፡

ቶሎ የማፍሰስ ችግር አንዳንድ ጊዜ የመውለድ ችግር ሊፈጥር ይችላል፡፡ ስለዚህ ቶሎ የማፍሰስ ችግሩ ካልተቀረፈ ምን አልባት ለመውለድ ሌላ የህክምና ዘዴ ሊያስፈልግ ይችላል፡፡
የዚህ ችግር ህክምና በሶስት ዘርፎች ይመደባል፡፡ እነዚህም ሴክሽዋል ቴራፒ፣ የመድሃኒት ህክምና፣ እና የሳይኮ ቴራፒ ናቸው፡፡

የመድሃኒት ህክምናው የድብርት መድሃኒት በመስጠት የዚህ የድብርት መድሃኒት የጎንዮሽ ጉዳት ዘግይቶ ማፍሰስ ስለሆነ ከጎንዮሽ ጉዳቱ ተጠቃሚ ለመሆን የታቀደ ነው፡፡ ነገር ግን እነዚህ መድሃኒቶችም ሌሎች ተጨማሪ የጎንዮሽ ጉዳቶች አላቸው፡፡ ሌላው መድሃኒት በብልት ላይ የማደንዘዣ ክሬም በመቀባት ስሜቱን በመቀነስ ቶሎ ማፍሰስን ለመዘግየት የሚሞክር ነው፡፡ ባይኮቴራፒው ከሳኮቴራፒስት ጋር በማውራት ጭንቀት በመቀነስ የሚሰራ ነው፡፡ አብዛኛው ባልትዳሮች ሁለቱም አብረው ሲኖሩ የተሻለ ውጤት አለው፡፡ ይህም በመካከላቸው ስለ ችግሩ በግልፅ ማውራትን እድል ይፈጥራል፡፡
የሴክሽዋል ቴራፒ/Sexual therapy/ ለምሳሌ ከግንኙነት በፊት አንድ ወይም ሁለት ሰዓት ቀደም ብሎ ማስተርቤት ማድረግ/ራስን አዝናንቶ መጨረስ/ ወይም ለረጅም ጊዜ ግንኙነት ሲያደርጉ በሌላ አይነት የወሲብ ጨዋታዎች ላይ ፎከስ በማድረግ በዋናው የወሲብ ግንኙነት ላይ ያለውን ጫና መቀነስ፡፡

ሌላው ጠቃሚው መንገድ የመጭመቅ ዘዴ ይባላል ሐኪምዎ ይህንን ዘዴ እንዲጠቀም ሊመክሩዎት ይችላሉ፡፡ አሰራሩ እንደሚከተለው ነው፡፡

ደረጃ አንድ፡- የግብረ ስጋ ግንኙነት ጨዋታ መጀመር/በተለመደው አኳኋን/ ይህ ብልትን በእጅ ማነሳሳትን ይጨምራል እስከ ፈሳሽ መምጫ ድረስ ይቀጥላል፡፡
ደረጃ ሁለት፡- የወሲብ ጓደኛህ ከማፍሰስህ በፊት በእጇ ክርክሩ ላይ ለበርካታ ሰከንዶች እንድትይዘውና የማፍሰስ ፍላጎቱ እስኪሞት በዛው መቀጠል፡፡
ደረጃ ሶስት፡- ጓደኛህ ጭምቅ አርጋ የያዘችውን ትልቀቀውና ለ30 ሰከንዶች መቆየት ከዚያም ወደ ጨዋታው መግባት በጨመቀው ቁጥር ደግሞ ያለው በድጋሚ የወሲብ ጨዋታ ወይም ማነሳሳት በድጋሚ ይነቃቃል፡፡
ደረጃ አራት፡- አሁንም የማፍሰስ ስሜት ሲመጣ የወሲብ ጓደኛህ በድጋሚ ክርክሩ ላይ ጨምቃ እንድትይዘው ማድረግ፡፡
ይህንን ቴክኒክ ደጋግሞ በማድረግ ከጓደኛ ጋር በሚደረግ ትክክለኛው ወሲብ ጊዜ ወዲያው ማፍሰስ ይቀርና አዲስ የመቆየት ልማድ ይፈጠራል፡፡ ይህንን ደጋግሞ ለብዙ ጊዜ ሳይታክቱ በማድረግ ይህንን ችግር ለመፈታት ይቻላል፡፡ መልካም ዕድል፡፡ መልካም የትዳር እና የወሲብ ዘመን፡፡


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>