(ቢቢኤን ራድዮ) የህዝበ ሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎች በዛሬው እለት ፍርድ ቤት የቀረቡ ቢሆንም ዳኞች አልተሟሉም በሚል ያልተካሄደ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን ለሁለቱ ዳኞች ግን እየደረሰባቸው ያለውን ነገር አህመድ ሙስጠፋና ኡስታዝ በድሩ ሁሴን በዝርዝር ማስረዳታቸው ታዉቐል፡፡ ቁልፍ ባለው ሰንሰለት በጨለማ ክፍል እንዳሰሩዋቸው ምግብም እንደከለከሏቸው የገለጹ ሲሆን ዳኛውም ይህን ሲሰሙ እንዴት እንደዚህ ይደረጋል በዚህ ዘመን ቀርቶ በአፓርታይድ ጊዜ እንኳን አይፈጸምም ነበር በማለት መኮነናቸው ታዉቐል፡፡ ዳኛውም አያይዘው እንኳን በ21ኛው ክፍለ ዘመን ቀርቶ አስርቱ ትእዛዛት በሚፈጸሙበት ጊዜ እንኳን እንዲህ አይነት ነገሮች አይደረጉም ነበር ማለታቸው ታዉቋል፡፡
ኮሚቴዎቹም አሰቃቂ ስቃይ በሚፈጸምበት በማእከላዊ እንኳን የምግብ ክልከላ እንደማይፈጸምባቸው ተናግረዋል፡፡ ኡስታዝ በድሩ ሁሴን የታሰረበት ሰንሰለት ረዥም ጥልፍልፍ ሲሆን ዙርያ ጥምም በማሰር ቆልፈውበት እንደነበር ገልጾ ካቴናውም የተፈታለት ፍርድ ቤት ሊመጣ ሲል ከ85 ሰአታት እስር በሁላ እንደሆነ ገልጽዋል፡፡
ጠዋት ወደ ፍርድ ቤት ሊመጡ ሲሉ ኮሚቴዎቹ የበድሩ ሰንሰለት ሳይፈታ ይሂድ ለፍርድ ቤት ማሳየት እንፈልጋለን ብለው የነበረ ቢሆንም የማረሚያ ቤቱ ሃላፊ በግዳጅ ሰንሰለቱን ፈተው ወደ ፍርድ ቤት እንዲሄድ እንዳደረጉ ለመረዳት ተችሏል።
↧
በነኡስታዝ በድሩ ሁሴን ላይ የተፈጸመውን ግፍ ”በአፓርታይድ ጊዜ እንኳን ያልተፈጸመ”በማለት ዳኛው መኮነናቸው ታወቀ
↧