Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

በ5 ዋነኛ መጽሔቶች እና አንድ ጋዜጣ ላይ የወንጀል ክስ ተመሠረተ

$
0
0

በስድስት የግል ፕሬስ ሕትመቶች እና አሳታሚዎቻቸው ላይ የወንጀል ክስ መመሥረቱን መንግስት አስታወቀ፡፡

ክስ የተመሠረተባቸው አምስት መጽሔቶች እና አንድ ጋዜጣ፤ በየጊዜው ህገ መንግስቱንና ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን በሀይል ለመናድ የአመፅ ቅስቀሳና የሀሰት ወሬዎችን በመንዛት ህገ መንግስታዊ ስርዓቱ በሀይል እንዲፈረስ እና ህዝብ በመንግስት ላይ ያለአግባብ አመኔታ እንዲያጣ የሚያደርጉ የወንጀል ተግባራትን በመፈፀም እንደተጠረጠሩ የፍትህ ሚኒስቴር መግለጫ ጠቁሟል፡፡Lomi-magazine-

መግለጫው አክሎ በጥቅሉ ባቀረበው ስሞታ፤ በህገ መንግስቱ የተበጁትን ገደቦች በማን አለበኝነት በመጣስ ስራዬ ብለው ብሄራዊ ደህንነትን አደጋ ላይ በሚጥል መልክ አመፅና ሁከትን የሚቀሰቅሱ፣ አክራሪነትንና ሽብርተኝነትን የሚያወድሱ እንዲሁም የሚያበረታቱ፣ በህዝቡ መሃከል የዘርና የሃይማኖት ጥላቻን የሚቀሰቅሱ፣ የህዝብ መሪዎችንና የተቋማትን መልካም ስምና ዝና በሀሰት የሚያጠፉና የሚወነጅሉ፤ የግል ሕትመት ውጤቶች አሉ ብሏል፡፡

ክስ የተመሠረተባቸው የሕትመት ውጤቶች፡-

* አዲስ ጉዳይ – በሮዝ አሳታሚ ኃ.የተ.የግ.ማህበር አሳታሚነት የሚታተም – ሳምንታዊ መጽሄት፣

* ሎሚ መጽሄት – በዳዲሞስ ኢንተርቴንመንትና እና ፕሬስ ስራዎች ኃ/የተ/የግ/ማ አሳታሚነት የሚታተም – ሳምንታዊ መጽሄት፣

* ዕንቁ መጽሄት – በአለማየሁ ሕትመትና ማስታወቂያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር አሳታሚነት – በየ15 ቀኑ የሚታተም መጽሄት፣

* ፋክት መጽሄት – በዮፋ ኢንተርቴንመንትና ፕሬስ ስራዎች ኃ.የተ.የግ.ማህበር አሳታሚነት የሚታተም – ሳምንታዊ መጽሄት፣

* ጃኖ መጽሄት በአስናቀ ኢንተርቴይመንትና ፕሬስ ሥራዎች ኃ/የተ/የግ/ማህበር አሳታሚነት – በየ15 ቀኑ የሚታተም መጽሄት፣ እና

* በቅርብ ወደ ሕትመት የገባው አፍሮ-ታይምስ ጋዜጣ (የሎሚ መጽሔት እህት እንደሆነ የሚታመን) ናቸው፡፡

እንደ ፍትህ ሚኒስቴር መግለጫ፤ ክስ የመመሥረት ውሳኔ የተወሰደው ህትመቶቹ ‹‹ምግባራቸውን እንዲያርቁ›› ሌሎች አማራጮች አሟጦ በመጠቀም ያላሰለሰ ጥረት ከተደረገ በኋላ፤ እንዲሁም ‹‹የጥቃታቸው ሰለባ የሆነው ህዝብም በእነዚህ የህትመት ውጤቶች የህግ ከለላ በተሰጣቸው ጥቅሞቹ ላይ ያለማቋረጥ የሚደርሰውን ጥሰት ለማስቆም መንግስት ህጋዊ እርምጃ እንዲወስድ በተለያዩ መንገዶች›› በመጠየቁ ነው ብሏል፡፡እንደመግለጫው ከሆነ፤ ክስ የማቅረቡ ሂደትም ‹‹በማን አለብኝነት በተደጋጋሚ ህጉን በጣሱ እና በሚጥሱ አሳታሚዎችና የመገናኛ ብዙሃን ድርጅቶች ላይ›› ይቀጥላል፡፡

አምስቱ መጽሔቶች በሽያጭ ብዛታቸው በመጀመሪያ ረድፍ የሚሰለፉ አንደሆኑ ሆርን አፌይርስ ከጥቂት ወራት በፊት ከብሮድካስቲንግ ባስልጣን ያገኘው መረጃ ይጠቁማል፡፡

መጽሔቶቹ፤ ባለፈው ጥር በመንግስት በተሠራው ‹‹በሰባት መጽሄቶች በተከታታይ ህትመቶቻቸው በአሉታና በተደጋጋሚ ያነሷቸው ጉዳዮች የአዝማሚያ ትንተና›› የተሰኘ ጥናት ውስጥ የተካተቱ መሆናቸው ይታወሳል፡፡

Source-hornaffairs


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>