Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) ብሔራዊ ምክር ቤት ሁለት ውሳኔዎችን አስተላለፈ

$
0
0

10606470_681304371954500_7184262179990938183_nየአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) ብ/ም/ቤት ነሐሴ 04 ቀን 2006 ዓ.ም የጠራው አስቸኳይ ስብሰባ ሁለት ውሳኔዎችን በማስተላለፍ ስብሰባውን በተሳካ ሁኔታ አካሂዷል፡፡
በዚህም መሰረት ጠዋት የተደረገውን ስብሰባ የመሩት አቶ አበበ አካሉ የም/ቤቱ አፈ ጉባኤ ሲሆኑ፣ ምክር ቤቱ የተወያየበት አጀንዳ የመኢአድና የአንድነት የውህደት ሂደትና የተደረሰበትን ውጤት መርምሮ አቅጣጫ ማስያዝ ሲሆን በተደረገውም ሰፊና ጥልቅ ውይይት
- የምርጫ ቦርድ ለመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) በደንቡና በአዋጁ መሰረት እንዲያሟላቸው የጠየቃቸውን ጉዳዮች እስኪያሟላ ድረስ በአንድነት ፓርቲ ደንብና መመሪያ መሰረት ውህደትን በሚመለከትና አዘጋጅ ኮሚቴ መወከል የብሔራዊ ም/ቤት ሥልጣን በመሆኑ ም/ቤቱ የወከለው የጠቅላላ ጉባኤ አዘጋጅ ኮሚቴ ለጊዜው ስራውን እንዲያቆም ውሳኔ በማስተላለፍ ከመኢአድ ጋር የሚደረገው ውህደት በማንኛውም ጊዜ እንደሚቀጥል አስገንዝበዋል፡፡
- በመቀጠልም የአንድነት ፓርቲ መዋቅራዊ አካላት የሥራ እንቅስቃሴ ወደ ነበረበት እንዲመለስና ከብሔራዊ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ጀምሮ እስከ ዝቅተኛው መዋቅር ድረስ የወጡትን የሥራ ዕቅዶች እንዲያከናውኑ ም/ቤቱ መመሪያ ሰጥቷል፡፡
የከሰዓት በኋላ የም/ቤቱን ውሎ የመሩት የም/ቤቱ ም/አፈ ጉባኤ አቶ ደምሴ መንግሥቱ ሲሆኑ የውይይቱ አጀንዳም የፓርቲው የመገናኛ ብዙኃን እንዲመራ ኃላፊነት የተጣለበት ኤዲቶሪያል ቦርድን በተመለከተ ነበር፡፡
- ም/ቤቱ በተደረገው ውይይት ቀደም ሲል የተቋቋመው ቦርድ በአጠቃላይ የፈጸማቸውን የሥራ ክንውን፣ ጠንካራና ደካማ ጎኖች በተመለከተ ሪፖርት እንዲያዘጋጅና በሚቀርበው ሪፖርት መሰረት ተወያይቶ በአዲስ መልክ የኤዲቶሪያል ቦርድ አባላትን ለማቋቋም ለነሐሴ 18 ቀን 2006 ዓ.ም ቀጠሮ በመያዝ ስብሰባው ተጠናቋል ሲሉ አቶ ደምሴ መንግስቱ የብ/ም/ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ለፍኖተ ነፃነት ገልፀዋል፡፡

Millions of voices for freedom – UDJ


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>