በአዲሳባ እና በመላው ሀገሪቱ ከፍተኛ ተነባቢነት ካላቸው መጽሄቶች ተርታ የምትመደበው አዲስ ጉዳይ አዘጋጆች መሰደዳቸው ተሰማ። መንግስት አዲስ ጉዳይን ጨምሮ በበርካታ ጋዜጦች እና መጽሄቶች ላይ ክስ ሊመሰርት መሆኑ በተሰማ ማግስት ”ምርጫ መጣ ፕሬስ ውጣ” የሚል ጽሁፍ ያስነበበችን አዲስ ነገር ከመታሰር አለመታስር ይሻላል ብላ መሰደድን መርጣለች።
ደረጄ ሀብተወልድ እንደነገረን የመጽሔቱዋን ባለቤት እንዳልካቸው ተስፋዬን ጨምሮ የመጽሔቱዋ ምክትል ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ኢብራሂም ሻፊ፣ ከፍተኛ አጋዘጅ ጋዜጠኛ እንዳለ ተሽ እና አዘጋጅና አምደኛ ሀብታሙ ስዩም በፕሬሶች ላይ እየተንደረደረ በመምጣት ላይ የሚገኘውን የክስ ናዳ ”ሽል” ብለው አምልጠውታል።
በቅርቡም የሰንደቅ ጋዜጣ ከፍተኛ አዘጋጅ የነበረው ዘሪሁን ሙሉጌታ እየደረሰብት ያለውን የደህነነቶች ጭቅጭቅ እና ንትርክ እንዲሁም የእስር እና እንግልት ስጋት ሽሽት ሀገሩን ለአስር አለቆች ትቶ መውጣቱን አለመዘገባችን ይታወቃል። (በቀንፍም እንዲህ እያደራጁ መዘገብ ሳይሻል አይቀርም ብለን በማይቀለደው እንቀልዳለን)
ሰዎቹ ሁሉን አባረው ሲያበቁ የእስር ሱሳቸውን ርስ በርስ በመተሳሰር ይወጡት እንደሁ እናያለን እንግዲህ!