ስድስት የአንድነት መራሮች በኣንድነት ፓርቲ ሊቀመንበር ኢንጂነር ግዛቸው የሚመራ ካቤኔ ውስጥ መቀጠላቸው ትርጉመ ቢስ መሆኑን መረዳታቸውን በመግለጽ ለግዛቸው ደብዳቤ ያስገቡት የአንድነት አመራሮች
ተክሌ በቀለ –ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዘዳንት
በላይ ፈቃዱ —ምክትል ፕሬዘዳንት
ሰለሞን ስዮም —የፖለቲካ ጉዳዮች ሃላፊ
ዳንኤል ተፈራ — የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ
ዳዊት አስራደ —የኢኮኖሚ ጉዳዮች
ፀጋየ አላምረው -–የገንዘብ ክፍል ሃላፊ ሀላፊ : ራሳቸውን ከኢንጅነር ግዛቸው ካቢኔ ማግለላቸው ታውቋል።
ኢንጂነር ግዛቸው በአንድነት እና በመኢአድ መካከል የሚደረገውን ውህደት በማኮላሸት ስራ ላይ ከመሰማራታቸውም ሌላ ሰርጎገቦችን እየሰበሰቡ ፓርቲው የሚያደርጋቸውን እንቅስቃሴዎች እያበላሹ መሆኑን አቤቱታዎች ይሰማሉ፡፤እንዲሁም በጀግናው አንዱአለም አራጌ እና በሃብታሙ መታሰር ጋር እንደሚጠረጠሩ እና የአንድነትን እንቅስቃሴ በዘለቀ ረዲ በኩል ለወያኔ ሪፖርት እንደሚያደርጉ በአባላቶቹ አቤቱታ ይቀርብባቸዋል።