Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

An act of Boycott (እቀባ የማድረግ ርምጃ) በአሸባሪነት ያስቀጣ ይሆን?

$
0
0

ጌታቸው ፏፏቴ

Boycottየ21ኛው ክፍለ ዘመን ፋሽስቶች የኢትዮጵያን ሕዝብ በኃይል አንበርክኮ ለመግዛት የመንግሥትን የሥልጣን ቦታ ከያዙ አንድ መቶ ሺ ስምንት መቶ ቀኖች(100800) ሆነዋል።በእነዚህ ቀኖች ውስጥ ታዲያ በእያንዳንዷ መንደር አንድ ሰው ይገደላል፤አንድ ሰው ይታሰራል፤አንድ ሰው ታፍኖ ደብዛው ይጠፋል፤የብዙ ሰዎች ሀብት ይዘረፋል፤ ብዙ ሰዎች ኮቴ ኮቴያቸውን እየተቀጠቀጡ አገር ጥለው እንዲወጡ ይደረጋል፤ብዙ ሰዎች በአሰቃቂ ሁኔታ ይደበደባሉ፤ብዙ ሰዎች አካለ ጎደሎ እንዲሆኑ ይደረጋል፤ብዙ ሰዎች በርሃብ ይቀጣሉ፤ብዙ ሰዎች ህክምና እንዳያገኙ ይከለከላሉ፤የብዙ ሰዎች ጉዳይ ፍትህ ሳያገኝ ያድራል፤በሕግ ዓምላክ የሚባልበት ቦታ ሳይኖር ነው እነዚህ ቀኖች የነጐዱት።

ይህን እኩይ ድርጊት የሚፈጽመው ደግሞ የኢትዮጵያ አንድነትና ነፃነት ታሪክ አልዋጥህ ያላቸው፤ካንዴም ሁለት ጊዜ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ለማስደፈር ሞክረው አልሳካ ያላቸው የምእራቡ አለምና የመካከለኛው ምሥራቅ ዐረብ ቱጃሮች ቅጥረኛ የነበሩ የባንዳ ልጆች ስብስብ ነው።የዚህ መረጃ ወይም ይህን ጉዳይ ጭብጥ ለማድረግ ሩቅ መሄድ የሚያስፈልገው አይደለም።ታሪክን አገላብጦ ማንበብ ነው።ዛሬም ቢሆን ይህን እኩይ በጥላቻ የበቀለና ያደገ ቅጥረኛ ድርጅት እንደ ተሰባሪ ዕቃ ተንከባክበው የያዙትና ያላሰለሰ ጥረት የሚያደርጉት እነዚህ የኢትዮጵያ ጠላት አገሮች ናቸው።ይህን የመሰለ ድጋፍ ባይቸርለት ኖሮ ህወሃት በኢትዮጵያ ምድር አንድ ቀን እንኳን ማደር ባልቻለ ነበር።

መሬት በሰው ልጅ ሙት አካል ስትጫንና የንጹሓን ደም እንደ ውሃ ሲጎርፍ ከዚህ በፊት በኢትዮ-ሶማሌ፤በኢትዮ-ኤርትራ፤በሱዳን መሐዲስቶች፤በግብጽ፤እንግሊዝ፤ቱርክ፤ጣሊያን እንዲሁም እንደ ህወሃት አገር በቀል የሆኑ የግራኝ መሀመድና ዮዩዲት ጉዲት ወረራ ሲካሄድ መከሰቱን ከታሪክ የተማርነውና በአይናችንም ያየነው እውነታ ነው።የቅርብ ጊዜውን የደርግን አረመኔያዊ ጭፍጨፋ ስናነሳም ጥቃቱ የተሰነዘረውና ኢላማው ያደረገው አቅም የሌለውንና ያልተደራጀውን ድኻ አርሶ አደርና ሰርቶ የሚበላ ከተሜ ነበር።

እነዚህን ዘመናዊ ፋሽስቶች የተለየ የሚያደርጋቸው “የምንፈልገው የኢትዮጵያን ህዝብ ሳይሆን  ያፈራውን ሀብትና መሬቱን ብቻ ነው”ብለው የተነሱና በሰው ልጅ ላይ በሚደርስ አሰቃቂ ድርጊት የሚደሰቱ መሆን ነው።መሬቱን ሸጠዋል፤ለተባባሪ የጎረቤት አገሮች በነፃ ሰጥተዋል፤የሀገርና የሕዝብ ንብረት ዘርፈዋል፤ትውልደ ኢትዮጵያውያንንም እንደ ጎመን እየመተሩ ቀጥለዋል።ጊዜው ደርሷል መሰለኝ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ ጭራሹን እንደ አበደ ውሻ ያክለፈልፋቸው ጀምሯል።አንድ አበአዊ አነጋገር አለ »ካልጠገቡ አይዘሉ ካልዘለሉ አይሰበሩ«እንዲሉ ጠገቡ ዝላይም አበዙ የቀረው መሰበርና መሰባበር ነው።ይህን ሁሉ ያመጣው የህዝብና የሀገር ሀብት ተዘርፎ፤ በሀገር ስም የሚለመን የውጭ እርዳታና ከበጎ ለጋሽ አገሮች የሚሰጥ ድጎማ ወደ ህወሃት ካዝና በመግባቱ ነው።

የተተኪውን ትውልድ ተስፋ የሚያጨልም ሴራም እየተካሄደ ነው።የፊተኞቹ ገዥዎቻችን ያሸከሙን የውጭ ብድር ወገብ አጉብጦ እያለ የዛሬዎቹ አይቶ አያውቁ ብሔራዊ ሞራል የሌላቸው ማህይማን ስብስቦች ደግሞ ብድርንና እርዳታን መደበኛ ተግባራቸው በማድረግ ቀጣዩ ትውልድ ከፍሎ የማይዘልቀው እዳ እየከመሩለት ነው።በብድርም ይምጣ እርዳታ መልክ ለሀገር ልማትና ለውስጥ ጉዳይ ውሎ ቢሆን እሰየው ለቁምነገር ውሏል ይባል ነበር።ይህ ግን ገንዘቡ ከመጣበት አገር ተመልሶ በግለሰቦች አካውንት ገብቶ ወደ ግል ሀብትነት መቀየሩ ነው ጉዳዩን የተለየ የሚያደርገው።

አንዳቸውም ሥራቸው አልቆ ለሕዝብ አገልግሎት መስጠት ጀመሩ የሚል ዜና ሰምቸ ባላውቅም ህዝቡን ለማደናገርና ወደ መብት ጥያቄ እንዳይሄድ ለማድረግ በርካታ ፕሮጀክቶች መወጠናቸውን ግን እሰማለሁ። በኢትዮጵያ ስም ከውጭ የሚገኘው ድጎማ ብቻውን የአባይን ግድብ ማስጨረስ ይችላል። ወይም በቅርቡ እንደሰማነው 488 የመንግሥት ቤቶች ለ23 ዓመታት ያህል አንዲት ቀይ ሳንቲም ገቢ ሳያስገኙ የትግራይ ወንበዴዎች በነፃ የኖሩበት ሂሳብ ቢወራረድ የስኳሩንም የአባይንም ጉዳይ ማስፈፀም በቻለ ነበር። ዳሩ ግን ሁኔታው ሌላ ነው ሕዝብን እያዘናጉና እያጭበረበሩ ለመኖር በሌላ መንገድ ደግሞ ኢትዮጵያዊነትን ማጥፋት ነው ማጠንጠኛው።

በነገራችን ላይ አዲሱ ለገሰ አንድ ወቅት በድሬ-ቱቢ ሲናገር ከወንድሙ ጋር በመሆን አባቱን ትጥቅ አስፈታነው ሲል ሰምታችሁ ከሆነ አባቱን ማዋረዱ ሳይሆን የታየው ሀቀኛ አብዮታዊ መሆኑን ነው።እኔ ስከማውቀው ድረስ ደግሞ አዲሱ ወላዋይና አድር ባይ አስመሳይም ነው።የ488 የመንግሥት ቤቶች የወንበዴዎች መኖሪያ መሆኑን ካጋለጡት መሀል አንዷ እንወይ ገብረመድኅን ስትሆን እንዲህ እንደ ዛሬው ብርጫው ሰፊ ባልነበረበት ወቅት እንወይ የአዲሱ ለገሰ ሚስት ነው የነበረች።ታዲያ ጀግናችን አዲሱ ለገሰ የጋሊቲ ሰፈር ልጅ እንወይን ከሥራ አስባረረ፤በዱላም አስደበደበ ታዲያ ይህ ሰው ነው ወይስ አውሬ?እንወይ ለአዲሱ በጣም የምትልቅበት እንጅ የምታንሰው አይደለችም።አዲሱ አሁን ደግሞ ህወሃት የግንባሩን አባላት ገለል በሉ ብሎ ብቻውን መሰብሰብ ሲጀምርና ሌሎችን ከጨዋታ ውጭ ሲያደርግ የአዲሱ ለገሰ ምርጫ ምን ሊሆን ይችል ይሆን?

ወደተነሳሁበት ሳልገባ ብዙ ነገር ነካካሁ እንደምናውቀው ማንኛውም መንግሥት ሲሄድ ሌላ መንግሥት ይተካል።በዚህ ሰአት አዲሱ መንግሥት በመንግሥት ይዞታ ሥር የነበሩ የመንግሥት የተባሉ ተቋማትን ፤ገንዘብን፤ሌሎች የጦር ኃይልን ፤የአየር መንገድን፤የትራንስፖርት አገልግሎትን፤ሕንፃዎችን ከሂያጁ መንግሥት ይረከባል ወይም በኢትዮጵያችን እንደተለመደው በኃይል ይወርሳል።የአሁኑ ሁኔታ ግን በጣም የረቀቀና በአይነቱ የተለየ ነው የጭነትም ሆነ የሕዝብ ማመላለሻ አገልግሎት ሰጭ ተቀሟት፤ራሱ አየር መንገድና የጦርና የፖሊስ ኃይልን ስንመለከት በአንድ ጎሳ የሚመሩና የህወሃት አገልግሎ ሰጭ ናቸው።ጉኡዝ የሆነውን ሕንፃም ይዘውት ባይሄዱም የመጨረሻዋ ቀን ስትደርስ እንደሚያፈርሱት ይታወቃል።

አንድ በወር 4.000.00 ዶላር ገቢ ሊያስገኝ የሚችልን ሕንፃ አንድ የህወሃት አባል የሆነ ሰው ለ23 ዓመታት አንዲት ቀይ ሳንቲም ሳይከፍል መኖር ሲባል በ488 ሕንፃዎች ኢትዮጵያ ልታገኝ ይገባት የነበረውን ገቢ ማሳጣት ማለት እንደ-እኔ ድምጹ በማይሰማ መሣሪያ ኢትዮጵያን መግደል ነው።ይህ አሀዝ ለጊዜው ይቅርብ እንጅ የእነዚህ እኩያን ተግባር ወደ መሀል ገባ ብሎ ሲታይማ ኢትዮጵያውያንን ብቻ ሳይሆን ዓለምን የሚያስደምም ነው የሚሆነው።

«በሬ በስድብ አይታረስም»እንዲሉ ህወሃትን በሰላማዊ ሰልፍ፤በስድብና በጥላቻ ብቻ እንደማንጥለው አውቀን ጥጋቡ ከልኩ አልፎ ዝላይ ስለጀመረ ዘሎ እንዲሰባበር ማድረግ የኛ ፋንታ ነው።በብድር በልገሳ ከውጭ የሚገኝ ገንዘብና ቁሳቁስ፤በሀገር ውስጥ የመንግሥት የነበረና ከሕዝብም የተዘረፈ ገንዘብና ሀብት በህወሃት እጅ ገብቶ ስለሚገኝ ሕዝብ በዚህ ላይ ዘመቻውን ማጧጧፍ ይገባዋል።ዘመቻው ግን የተደራጀና መሪ ያለው መሆን አለበት።መሪ የሌለው ዘመቻ ውጤቱ መጥፎ ሁኔታዎችን ሊያስከትል ስለሚችል የተቃዋሚ ኃይሎች ኃላፊነቱን መውሰድ አለባቸው።በቅርቡ ድምጻችን ይሰማ በማለት ህወሃትን እያርበደበዱት የሚገኙት እስላም ወገኖቻችን ያደረጉትን የ24 ሰአት የቴሌፎን አለመደወል እቀባ እንደ አንድ አብነት ወስደን በሚከተሉት የህወሃት ተቋማት ላይ ለረጅም ጊዜ የሚቆይ እቀባ ማድረግ ከቻልን የህወሃት ጥጋብ በመጠኑም ቢሆን ሊተነፍስ ይችላል ብየ አስባለሁ።

1/ገንዘብ መላክ፦አብዛኛው ኢትዮጵያዊ አነሰም በዛ የሰውነቱ ክፋይ ለሆኑ ወገኖቹ ወደ ሀገር ቤት ገንዘብ ይልካል ይህ የሚላከው ገንዘብ ደግሞ የህወሃት ወደ ሆነው ባንክ ሄዶ ይገባል በዚህ ምክንያት የህወሃትን የገንዘብ(የዶላር) እጥረት ቀረፍንለት ማለት ነው።በሌላ መንገድ ሳናስበው ህወሃትን እያጠናከርን እንደሆነና ሀገር ከሚያፈርስና ህዝብ ከሚጨፈጭፍ ፀረ-ሕዝብ ድርጅት ጋር ተባብረናል ማለት ነው የሚሆነው።ስለዚህ የህወሃትን ባንኮች ለይቶ ማወቅና በነዚህ ባንኮች ገንዘብ አለመላክና አለማስቀመጥ አንዱ ይሆናል።

2/ድሮ የመንግሥት የነበሩ የጭነትና የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች ሥራ እንዲቆም በማድረግ ቦታውን ህወሃት ተክቶ እየሠራበት ይገኛል።የሌሎች የግል ባለሀብቶችን የትራንስፖርት አገልግሎት መጠቀም መቻልና ህወሃትን ከመተባበር መቆጠብ።

3/አቅሙ የተመናመነ ቢሆንም በተወሰነ ደረጃም ቢሆን ህወሃት ገቢ በሚያገኝባቸው ተቋማት ለምሳሌ እንደ ዳሽን ቢራ የመሳሰሉትን ህዝቡ ይገለገልባቸዋል ይህ ደግሞ በተዛዋሪ የፀረ-ሕዝብ ካምፕን ማጠናከር ነው የሚሆነው ስለዚህ በዚህ ዙሪያ ርምጃ(አቋም) መውሰድ ያስፈልጋል።

4/ሆቴሎች፤ሬስቱራንቶች፤ቡና ቤቶች፤ምግብ ቤቶች፤ግሮሰሪዎች በህወሃት እጅ እንደወደቁ ይታወቃል እነዚህን በሀገር ቤትም ሆነ በውጭ አገር ህዝቡ ዘር እንዳይልባቸው ቢደረግና የሌሎችን አገልግሎት ሰጭ ድርጅቶችን ምርት ብንጠቀም ወገንን እረዳን እኛንም ጠቀምን ማለት ነው አልጠግብ ባዮችንና ስግብግቦችን ደግሞ ትምህርት እንዲሆናቸው አደረግን ማለት ነው።

5/በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ትብብርን መንፈግ፤ደህንነት፤ፖሊስና የአጋዚ ሠራዊት አባላትን ስምና የኃላፊነት ደረጃ ማወቅ፤የሚሠሩትን ዘግናኝ ተግባር ዘግቦ በፌስ ቡክና በሌሎች ድረ-ገጾች እንዲነበብ ማድረግ፤አንድ ግለሰብ ላይ ጥቃት ሲሰነዘር ሌሎቻችን ጩኸት ማሰማትና ማደናገጥ ላልሰማው ማሰማት…ወዘተ ተግባራት ገቢራዊ ለማድረግ የተቃዋሚ ኃይሎች የሚከተሉት መንገድ ሊሆን ይገባል ብየ አምናለሁ።

በመጨረሻም ከአንዳርጋቸውና ከሌሎችም እንደተመለከትነው የውጭ አገር ዜግነት አለኝ ብሎ መዘናጋት ከንቱነት ነው።ለአሜሪካም ሆነ እንግሊዝና ሌሎች አገሮች የሚቀርበው አቤቱታና ሰላማዊ ሰልፍም ለጊዜው ስሜትን ለማብረድ ካልሆነ የሚገኝበት ተስፋ የለም።አቀናባሪውና ከኋላ ሆኖ አይዞህ ባዩ ማን ሆነና? ይልቁንስ አንድ ሕዝቡም ሆነ የተቃዋሚ ኃይሎች እጅግ ጠቃሚ መሆኑን እያወቅን ነገር ግን በተግባር የማንፈጽመው ጉዳይ «ህወሃት አጥብቆ የሚፈራውንና የሚጠላውን አንድነት መፍጠር አለመቻል ነው»ይህ ደግሞ ኃላፊነት የጎደለው በሀገርና በህዝብ ላይ ያለንን ደካማ አስተሳሰብ አጉልቶ የሚያሳይ ነው።አመንም አላመን ህወሃት በሚሄድበት መንገድ እየሄድን እንደሆነ ልንቀበለው ይገባል።አሁን በቅርቡ ብቻ ህወሃት የግንባሩ አባላትን እያገለለ የሚሄድበትን መንገድ እንኳ ተገንዝቦ መቀስቀሻ ነጥብ አለማድረግ ትልቅ ድክመት ነው ብየ አምናለሁ።

ቸር ይግጠመን፦ ጌታቸው ፏፏቴ


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>