አንድ ስኒ ቡና ለንቃት ሁለትና ሶስት ድብን ብሎ በመተኛት የካፌይን ተፅዕኖ ሲገለፅ በተለያዩ አጋጣሚዎች ስራ፣ ጥናትንና በአጠቃላይ ለነቃ ውሎ ስንል ካፌይን ብለን የምንጠራውን ኬሚካል የያዙ መጠጦችንና ምግቦችን እንወስዳለን፡፡ በተለይም የዚህ ኬሚካል በብዛት መገኛ የሆኑትና በደከመንና በዛልን ወቅት ከድብርትና ከዱካክ ወጥተን ነቃ እንድንል የምንጠጣቸው ቡና፣ ሻይና የተለያዩ ለስላሳ መጠጦች ዋነኛ ተጠቃች ናቸው፡፡ ካፌይን አዕምሮን የሚያነቃቃ ሲሆን ከላይ ከጠቀስናቸው መጠጦች በተጨማሪ በሌሎች መግቦች ውስጥ ለምሳሌ በብስኩቶችና በቸኮሌቶች ውስጥ እንደዚሁም በአንዳንድ መድኃኒቶች (ለምሳሌ በራስ ምታት መድሃኒቶችና ማስታገሻዎች) ውስጥ በሰፊው የሚገኝ ነው፡፡ በአገራችንም በተለያየ መልኩ በሚሊዮን በሚቆጠሩ ሰዎች የሚወሰድ ነው፡፡ በብዙ ሰዎች በመወሰዱና በመለመዱም በተለያዩ ባለስልጣናትና የሃይማኖት መሪዎች ዘንድ ሳይቀር በ‹‹እፅ›› መልክ የሚወሰድም ነው፡፡ ነገር ግን ካፌይን መውሰድና ሱስ ውስጥ መግባት ከጤና ጋር ተያይዞ የሚመጡ ችግሮችን ሊያስከትል ይችላል፡፡
አንድ ስኒ ቡና ከ100 እስከ 150 ሚሊ ግራም ካፌይን በውስጡ ይይዛል፡፡ ሻይ የዚህን ሲሶ ያህል ካፌይን ሲኖው፣ በአንዳንድ መድሃኒቶች ይህንን ያህል ካፌይን የመገኘት አጋጣሚም ሊኖር ይችላል፡፡ በለስላሳ መጠጦች፣ በጣፋጭ ከረሜላዎችና ቸኮሌቶች ውስጥ እንደዚሁም በብስኩቶችና በሻይ ውስጥም በብዛት መኖሩ ህፃናት ልጆችም ሳይቀሩ በቀላሉ ሊወስዱት ይችላሉ፡፡
በዓለም ዙሪያ በአማካይ በቀን ውስጥ ከ80 ሚሊ ግራም በላይ ካፌይን በየቀኑ ይወሰዳል ተብሎ ይገመታል፡፡ ከካፌይን ጋር የተያያዙ አራት አይነት የጤና ችግሮች አሉ፡፡
1. የካፌይን ስካር (ኢንቶክሲኬሽን)
ይህ ስካር የሚጀምረው ከ250 ሚ.ግ በላይ ካፌይን ከተወሰደ በኋላ ነው፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዘው የሚታዩ ምልክቶች ጭንቀት፣ የህሊና መረበሽ፣ መቁነጥነጥ፣ መነጫነጭ፣ ማቅለሽለሽ፣ ማላብ፣ የሆድ መረበሽ፣ የሽንት መብዛት፣ እንቅልፍ ማጣትና በእግርና በእጅ ጣቶች ላይ የመወረር አይነት ስሜቶች መፈጠር ናቸው፡፡ በዚህ ጊዜ የተወሰደው ካፌይን ከ1000 ሚ.ግ በላይ ከሆነ የአፍ መኮላተፍ፣ የሃሳብ መደነጋገር፣ የልብ ትርታ መዛባት፣ ወፈፍ ማድረግ፣ የሌለና የማይታይ ብርሃን መታየት ሊከተሉ ይችላሉ፡፡ የካፌይን ብዛቱ ከ10,000 ሚሊ ግራም (10 ግራም) በላይ ካለፈ ግን ድንገተኛ ሞት ሁሉ ሊከተል ይችላል፡፡
2. ካፌይን ሳይወሰድ ሲቀር የሚከሰት ህመም
በዚህ ጊዜ የህመሙ አይነትና መጠን ከሰው ሰው እንደሚወሰደውና እንዳስለመዱት ብዛትና የልምድ ጊዜ እርዝመት ይለያያል፡፡ የተለመደው ካፌይን ሲቀር ከሚታዩ ምልክቶች መካከል ራስ ምታት፣ ጭንቀት ወይም መደበት፣ ድካም ወይም መፍዘዝ፣ ማቅለሽለሽ ወይም ማስታወክ ሊከተሉ ይችላሉ፡፡ እነዚህ ካፌይኑ ከቀረ ከ12 እስከ 24 ሰዓታት ውጥ የሚጀምሩ ሲሆን በሁለተኛው ቀን የሚብሱ ነገር ግን በአንድ ሳምንት ውስጥ ተመልሰው የሚጠፉ ናቸው፡፡
3. የእንቅልፍ መቃወስና ጥልቅ የሆነ ጭንቀት
መረበሽ፣ መነጫነጭ፣ መቁነጥነጥ ወይም በአንድ ቦታ ረጋ ብሎ አለመቀመጥን ሊያመጣ ይችላል፡፡ በተለይም የመርበትበትና በሆነው ባልሆነው መደንገጥ ያለባቸው ሰዎች ካፌይን በብዛት ከወሰዱ በኋላ በሽታው ሊነሳባቸው ይችላል፡፡ ስለዚህም በተቻለ መጠን ህመማቸው እንዳያገረሽባቸው ብዙ ካፌዬን መውሰዳቸውን መቀነስ አለባቸው፡፡ ይህ ካልሆነ ደግሞ ትልቅ ጭንቀት ውስጥ ሊገቡ ይችላሉ፡፡
በእንቅልፍ ላይ የሚያመጣውን ለውጥ ስናይ ደግሞ ቶሎ እንቅልፍ እንዳይመጣ ካደረገ በኋላ በቀጣይነት ለረዥም ጊዜ መተኛት አለመቻልና በማለዳ ከእንቅልፍ መንቃትን የሚያስከትላቸው ተፅዕኖዎች ናቸው፡፡
የመፍትሄ እርምጃዎች
የካፌይን አጠቃቀምን ለመቀነስ ወይም እስከ መጨረሻው ለማቆም የመጀመሪያ እርምጃው ምን ያህል ካፌይን በቀን እንደሚወሰድ እና በምን አይነት መንገድ እንደተወሰዱ (በመጠጥ፣ በምግብ፣ በመድሃኒት…ወዘተ) እንደሚወስዱ ለይቶ ማወቅ፡፡
ከዚህ በኋላ በአንድ ጊዜ ሳይሆን ቀስ በቀስ የካፌይን አወሳሰዱን በመቀነስ በሳምንታት ውስጥ የሚፈለገው የተሻለ የመፍትሄ ደረጃ ላይ መድረስ ይቻላል፡፡ ከእነዚህ ጋር አብሮ ካፌይን የሌላቸውን መጠጦችንና ምግቦችን ለይቶ አውቆ እነዚህኑ በምትክ መውሰድን ልማድ ማድረግ አስፈላጊ ነው፡፡ ካፌይን መውሰድ በድንገት በሚቆምበት ጊዜ የሚከተሉትን ህመሞችንና የድብርት ስሜቶች ሲከሰቱ ማስታገሻ መድሃኒቶችን መውሰድ የተሻለ አማራጭ ነው፡፡
ለዚህም ነው አንድ ስኒ ቡና ጥሩ ንቃትን ለመፍጠር ያስችላል፡፡ ነገር ግን ሁለት ሶስት እያልን ስንደጋግም የአንጎላችን የመላመድ ብቃት እየጨመረ ይመጣና በንቃት ከመቆየት ይልቅ ድብን ወዳለ የእንቅልፍ ዓለም ውስጥም ያስገባል፡፡ ይህም የካፌይን ተፅዕኖ ተቃራኒ በሆነ መልኩ የሚፈፅመው ድርጊትም ጭምር ነው፡፡ በአጠቃላይ የካፌይን አጠቃቀማችንን ከምንወዳቸው ምግቦችና መጠጦች አንፃር መጠኑን በመቆጣጠር መቀነስ ሲልም እስከመተው ደረጃ መድረስ እንችላለን፡፡
CAFFEINE SIDE EFFECTS & SAFETY
Caffeine is LIKELY SAFE for most adults when used appropriately. Caffeine can cause insomnia, nervousness and restlessness, stomach irritation, nausea and vomiting, increased heart rate and respiration, and other side effects. Caffeine can make sleep disorders in patients with acquired immunodeficiency syndrome (AIDS) worse. Larger doses might cause headache, anxiety, agitation, chest pain, and ringing in the ears.
Large doses may be UNSAFE and can cause irregular heartbeats and even death.
Special Precautions & Warnings:
Pregnancy and breast-feeding: Caffeine is POSSIBLY SAFE in pregnant or breast-feeding women in daily amounts of less than 200 mg. This is about the amount in 1-2 cups of coffee. Consuming larger amounts during pregnancy might increase the chance of miscarriage and other problems. Caffeine passes into breast milk, so nursing mothers should closely monitor caffeine intake to make sure it is on the low side. Caffeine in large amounts is POSSIBLY UNSAFE during breast-feeding. Caffeine can cause sleep disturbances, irritability, and increased bowel activity in breast-fed infants.
Anxiety disorders: Caffeine might make these conditions worse. Use with care.
Bipolar disorder: Too much caffeine might make this condition worse. In one case, a 36-year-old man with controlled bipolar disorder was hospitalized with symptoms of mania after drinking several cans of an energy drink containing caffeine, taurine, inositol, and other ingredients (Red Bull Energy Drink) over a period of 4 days. Use caffeine with care and in low amounts if you have bipolar disorder.
Bleeding disorders: There is concern that caffeine might aggravate bleeding disorders. Use caffeine with care if you have a bleeding disorder.
Heart conditions: Caffeine can cause irregular heartbeat in sensitive people. Use caffeine with caution.
Diabetes: Some research suggests that caffeine may affect the way the body uses sugar and might worsen diabetes. But the effect of caffeinated beverages and herbs has not been studied. If you have diabetes, use caffeine with caution.
Diarrhea: Caffeine, especially when taken in large amounts, can worsen diarrhea.
Irritable bowel syndrome (IBS): Caffeine, especially when taken in large amounts, can worsen diarrhea and might worsen symptoms of IBS.
Glaucoma: Caffeine increases the pressure inside the eye. The increase occurs within 30 minutes and lasts for at least 90 minutes after drinking caffeinated beverages.
High blood pressure: Consuming caffeine might increase blood pressure in people with high blood pressure. However, this effect might be less in people who use caffeine regularly.
Weak bones (osteoporosis): Caffeine can increase the amount of calcium that is flushed out in the urine. If you have osteoporosis or low bone density, caffeine should be limited to less than 300 mg per day (approximately 2-3 cups of coffee). It’s also a good idea to get extra calcium to make up for the amount that may be lost in the urine. Older women with an inherited disorder that affects the way vitamin D is used should use caffeine with caution. Vitamin D works with calcium to build bones.
(Source: WebMed Megazine)