Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ሚድሮክ ያቀረበውን የካርታ መምከን አቤቱታ ተቀበለ

$
0
0

•የአዲስ አበባ አስተዳደር የመከነው ካርታ እንዲመለስ አዘዘ

የአዲስ አበባ አስተዳደር ግንባታ ሳይካሄድባቸው ለዓመታት ታጥረው የተቀመጡ ሁለት ቦታዎች ካርታ ማምከኑን የተቃወመው ሚድሮክ፣ ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ያቀረበው አቤቱታ ተቀባይነት ማግኘቱን ምንጮች ገለጹ፡፡

HMDAMUDIየአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሚድሮክ ልማት ለማካሄድ ከዓመታት በፊት ተረክቦ ግንባታ ሳያካሂድ አጥሮ ያስቀመጣቸው ቦታዎች ያሉበትን ሁኔታ በከፍተኛ ባለሙያዎች አስጠንቶ ነበር፡፡ ባለሙያዎቹ በተለይ በልደታ ክፍለ ከተማ ዋቢ ሸበሌ ሆቴል ጎንና በየካ ክፍለ ከተማ በሻሌ ሆቴል አካባቢ የሚገኙት ቦታዎች ምንም ዓይነት ግንባታ ሳይካሄድባቸው ለዓመታት የተቀመጡ በመሆናቸው፣ ካርታቸው እንዲመክን የውሳኔ ሐሳብ አቅርቦ ነበር፡፡ የሁለቱ ቦታዎች ካርታ እንዲመክን የቀረበው የውሳኔ ሐሳብ ተቀባይነት በማግኘቱ ካርታዎቹ በክፍላተ ከተሞቹ መክነዋል፡፡ 

ነገር ግን ሚድሮክ በተወሰደው ዕርምጃ ደስተኛ ባለመሆኑ ምክንያት ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አቤት ብሏል፡፡ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የቀረቡትን የሚድሮክ መቃወሚያ ሐሳቦች መቀበሉን የሚናገሩት ምንጮች፣ የአዲስ አበባ አስተዳደር ያመከነውን ካርታ በድጋሚ እንዲሰጥ መመርያ ማስተላለፉን አስረድተዋል፡፡

ከፍተኛ ባለሙያዎች ተካተውበት የሚድሮክ 11 ቦታዎችን ያጠናው ኮሚቴ፣ ካርታቸው መክኖ የነበረባቸው ሁለቱ ቦታዎች ምንም ግንባታ እንዳልተካሄደባቸው አመልክቷል፡፡ ከእነዚህ ቦታዎች በተጨማሪ ለሸራተን ማስፋፊያ ከሦስት ዓመት በፊት ነዋሪዎች ተነስተው ነፃ የሆነው መሬትም ግንባታ እንዳልተጀመረበት ኮሚቴው በጥናቱ አመልክቷል፡፡ በተወሰነ ደረጃ ፒያሳ የሚገኘውና ካዛንቺስ አካባቢ የሚገኙት ቦታዎች መሠረት ለማውጣት የተወሰነ ሥራ መሠራቱንም የኮሚቴው ሪፖርት ጠቁሟል፡፡ 

በቀረበው የውሳኔ ሐሳብ ላይ ተመሥርቶ የአስተዳደሩ ካቢኔ የማስተማሪያ ዕርምጃ ይወስዳል ተብሎ ሲጠበቅ፣ ሐሳቡን የሚቀለብስ ሥራ መሠራቱ አስገራሚ እንደሆነባቸው የአስተዳደሩ ሠራተኞች ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ 

ኮሚቴው ከሚድሮክ ቦታዎች በተጨማሪ በአዲስ አበባ ከተማ 109 ቦታዎች ያለግንባታ ታጥረው ለዓመታት መቀመጣቸውንና ከእነዚህ ቦታዎች መካከል 56 ያህሉ ዕርምጃ እንዲወስድባቸው የውሳኔ ሐሳብ አቅርቧል፡፡ የውሳኔ ሐሳቡ ከቀረበ በርካታ ወራትን ቢያስቆጥርም ከብዙ መዘግየት በኋላ፣ የከንቲባ ድሪባ ኩማ ካቢኔ በዚህ ሳምንት በውሳኔ ሐሳቡ ላይ ተመሥርቶ የመጨረሻ መመርያ ለመስጠት ፕሮግራም መያዙ ታውቋል፡፡

Source: Ethiopian Reporter


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>