Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

የአቃቂ ቃሊቲ የአንድነት ፓርቲ ልዩ ኮንፈረንስ ዛሬ በይፋ ተከፈተ – ፍኖተ ነጻነት

$
0
0

UDJ‹‹የነጻነት ትግሉ በአፈና ስር ቢወድቅም ትግሉ ለአንድ አፍታም አይቆምም›› በማለት ኮንፈረንሱን በንግግር የከፈቱት የአዲስ አበባ ከተማ የአንድነት ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ ዘካሪያስ የማነብርሃን ይህ ኮንፈረንስ በአይነቱ ልዩ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ይህ ልዮ ኮንፈረንስ ለሁለት ተከታታይ ቀናት የሚደረግ እና በመዝጊያው ዕለት የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች ፣የብሄራዊ ምክር ቤት አባላትና የወረዳ አመራሮች በአጠቃላይ የአንድነት የአዲስ አበባ አባላት በሚታደሙበት የአቋም መግለጫ በማውጣት በታላቅ ድምቀት እንደሚጠናቀቅ ከወጣው መርሃ ግብር ለማወቅ ተችሏል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ የገዢው ፓርቲ የአስተዳደሩ ሃላፊዎች በሰጡት ጥብቅ ትዕዛዝ መሰረት የአካባቢ ጽዳት እንዲደረግ በማዘዝ ኮንፈረንሱ እንዲደናቀፍ ጥረት ማድረጋቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፤የክፍለ ከተማው የአንድነት ጽ/ቤት ዕድሮች ሊያከራዩት የነበረው ድንኳንና ወንበሮችን እንዳያገኝ ለዕድሮች አመራር በኢህአዴግ ጥብቅ መመሪያ ስለተሰጣቸው ስምምነታቸውን ጥሰው ዕድሮች ለእናንተ አናከራያችሁም ብለው መከልከላቸውን የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ የአንድነት ጽ/ቤት አስታውቋል፡፡


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>