Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

ፍትህ ሚ/ር በጋዜጠኞች ላይ የጀመረውን ዘመቻ ቀጠለ፤ አፍሮ ታይምስና ጋዜጠኛ ቶማስ አያሌው የክስ ቻርጅ ደረሳቸው (ክሱን ይዘነዋል)

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) ለአዲስ ጉዳይ መጽሔት አዘጋጆች መሰደድ ምክንያት የሆነው የፍትህ ሚ/ር ጋዜጠኞችን ሰዶ የማሳደድ ዘመቻ ቀጥሎ በትናንናው ዕለት ሎሚ መጽሔት እና ጋዜጠኛ ግዛው ታዬ የክስ ቻርጅ የደረሳቸው መሆኑን ዘ-ሐበሻ መዘገቧ አይዘነጋም። ዛሬ በደረሰን መረጃ መሰረት የአፍሮ ታይምስ ጋዜጣ አዘጋጅ ጋዜጠኛ ቶማስ አያሌው ከፍትህ ሚ/ር የክስ ቻርጅ ደርሶታል።

ጋዜጠኛ ቶማስ አያሌው

ጋዜጠኛ ቶማስ አያሌው


የፍትህ ሚ\ር በጋዜጠኛውና በአፍሮ ታይምስ አሳታሚ ድርጅት ላይ የመሰረተው ክስ “የሃሰት ወሬዎችን በማሳተም ሕዝብን ለማነሳሳት በማሰብ ሕዝቡ በህገመንግታዊ ሥርዓቱ ላይ አመኔታ እንዳይኖረው፣ ጥርጣሬ እንዲገባው ለማድረግ በማሰብ” የሚል ነው። ጋዜጠኛ ቶማስ የቀረበበት ክስ በሚያዝያ 21 እና 22 2006 በወጣው አፍሮ ታይምስ ጋዜጣ ላይ “ልዩ ሃይሎችና መከላከያ ሠራዊት ተፋጠዋል” በሚለው ዜና ሥር “ቀደም ባሉት ጊዜያት በጋምቤላ ክልል ሰፍሮ የሚገኘው የመከላከያ ሰራዊት የፈለገውን ሰው ሲያስር፣ ሲገድል፣ ሴቶችን አስገድዶ ሲደፍር ቆይቷል። ይህም የሰራዊቱን ስርዓት አልበኝነትና ሕገወጥ ድርጊት ለማስቆም የሞከረ መንግስታዊ አካል አልነበረም።” በሚል በሰፈረው መረጃ ሲሆን ለዚህም ፍትህ ሚ/ር “አገሩንና ህገመንግስቱን በመጠበቅ እንዲሁም በዓለም አቀፍ ሕብረተሰብና መንግስታት መልካም ስነምግባር እያከናወነ ያለውን የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በሕዝቡ ዘንድ አመኔታ እንዲያጣ ጥርጣሬ እንዲገባው ለማድረግ በዋና ወንጀል አድራጊነት ተካፋይ በፈጸሙ ሐሰተኛ ወሬዎችን በመንዛትና ሕዝብን በማነሳሳት ወንጀል ተከሰዋል” ሲል በክስ ቻርጁ ላይ አስፍሯል፡፡

በሃገር ውስጥ የሚታተሙ በርካታ መጽሔቶችን እና ጋዜጦችን እከሳለሁ ሲል የቆየው ፍትህ ሚ/ር ጋዜጠኞችን ለማፈን የሚያደርገውን ተንኮል ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ሲተቹት እንደቆዩ ይታወሳል።

thomas ayalew 1

thomas ayalew 2


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>